TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " የህዝቡን ኑሮ አይታችሁታል ? ይሄ ማህበረሰብ ከኮሪደር ልማቱ ይልቅ የዕለት ጉርሱን ሸፍኖ የሚበላበት ነገር አያስፈልገውም ? " - ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ የኮሪደር ስራው ላይ የሚነሱት ጥያቄዎች ምንድናቸው ? የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ ይቀይራል የተባለው የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል። አሁን ላይ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ስራ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ነው።…
#AddisAbaba
ለምን የልማት ተነሺዎችን እዛው ቦታቸው ላይ ቤት ሰርቶ ማስገባት አልተቻለም ?
በአዲስ አበባ ከሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ጋር በተያያዘ በርካታ ነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ከኖሩባቸው ሰፈሮች እንዲነሱ እየተደረገ ነው።
አስተያየት ሰጪዎች ፤ " ይሄ ነገር ነባር የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመሃል ለማስወጣት ፤ የማህበራዊ ትስስሩንም ለመበጣጠስና ፤ ነባሩን ነዋሪ ለመበታተን ፤ የልማት ተነሺ ቦታዎችንም ለሚፈልጉት ባለሃብት ለመስጠት ነው ፤ እውነት ልማት ከሆነ ለምን ባሉበት በኖሩበት ቦታ የጋራ መኖሪያ ቤት አይሰራላቸው ? " ሲሉ ይጠይቃሉ።
ከሰሞኑን ከንቲባ አዳነች በተገኙበት ከዚሁ ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዘ የውይይት መድረክ ላይ ፤ " ለምን የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ከተገነባ በኃላ ከለማ በኃላ በነበሩበት ቦታ መኖር አይችሉም ? ልክ እንደ አዋሬ ለምን አልተደረገም ? እዛው እንዲኖሩ ለምን ማድረግ አልተቻለም ? " የሚል ጥያቄ ተስቷል።
እንዲሁም ረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ ነዋሪዎች ፦
- ከእድራቸው
- ከእቁባቸው
- ከሰንበቴያቸው ፤ በእስልምናም በኩል ያሉት የማህበረሰቡ መገናኛዎች እንዲበተኑ እየተደረጉ ነው የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምን መለሱ ?
" እዛው አካባቢ ላይ ብታለሙ አይሻልም ወይ ? እውነት ነው ይሻላል እንላለን። በነበሩበት አካባቢ ቢሆን የበለጠ ቅድሚያ የሰጠዋል።
አዋሬ እንደዛ ነው የለማው። አዋሬ ብቻ ሳይሆን 70 ደረጃ የገነባናቸው ቤቶች እዛው ሰፈራቸው ነው። በተመሳሳይ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ የበጎነት መንደር ብለን የሰራነው እዛው ነው። ለሚኩራም ሎውኮስት ሀውስ የተሰሩት እዛው ነው፣ ጉለሌ፣ አየር ጤና ሁሉንም መዘርዘር ይቻላል።
ሰፋፊ አካባቢዎችን ስናነሳ አንደኛ የሚገነባበት ቦታ የለም ፤ ካልተነሱ በስተቀር። ሁለተኛ በጥናታችን ሲገነባ የመስረተ ልማቱ የፍሳሽ፣ የጎርፍ መውረጃው የከተማ ልማት የመሬት አጠቃቀሙ የመኖሪያ ቤት መሆን የሌለበት አካባቢ አለ። ተዘግቶ የተገነባበት አለ ጥናቱ በዝርዝር ያስረዳል።
ስለዚህ ሰፋ ወዳለ ቦታ ይሄንን ማህበረሰብ መውሰድ ያስፈልጋል። ቤት ብቻ አይደለም ያየነው። በአካባቢያቸው የሚያስገልጉ ሌሎች መሰረተ ልማቶች አብረው መኖር አለባቸው።
ሌሎች ሀገሮችን እኮ እናውቃለን መኖሪያ ቤቶች መሃል ዋናው ከተማ ላይ ናቸው እንዴ ? ንጹህ አየር ወዳለበት ከተማ ውስጥ ነው ከከተማ አልወጣም። እዚህ ነው የተሻለ ቦታ የተሻለ ሰፋ ያለ ለልጆችም የሚሆን ፤ ብዙ ሰው ሊይዝልን የሚችል ቦታ ላይ ገንብተን አዲስ ቤት መሰረተ ልማት የተሟላለት ቤት አስገብተናል።
ጥያቄ የምታነሱ ወገኖቻችን ኑ አብረን እንሂድና ገላን ጉራን፣ አቃቂን እንመልከት ፣ አቃቂ የቁጠባ ቤቶች ግቢ እንሂድ አብረን ፣ አራብሳ ግቢም የልማት ተነሺዎች የገቡበት አካባቢን እንይ።
አንዳንድ ቦታዎች የተጠቆሙ (የመሰረተ ልማት ችግር ያለባቸው) ካሉ እንደግብዓት እንወስዳለን ህዝባችን እንዲንገላታ አንፈልግም ፤ ህዝባችን እንዲንገላታ ምንም አይነት ፍላጎት የለንም።
ግን እሱም ቢሆን ይኖሩበት ከነበረው ጋር አይወዳደርም።
ከማህበራዊ ትስስራቸው ተበታተኑ የሚለው ፍጹም ውሸት ነው። አልተበታተኑም። የአንድ አካባቢ ሰዎችን አንድ አካባቢ ነው ዕጣ ያስወጣነው። ዕጣውን ለሁሉም ከየአካባቢው ለሚነሱት በጋራ አይደለም ያደረግነው ቀጠናቸውን እንኳን ጠብቀንላቸዋል።
እቁብ፣ እድር፣ ማህበር አላቸው፣ ትስስር አላቸው። ' አይ የቁጠባ ቤት ላይ አንገባም ኮንዶሚኒየም ነው ' ሲሉ የተወሰኑ ሰዎች ኮንዶሚኒየም ሲመርጡ ወደ ሌላ ሄደው ሊሆን ይችላል። ይሄ ለተባለው ግን በቂ ማሳያ አይሆንም።
ባለቤቱ መርጦ ' ይሄ ይሻለኛል በዛው ንብረት ይዛለሁ የጋራ መኖሪያ ቤት ማግኘት ማለት ባለቤት መሆን ነው በቁጠባ እየከፈልኩ ከምኖር ባለቤትነትን እመርጣለሁ ' ካለ ለምንድነው ? ከማህበራዊ ትስስርህ ተነጥለህ ፤ እዚህ እቁብ፣ እድር አለ እዚህ ሰፈር ካልሆነ አትገባም አንለውም። እንደዛ የተባለ ካለ ይዛችሁ ኑ " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaAddisAbabaFamily
@tikvahethiopia