TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NCDO

በወሎ እና በአፋር በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።

#ነሲሓ_የበጎ_አድራጎትና_የልማት_ድርጅት (NCDO) በወሎ እና በአፋር በጦርነቱ ምክንያት ይበልጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ድርጅቱ ከሳምንት በፊት በአፋር ክልል ከሰመራ ከተማ በ270 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ኢሪብቲ ከተማና በጭፍራ ከተማ በመገኘት በጀርመን ኮሎን ኤን አር ቬ የባርባሮሳ ፕላትስ ጓደኛማማቾች ጋር በመተባበር በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ወሎ ውስጥ ከዓለም አቀፍ የሐረሪ ተወላጆችና ሐረሪ ደርሲ ጋር በመተባበር በኩታበር ወረዳ፣ በቦሩ ሜዳ፣ በሐይቅ ከተማ፣ በወረባቦና ቢስቲማ ከተማ በመገኘት ላለፉት ተከታታይ 3 ቀናት ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች ያሰባሰበውን ድጋፍ ለተጎጂዎች አከፋፍለዋል። በወሎ ውስጥ ብቻ በጠቅላላ ለ1 ሺህ አባወራዎች የአንድ ወር አስቤዛ የተሰጠ ሲሆን፤

ለአንድ አባወራ፦
1) ዘይት: 1 ሊትር
2) ዱቄት: 10 ኪሎ
3) ሩዝ: 4 ኪሎ
4) ፓስታ: 4 እሽግ
5) መኮረኒ: 4 ኪሎ
6) የህፃናት አልሚ ምግብ እና ብስኩት
7) የተለያዩ ያገለገሉ አልባሳት ተበርክተዋል።

ጉዳቱ እጅግ የከፋ በመሆኑ የተነሳ ሌሎችም አካላት ርብርብ ያደርጉ ዘንድ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#ነሲሓ

" ነሲሓ የበጎ አድራጎት እና የልማት ድርጅት " በደብረ ብርሃን የመጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ድጋፉ " ዘካተል ፊጥራችንን ለወገኖቻችን" በሚል መሪ ቃል የሚሰበሰብ መሆኑን አመልክቷል።

የበጎ አደራጎት ድርጅቱ " ሙስሊሞች የምታወጡትን #ዘካተል_ፊጥር በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ይሆን ዘንድ በሚከተሉት አካውንቶች እያሰባሰበን ነውና መስጠት ትችላላችሁ !! " ብሏል።

ድርጅቱ በሁሉም ባንኮች የአካውንት ስሙ ነሲሓ በጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን የገለፀልን ሲሆን ቁጥሮች፦
- ንግድ ባንክ 1000328070778
- ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል 1357377300001
- ዳሽን ባንክ 7913417861611
- ንብ ኢንተርናሽናል 7000016912412
- ዘምዘም ባንክ 0001040310301
- አዋሽ ባንክ 01410797317600 ናቸው።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ በ 0972747474 ብትደውሉልን ማንኛውም አይነት ዝርዝር መረጃ መስጠት እንችላለን ብሏል።

@tikvahethiopia