TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNGA

በአሜሪካ አነሳሽነት 193 አባል ሀገራት ላሉት የተመድ ጠቅላለ ጉባኤ የቀረበው ሩስያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት የማገድ የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ዛሬ ፀድቋል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከ193 አባልት 93 ሀገራት የደገፉት ሲሆን 58 ሀገራት ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፤ 24 ሀገራት ደግሞ ተቃውመዋል።

በዚህም በአብላጫ ድምጽ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ታግዳለች።

የውሳኔ ሃሳቡ ለጉባኤው የቀረበው ሩሲያ ጦሯ ዩክሬን ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ግፍ ፈጽሟል በሚል ነው።

የውሳኔ ሃሳቡን አሜሪካ፣ ዩኬ፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ ፣ጀርመን፣ ፖላንድ ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ፖርቹጋል፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ...ሌሎችም በርካታ ሀገራት ደግፈዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሴኔጋል፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ደ/አፍሪካ፣ ፓኪስታን፣ ኩዌት፣ ኳታር፣ ኡጋንዳን ጨምሮ 58 ሀገራት በድምፀ ተአቅቦ አልፈዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ ጎረቤታችን ኤርትራ፣ አልጄሪያ ፣ ቡሩንዲ፣ ቻይና፣ ጋቦን፣ ኢራን፣ ሶሪያ ዝምባብዌ...ሌሎችም ሀገራት ተቃውመዋል።

እንደ ጎረቤታችን ሱማሊያ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ሞሪታኒያ፣ የመሳሰሉ ሀገራት ጭራሽ ድምፅ አልሰጡም።

ዛሬ ሩስያ ከተመድ ሰብዓዊ መብት ም/ቤት ትታገድ ተብሎ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተቃውማ ድምፅ የሰጠችው ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ዙሪያ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ " ሩስያ ዩክሬንን ወራለች ወታደሮቿንም ታስወጣ " በሚል በቀረበ የውሣኔ ሃሳብ ላይ ሙሉ በሙሉ ድምፅ ሳትሰጥ ወንበሯን ባዶ አድርጋ መውጣቷ ይታወሳል። በወቅቱ ውሳኔው " በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ ነው " መባሉ አይዘነጋም።

ሩስያ የዛሬውን የተመድ ጉባኤ ውሳኔ " ህገወጥ " ብላዋለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU2022Summit ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር አፍሪካ በተመድ ፀጥታ ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚሠራበት ጊዜ መሆኑን ገለፁ። ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " አሁን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሻሻልበት እና አፍሪካም በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚሠራበት ጊዜ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ…
#UNGA  

አሜሪካ የተመድ የፀጥታ ም/ቤት ሁሉን አካታች እንዲሆን ለማድረግ #ሪፎርም እንዲደረግበት ጥሪ አቀረበች።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 77ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ፦
- #የአፍሪካ
- ላቲን አሜሪካ
- ካሪቢያን ሀገራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ለዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት የተሻለ ብቃት እንዲኖረውና ሁሉንም አካታች እንዲሆን ለማድረግ ሪፎርም እንዲደረግበትም ባይደን ጥሪ አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ አሁን ላይ 5 ቋሚ እና 10 ተለዋዋጭ በድምሩ 15 መቀመጫዎቸ ያሉት ሲሆን ይህ የመቀመጫ ቁጥር እንዲጨምር ጠይቀዋል።

በአፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካና ካሪቢያን ውስጥ የሚገኙ ሀገራት በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲያገኙ የጠየቁት ባይደን አሜሪካ ይህንን አቋም ለረጅም ጊዜ ስትደግፍ ቆይታለች ብለዋል።

በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ያላቸው ሀገራት በእነሱ ላይ ወይም በአጋሮቻቸው ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመሻር መብት አላቸው።

ባይደን አሜሪካን ጨምሮ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ያላቸው ሀገራት ምክር ቤቱ ተዓማኒነት ያለውና ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥል ከአቅም በላይ ከሆኑ ያልተለመዱ ሁኔታዎች ውጪ ድምጽን በድምጽ መሻር መብታቸውን ከመጠቀም እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

አፍሪካ በፀጥታው ም/ ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ለማስቻል የተለያዩ ዘመቻዎች ሲካሄዱ እንደነበር ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከዚህ ቀደም ይህንን የአፍሪካ ሀገራት በተመድ የጸጥታው ጥበቃ ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ማግኘት አለባት የሚለውን ሃሳብ መቀላቀላቸውን ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#UNGA

የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት #በአፍሪካ_ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

አቶ ደመቀ ፤ ይህንን የገለፁት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 77ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት በሚደረግ የሰላም ድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ ነው ያሉ ሲሆን " ከአፍሪካ ሕብረት ውጭ የሚደረግ ሌላ አካሄድ ተቀባይነት አይኖረውም። " ሲሉ ተናገረዋል።

በሌላ በኩል በንግግራቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ #በአፍሪካ_ህብረት ማዕቀፍ ስር በሚደረግ የሶስትዮሽ ድርድር ጉልህ ተፅዕኖ በማያደርስ እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ልዩነቶችን ለመፍታት አሁንም ፅኑ አቋም አላት ሲሉ ለጉባኤው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በንግግራቸው አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጠይቀዋል።

" እኛ አፍሪካውያን ይህ ጥያቄያችን ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ይህን ጥያቄ መጠየቃችንን እንቀጥላለን። " ብለዋል።

ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው ፤ የሚሰጠውም ጭምር በፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ተገቢው ውክልና ሲኖራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ምሽት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ያሰሙት ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል (40 MB)።

@tikvahethiopia