TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።

የከተራና የጥምቀት በዓልን ተከትሎ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር ለትራፊክ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በጥምቀት በዓል በርካታ ህዝብ ታቦታትን አጅቦ ከተለያዩ ቤተ-ክርስቲያናት ወደ ጥምቀተ ባህር የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በትራፊክ ፍሰቱ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታቦታቱ በሚጓዙባቸው መንገዶች ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን በተለይም በርካታ ህዝብ በሚታደምበት በጃን ሜዳ ከጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው እስኪመለሱ መንገዶቹ ለተሸከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

- ከ6ኪሎ አደባባይ እስከ 3ተኛ ሻለቃ ፈረንሳይ ለጋሲዬን መንገድ

- ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ በምንሊክ ሆስፒታል እስከ ቀበና አደባባይ

- ከምንሊክ ሆስፒታል እስከ 6 ኪሎ ታክሲ ተራ

- ከቅድስተ ማርያም ቤ/ክርስቲያን እስከ 6 ኪሎ፣

- ከ6ኪሎ እስከ መነን፣

- ከሀምሌ 19 እስከ ግብፅ ኢምባሲ፣

- ከቅድስተ ማሪያም መነጸር ተራ እስከ ጃንሜዳ፣

- ከግንፍሌ ድልድይ ምንሊክ ሆስፒታል ውስጥ ለውስጥ፣

- ከግንፍሌ መገንጠያ ምንሊክ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣

- ከምንሊክ ሆስፒታል የኋላ በር እስከ ቤላ መገንጠያ ድረስ፣ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳና በዙሪያው ተሽከርካሪ አቆሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ እየገለፀ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትእዛዝ በመቀበል የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ከላይ የሚታዩት ተጠርጣሪዎች ተሽከርካሪ በመጠቀም እየተንቀሳቀሱ የማታለል ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች እንደሆኑና አሁን ላይ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
                         
እንደ ፖሊስ መረጃ ፤ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ " 3-B48631 አ.አ " በሆነ ተሽከርካሪ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።

ግለሰቦቹ  በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው 6 ኪሎ ዩኒቪርሲቲ አንደኛ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በፈፀሙት ወንጀል ነው የተያዙት።

ተጠርጣሪዎቹ ባንኮች ላይ ትኩረት አድርገው ሲንቀሳቀሱ የነበር ሲሆን ፤ በዚሁ አካባቢ በሚገኝ አንድ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ አንዱ ተጠርጣሪ ስራ አስኪያጁን የNGO አካውንት ለመክፈት እንደፈለገ ይነግረዋል።

ስራ አስኪያጁም አስፈላጊ መስፍቶችን ይነግረዋል ፤ በኃላም ፎቶና ሌሎች መስፈርቶችን አሟልቶ እመለሳለሁ ይላል። ቀጠል አድርጎ ድርጅታቸው በቅናሽ የሚሸጣቸው 53 ኢንች ሁለት ቴሌቪዥኖች ስላሉ የሚገዙ ከሆነ ይውሰዱ ሲል ይናግረዋል።

ስራ አስኪያጁ ቴሌቪዥን መግዛት እንደሚፈልግ ፤ እጁ ላይ ግን ያለው 3 ሺህ ብር እንደሆነና 12 ሺህ ተበድሮ 15 ሺህ ብር መስጠት እንደሚችል ይገልጻል። በዚህ ወቅት ተጠርጣሪው ችግር የለም ሌላ ጊዜ ቀሪውን ገንዘብ ወስዳለሁ ይላል።

ስራ አስኪያጁም ብሩን ሰጥቶ ቴሌቪዥኑን ለመረከብ አንድ የራሱን ሰው አብሮ ይልካል። ልክ ከባንክ እንወደጡ ከላይ ያለችው መኪና (የግብረአበሩ) ውስጥ ይገባሉ። ጥቂት ተጉዘው 6 ኪሎ ሲደርሱ ተጠርጣሪው ብሩን የያዘውን ሰው ብሩን ስጠኝ ብሎ ይቀበላል።

ሹፌሩ (ግብረአበር) መኪናውን ሲያቀዘቅዝ በሩን ከፍቶ ቴሌቪዥንኑን ሊያመጣ የተላከውን ሰው ወርውሮ ይጥለውና በፍጥነት ይነዱታል።

በወቅቱ በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የወንጀል መከላከል ስራ ሲሰሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት በደረሳቸው ጥቆማ ወንጀሉን ፈፅሟል የተባለውን ግለሰብ ከነ ግብራበሩ እና ሲጠቀሙበት ከነበረው መኪና ጋር ተከታትለው በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ከ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የሚኒስትሮች ስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀ ፦

ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት

ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሔራዊ ቤተ - መንግስት -በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ

ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶቹ እንግዶች ሲያልፉ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለእንግዶቹ ቅድሚያ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑና ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ ፦

ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን

ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ሐሙስ የካቲት 7 ቀን / 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

ይህ ተከትሎ መንገዶች ይዘጋሉ።

በዚህም መሰረት፡-

- ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ

- ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ

- ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ

- ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ

- ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት

- ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ

- ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን

- ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #AddisAbaba

ነገ መንገድ ይዘጋል።

ነገ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ሩጫ ይካሄዳል።

ሩጫው የ2016 " የኢትዮጵያ ታምርት " የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ነው።

የአዲስ አበባን ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልል እንደሆነም ታውቋል።

መነሻው መስቀል አደባባይ ከዛም በለገሃር ፣ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎተራ ማሳለጫ ፣ አጎና ሲኒማ ፣ ጥላሁን አደባባይ አድርጎ መዳረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል።

ይህን ተከትሎ ሩጫው ተጀምሮ እስኪያልቅ የሚዘጉ መንገዶች እንዳሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

- ከመገናኛ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ
- ⁠ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል
- ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ አጎና መስቀለኛ
- ከጎርጎሪዎስ አደባባይ ወደ ጎተራ
- ከጎተራ ሼል ወደ ጎተራ
- ከማሞ ማቋረጫ ወደ ጎተራ
- ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
- ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ቄራ በረት
- ከመካኒሳ አቦ አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
- ከካርል አደባባይ ወደ ሳር ቤት አደባባይ
- ከልደታ ፀበል ወደ ኤዩ መብራት
- ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደኤዩ መብራት
- ከኦርቢስ መታጠፊያ/ጮራጋዝ/ መስቀለኛ ወደ ሲጋራ ፋብርካ
- ከጠማማ ፎቅ ወደ ጥይት ፋብርካ
- ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ወደ ገነት መብራት
- ከከፍተኛ ፍ/ቤት /ባልቻ ሆስፒታል/ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከአረቄ ፋብርካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
- ከሠንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት
- ከበድሉ ህንፃ ወደ ቴሌ ባር
- ከብሔራዊ ቲያትር መብራት ወደ ለገሃር መብራት
- ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት
- ⁠ከብ/ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
- ⁠ከኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

#AddisAbabaPolice #እንድታውቁት

@tikvahethiopia
" የመኪና እቃ የተሰረቀባችሁ በአካል ቀርባችሁ ንብረታችሁን ምረጡ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በከተማይቱ የመኪና እቃ ስርቆት ወንጀል ስጋትን ለመቀነስ ሕግን መሰረት ያደረገ ኦፕሬሽን በልደታ ፤በአራዳ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዋሳኝ ወረዳዎች ላይ መስራቱን አሳውቋል።

ፖሊስ በተለምዶ ሱማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ባካሄደው ኦፕሬሽን ፦
528 ልዩ ልዩ ፍሬቻዎችን ፣
187 ስፖኪዮችን ፣
113 የመኪና መብራቶች ፣
172 የዝናብ መጥረጊያ በአጠቃላይ 33 ልዩ ልዩ በድምሩ 1 ሺ 269 አይነት የመኪና እቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡

የተሰረቁ የመኪና እቃዎችን ሚገዙና የሚያሻሽጡ 89 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን ገልጿል።

በተለያየ ጊዜ የመኪና እቃ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ፦
° በልደታ ፣
° በአራዳ
° በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች በመቅረብ  ንብረታቸውን መምረጥ እንደሚችሉም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ በከተማው ለመኪና እቃ ስርቆት መስፋፋት ልዩ ልዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በተለይ ወንጀለኞችን በማደራጀትና በማሰማራት የመኪና እቃ የሚያሰርቁ እና የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለወንጀሉ መስፋፋት ዋና ምክንያት ናቸው ብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተለያየ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የመኪና ስፖኪዮ በመስረቅ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች (ታዳጊ ልጆች) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቂርቆስ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ሚያዚያ 23 እና 24/ 2016 ዓ.ም ወረዳ 2 ጋዜቦ አደባባይ እና ወረዳ 9 አካባቢ ነው የተያዙት ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ #ከመስቀል፣አደባባይ ወደ #ቦሌ በሚወስደው መንገድ ላይ የትራፊክ መብራቶችና ተሽከርካሪ በሚቆምባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ስፖኪዮ ሲሰርቁ እንደነበር ፖሊስ አመልክቷል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ለይ ተሳትፈው የተገኙት ህፃናቶች መሆናቸውን ገልጿል።

በዚህ መነሻ በተደረገ ምርመራ ለህፃናቱ ስምሪት የሚሰጡ የተደራጁ ወንጀለኞች መኖራቸውን ፖሊስ ማረጋገጡን አሳውቋል።

" አንዳንድ ህፃናት መኪና የሚጠብቁ እንዲሁም ደግሞ እርዳታ የሚፈልጉ መስለው በመቅረብ የወንጀል ተግባራት እንደሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ተገንዝበው በትራፊክ መብራቶችም ሆነ የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ሌሎች ቦታዎች ላይ ሲቆሙ እና በዝግታ ሲያሽከረክሩ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል " ሲል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በማህበራዊ ሚዲያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን / ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ #ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 " አማረ እና ቤተሰቦቹ " በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማና በፖሊስ ክትትል ተይዘዋል።

አሁን ላይ የካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ፦
- ሮሄ፣
- ልዩነት፣
- ጣዕም፣
- አዲስ አለም፣ 
- ዘይቤ፣
- ህይወት፣
- እይታ፣  እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ ነበር።

ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፊ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ ናቸው።

ከላይ ከተጠቀሱት 8 የዩቲዩብ ገፆች በተጨማሪ #ክህሎት እና #ሲንግል የተባሉ ሌሎች ሁለት የዩቲዩብ ገፆችም በዚያው ህንፃ ላይ የፈጠራ ወሬ ሲፈበርኩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ተከራይተው በሚሰሩበት ህንፃ 8ኛ እና 13ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአቸው ላይ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ የፈጠራ ወሬ ለመቅረፅ እና ለማሰራጨት የሚጠቀሙባቸው የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

ግለሰቦቹ መረጃውን ለማሰራጨት የሚያስችል ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የህጋዊነት ማረጋገጫ ሆነ ፈቃድ እንደሌላቸው በምርመራ ሂደት ተረጋግጧል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬዎቹን የሚሰራጩት ታሪኩን ለሚተውኑላቸው ግለሰቦች #ገንዘብ_በመክፈል ሲሆን በወቅቱ ጉዳዩን በጥልቀት ሳይረዱ እና መረጃው ሳይኖራቸው የማያውቁትን የፈጠራ ታሪክ ሊሰሩ ለቀረፃ ስራ የተጠሩ ሌሎች 3 ሰዎችን ፖሊስ አግኝቷል፡፡   
 
መሰል የውሽት ታሪኮችን ቀልብ በሚስብ መልኩ እያቀናበሩ በማሰራጨት በህብረተሰቡ ላይ መደናገርን የሚፈጥሩ ሌሎች ግለሰቦችም ተለይተው የታወቁ  እና በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትል ስራው ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ከሌቦች የሚረከብ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ማሞ ድልድይ አካባቢ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከማለዳ 12 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ግለሰብ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ባደረገው ክትትል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከሌቦቹ ላይ የሚረከብ " ታምራት ፍቅረማርያም " የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በእለቱ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክና በልዩ ልዩ ጊዚያት ከሌቦች የተረከባቸውን ፦
➡️ 61  ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣
➡️ 251 የታብሌት ስልክ ሽፋኖችን ፣
➡️ 2 ላፕቶፖችን እና በጥሬ 60 ሺ አንድ መቶ ብር ከሌባ ተቀባዩ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ መያዙን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከሌቦች ተቀብሎ የሚያስቀምጠው በተከራየው ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።

ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራይን ማንነነት እና በምን ስራ ላይ እንደተሰማራ የማረጋገጥ ግዴታ እንደለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

" የሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል / ተሰርቂያለሁ " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ስልኩን በመለየትና አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ጓደኛቸውን #በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ተያዙ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ ነው።

ጓደኛማቻቾቹ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል።

ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ካበናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ " ወለቴ " ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት አረጋግጧል።

መኪናውም ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማወል ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia