TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለትውስታ ከአምናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቲክቫህ ቤተሰቦች ጉዞ...

ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ፤ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩና በማህበራዊ ሚዲያ(ቴሌግራም) ብቻ የተሰባሰቡት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች...

በልዩነቶቻቸው ተከባብረው፤ በሰውነታቸው ተዋደው፤ ከምንም ነገር በላይ ሰብዓዊነታቸውን አስቀድመው፤ ጥላቻን፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ሰዎችን በማንነታቸው ማሸማቀቅን፣ መግፋትን፣ ሰዎችን በሰውነታቸው አለማክበርን #ተፀይፈው "ነጩን የሰላም ምልክት፣ባንዲራ ተሸክመው ለሀገራች ህዝቦች ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር።

ለሀገራቸው ሰላም እና ፍቅር ቀና አስበው፤ ያለ አንዳቸው የግለሰብም ሆነ የድርጅት ድጋፍ፣ የትምህርት ጊዜያቸውን ሰውተው፤ ረጃጅም ጉዞዎችን እየተንገላቱ ተጉዘው፤ ከቤተሰባቸው ከሚላክላቸው ገንዘብ ቀንሰው ለጉዞ አውለው፣ ከራሳቸው ኪስ አውጥተው ተመገበው፣ የሚስማማቸውን ምግብ ካገኙ በልተው ከሌለም ፆም አድረው፤ ለፍቅር እና ለሰላም ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። እንደ አንድ #ዜጋ ከራሳቸው የሚጠበቀውን በዚህ እድሜያቸው አድርገዋል። የህሊና ተወቃሽ ከመሆንም ድነዋል። ሁሌም ለሰው ልጅ ባላቸው ቀና አመለካከት ስናከብራቸው እና ስናወድሳቸው እንኖራለን።

የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
.
.
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"

#Jimma #Wollo #Haramaya #DebreBrihan #Mekelle #Woldia #ArbaMinch #Hawassa #WolitaSodo #Wachamo #Wolkite

የቲክቫህ ቤተሰቦች ትውስታ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WolitaSodo

በደቡብ ከልል የዎላይታ ሶዶ ከተማ ሴቶች «የዎላይታ ህዝብ በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ ይሰጠው» ሲሉ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። ወጣት ሴቶችና እናቶችጥያቄአቸውን ያቀረቡት ዛሬ ከማለዳው አንስቶ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመጓዝ ነው። በወቅቱም ሴቶቹ «የሪፈረንደሙ ቀን በአስቸኳይ ይገለጽልን!!» ፣ «ለሰላማዊ የህዝብ ትግል ክብር ይሰጠው!!» የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። የሰልፉ ዓላማ ህዝቡ ከዓመት በፊት በክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ የደቡብ ክልል ምክር ቤትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት በአፋጣኝ ገቢራዊ እንዲያደርጉ ለማሳሰብ ያለመ መሆኑን ከሰልፉ አሰተባባሪዎች አንዷ ወይዘሪት በረከት ቶማስ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia