TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ‼️

ከሰሞኑ በሀገራችን በሚገኙ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ #ያልተፈፀመን ድርጊት የተፈፅመ በማስመሰል በተማሪዎች መካከል #መጠራጠርና አለመረጋጋት ተፈጥሮ የትምህርት ሂደቱን የማደናቀፍ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው፡፡

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲም አንዲት ተማሪ ላይ በደረሰ #የአስገድዶ_መድፈር ጥቃት ህይወቷ አለፈ የሚል #የሀሰት መረጃ በማሰራጨት በተማሪዎች መካከል ድንጋጤና ተቃውሞ ተፈጥሮ #የብሄር ተኮር የቡድን ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ ተደርጎ ትናንት ምሽት ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም በዋናው ግቢ ጥቂት ተማሪዎች በቡድን እንዲደባደቡ ምክንያት ሆኗል፡፡ በግጭቱ በተማሪዎች ላይ የከፋ ጉዳት አልተከሰተም፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱ ዛሬ በከፊል የተካሄደ ሲሆን በዩኒቨርሲቲያችንም ዛሬ የፀጥታ ችግር ያልተከሰተ ሲሆን የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታይ ተማሪዎችም ዓመታዊ የቅዱስ ሚካኤል የንግስ በዓልን ገንደ ጄይ አካባቢ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ተገኝተው አክብረው ተመልሰዋል፡፡

በተማሪዎቹ መካከል ተከስቶ የነበረው ችግር ዳግም እንዳይከሰት ሊደረግ በሚገባው ጥንቃቄ ዙሪያ ከተማሪዎች ተወካዮችና የጸጥታ አካላት ጋር ዛሬ #ውይይት የተደረገ ሲሆን ተማሪዎችም ችግሩ ዳግም እንዳይከሰት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር እንዲቻልም ነገ ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የኃይማኖት አባቶች ፤ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በሚገኙበት የዕርቅና የይቅርታ መድረክ ለማዘጋጀት ተስማምተዋል፡፡

ከሰሞኑ በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ የከፍተኛ ትምህርትና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም መግለጫ አውጥቷል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

ዛሬ በብዛት ሼር እየተደረገ ያለ #የሀሰት ዜና የሱዳኑ መሪ ሀሰን አልበሽር ስልጣናቸውን ለቀቁ። የዜናው ምንጭ አፍሪካን ዴይሊ የሀሰት ዜናን ከትክክለኛው በመፐወዝ ይታወቃል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ‼️

በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳሰበ፡፡

በድሬድዋ ከተማ ግጭት የተፈጠረው ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የጥምቀት ማግስት የቃና-ዘገሊላ በዓልን በሚያከብሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች በፈጠሩት ረብሻ ሳቢያ ነው፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡስማን በስልክ ለአብመድ እንደተናገሩት በዕለቱ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ችግር በሁለት እና ሦስት ቀናት ወደ ተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ተስፋፍቷል፡፡

‹‹ሃይማኖታዊ በዓሉን በመረበሽ የድሬዳዋ ከተማን አንድነት መሸርሸር እና አገራዊ ሰላምን ለማደፍረስ ታስቦ የተሠራ ነው›› ብለዋል ከንቲባው፡፡ ግጭቱን ሃይማኖታዊ መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ፀብ የማጫር ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ አካላት መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡ ከክብረ በዓሉ ቀደም ብለው ጭምር ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበርም ነው አቶ ኢብራሂም የጠቆሙት፡፡

ቀደም ብሎ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግም ሌላ የግጭት አጀንዳ እንደተነደፈ አስታውቀዋል፡፡ እንደ ከንቲባው ገለጻ ችግሩን የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የጎሳ እና የፖለቲካ መልክ ለማስያዝ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡

ሰላም በመደፍረሱ ምክንያት የዝርፊያ ወንጀሎች እየተባባሱ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

በተለይ ወደ ባንኮች ተደራጂቶ የመሄድ አዝማሚያ መኖሩን፣ መንገድ የመዝጋት፣ የግለሰቦች ቤትና ንብረት የማውደም እና የተወሰኑ የመንግሥት ተቋማት ላይ ጉዳት የማድረስ ሁኔታዎች በከተማዋ መስተዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡

የከተማዋን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ‹‹ለዚህም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ ነው፡፡ ከግጭቱ ጀርባ ስውር አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ከ80 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ለሕግ የማቅረብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ነው ያሉት ከንቲባው፡፡

‹‹ችግሩ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ #የመከላከያ_ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊሶች ወደ ከተማዋ ገብተዋል›› ያሉት ከንቲባው ዛሬ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አስታውቀዋል፡፡

‹‹አንድ ስፍራ ብቻ አሁንም ችግሩ አለ፤ የፀጥታ ኃይሎች ሰላም ለማስከበር ወደ ስፍራው አቅንተው ሰላም የማስከበር ሥራ እየሠሩ ነው›› ብለዋል አቶ ኢብራሂም፡፡

ድርጊቱ የድሬዳዋን ሕዝብ የዘመናት አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡

በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው #የሀሰት_ወሬ የድሬድዋን ከተማ ብቻም ሳይሆን የሀገሪቱን ሰላም #ለማደፍረስ እንደ ቤንዚን የሚጠቀሙ ስውር የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው አካላት በመኖራቸው መጠንቀቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
FAKE NEWS‼️

"ሰበር ዜና!! የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል president ሙክታር ከድር እና የቀድሞ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ ዛሬ ከመኖሬያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ #ተይዘዋል!!ምንጭ፦ OBN"
.
.
የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ #አድማሱ ወሬው #የሀሰት መሆኑን ለAPው ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት አረጋግጠዋል። አቶ አዲሱ አረጋም "fake news" ብለው በሜሴጅ ለአለም ኣቀፉ ጋዜጠኛ አሳውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

በርካታ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች እና ብዙ የሶሻል ሚድያ ተከታታይ ያላቸው ግለሰቦች የአፍሪካ ህብረት አማርኛን ስድስተኛ የስራ ቋንቋው አድርጎ እንደመረጠ ትናንት ሲፅፉ ነበር። እውን ሆኖ "እልል" ባስባሉን እያልኩ ነበር፣ ነገር ግን መረጃው #የሀሰት ነው።

ዛሬ በጠዋቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ቃል አቀባይ የሆነችው ኤባ ካሎንዶ ጋር ደወልኩ። በመልሷም፦

"የቋንቋ ምርጫ የመሪዎቹ አጀንዳ ላይ ጭራሽ አልነበረም። እርግጥ ጠ/ሚር አብይ ስለ አፍሪካ ሀገር በቀል ቋንቋዎች ጥቅም አውርተዋል። የኢኳቶርያል ጊኒው መሪም ቋንቋቸው የአፍሪካ ህብረት ቋንቋ እንዲሆን ይፈልጋሉ። ይህ ማለት ግን ሆኑ ማለት አይደለም። ስለዚህ ኤልያስ፣ አማርኛ የአፍሪካ ህብረት ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሆነ የተባለው የሀሰት ዜና (fake news) ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የፌደራል ስርዓት ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም" --- ኦዲፒ
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታወቀ። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።

ለፌደራል ስርዓቱ መምጣት ከፍተኛ ዋጋ ተከፍሎበታል ያለው ፓርቲው፥ ስርዓቱ ለድርድር የማይቀርብ መሆኑንም አስታውቋል በመግለጫው። በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ #የሀሰት_ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንም ኦዲፒ በመግለጫው አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅትም በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የፌደራል ስርዓቱን ሊያፈርስ እንደሆነ እንዲሁም ህብረተሰቡ በፌደራል ስርዓት ላይ ያለውን እምነት እና ተስፋ እንዲቀንስ ከፍተኛ የሆነ የሀሰት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንም ገልጿል።

የሀሰት ዘመቻው ሁለት ዓላማ ያለው ነው ያለው ኦዲፒ፥ ከእነዚህም አንደኛው የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሁን ያለውን ለውጥ በጥርጣሬ እንደሚመለከቱ ማድረግ ነው ብሏል።

በዚህም የራሳቸውን ባህል፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ታሪክ ማሳደግን በትግል እና በመስዋእትነት ያገኙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የፌደራል ስርዓቱ ሊፈርስ ነው በሚል በጥርጣሬ ተቃውሞ እንዲያስነሱ ታስቦ የሚደረግ ሴራ መሆኑንም ገልጿል።

በተጨማሪም የኦሮሞን ህዝብ “ተጨማሪ መብት ማግኘትህ ቀርቶ ከዚህ ቀደም የተገኘውን መብት ልታጣ ነው” በሚል በማደናበር እርስ በርስ ለማጋጨት ያለመ መሆኑንም አስታውቋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ለመመለስ እንደሚሰራ በመግለጽ፥ የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሰራበት ያለ መሆኑን ገልጿል።

ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ላይም ትኩረት በመስጠት እየሰራበት መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል።

ኦዲፒ ለተጨማሪ ድል ይሰራል እንጂ ከዚህ ቀደም የተገኙ ድሎችን አያከሽፍም ያለው ፓርቲው፥ በፌደራል ስርዓት ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥም ገልጿል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

በአርቲስት #ሙሉቀን_መለሰ "ህልፈት" ዙርያ የተሰራጨው መረጃ #የሀሰት ሆኖ ተገኝቷል።

Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/ @eliasmeseret /
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዜጎች በሀገራቸው ያለስጋት መኖር እንዲችሉና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ኅብረተሰቡ በተደራጀ አግባብ ተንቀሳቅሶ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጠየቁ፡፡ ከደቡብ ወሎ ዞንና ደሴ ከተማ መሪዎች ጋር በደሴ ከተማ ውይይት ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚስተዋለው ሥርዓት አልበኝነት፣ የስልጣን ጥማት፣ የግል ጥቅም ፍለጋ፣ የደቦ ፍርድና #የሀሰት_መረጃ የሕግ የበላይነትን እየሸረሸረ እንደመጣ ገልፀዋል፡፡

Via ኢዜአ
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ክለቦች ለመገናኛ ብዙሃን የሚያደርሷቸው #የሀሰት ውንጀላዎች የኢትዮጵያን እግር ኳስ ዕድገትን ያቀጭጨዋል እንጂ አያሳድገውም!" የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በየጊዜው ግድቡ ቆማል በሚል በግብፅና በተለያዩ አፍራሽ ኃይሎች የሚሰራጨውን #የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመያዝ አሉታዊ መልዕክት የሚያስተላልፉ አካላትን ውሸትና ሴራ የምናጋልጠው ግንባታውን በተግባር በማፋጠን ብቻ ነው።" ዶ/ር አብርሃም በላይ/የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
" የእኛን ምሩቃን ለመቅጠር ስትፈልጉ የትምህርት ማስረጃቸውን #ለማረጋገጥ ጠይቁን ፤ ትክክለኛውን ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ እንሰጣችኃለን " - ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፤ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገው የትምህርት ማስረጃ ማጣራት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም የተሠሩ #የሀሰት የትምህርት ማስረጃዎች መገኘታቸውን አሳወቀ።

ተቋሙ ፤ ህገወጥ የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት በተሰራው ስራ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ትክክለኛ ያልሆነውን ውጤት በራሳቸው ጊዜ የራሳቸው አድርገው ውጤት ማሻሸል እንደቻሉ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

" ይህ አሳፋሪ ወንጀል ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ግለሰቦቹ ይህን በመፈፀም በአቋራጭ መንገድ ስራ የመቀጠር እና የሌሎች ሰዎች የስራ እድል ጭምር በማጥፋት ድርጊት መሰማራታቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን ስም ለመጥፋት እንደሞከሩ ገልጿል።

በእንደዚህ ዓይነት የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ላይ መሳተፍ ከዜጎች የማይጠበቅ ተግባር ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ባለፈ ማንኛውም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የግል ተቋማትና ድርጅቶች ከዛሬ ህዳር 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የተመረቁ ምሩቃንን ለመቅጠር ሲፈልጉ የተቀጣሪዎችን መረጃ በፖስታ ቁጥር P.O.Box 667 እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ኢሜይል email address: [email protected] በመላክ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የምሩቃንን ትክክለኛውን የትምህርት ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ ሰጣለሁኝ ብሏል።

* ከላይ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ስም የተያያዘ ሲሆን አብዛኞቹ በተለያዩ የሀገሪቱ #ባንኮች ውስጥ እንዲሁም በመንግሥት መ/ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopia