TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ከተያዘው እቅድ ውጭ እኛ የማናቀውን ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

በትግራይ ክልል ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀው ማንኛውም ሰብሰባ ማካሄድ የሚከልክል የስራ መመሪያ ይፋ ተደረገ።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፊርማ ለሁሉም
-  የዞን አስተዳደሮች
- ለወረዳ አስተዳደሮች
- የክፍለ ከተማ አስተዳደሮችና
- የወረዳ ምክር ቤቶች 
የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፈቀደው ውጪ ሌላ ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም ይላል።

➡️ የኮሌራ በሽታ መከላከል
➡️ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መመለስና የክልሉን ግዛታዊ አንድነት ማስከበር
➡️ የ2016 ዓ.ም በጀት መዝጋትና የ2017 ዓ.ም በጀት ማዘጋጀት ... ሌሎች ህዝባዊና መንግስታዊ እቅዶች የጊዚያዊ አስተዳደሩ መሆናቸው የጠቀሰው የስራ መመሪያው ፤ " ከዚህ ውጪ የሚደረጉ ሰብሰባዎች የተያዘው እቅድ ስለሚጎዱ አይፈቀዱም " ብሏል።

ከላይ ከተጠቀሱት እቅዶች ውጪ ማሰተናገድ የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስራ በማደናቀፍ #ተጠያቂነት_የሚያስከተል መሆኑን  በመግለጽ አስጠንቅቋል።

የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ይህኑን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia