TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#China #Tibet

ለሊቱን እና ጥዋት ላይ በዓለም በተለያዩ ሀገራት የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።

ከነዚህ ውስጥ እጅግ የከፋው እና የ53 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ በቻይና ፤ ቲቤት ግዛት ደርሷል።

የቻይና የመሬት መንቀጥቀጥ ኔትዎርክ ሴንተር በሬክተር ስኬል 6.8 የተመዘገበ ነው ብሏል።

የአሜሪካው ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ግን የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 7.1 የተመዘገበ ነው ሲል አመልክቷል።

በሬክተር ስኬል 6.8 ሆነ ከዛም በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እጅግ ጠንካራና አደገኛ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ሊያደርስ የሚችል ነው።

በቲቤት 6 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከፍተኛ 7.1 ነው።

በመሬት መንቀጥቀጡ ህንጻዎች ፣ መኖሪያ ቤቶች ተደርምሰዋል።

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የቻይና ሚዲያዎችን ዋቢ በማድረግ በትንሹ 53 ሰዎች እንደሞቱ ነገር ግን ከፍርስራሽ ስር ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የነፍስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተዋል።

አደጋው ተራራማ በሆኑ የገጠራማ ክፍሎች የደረሰ ሲሆን ዋና ወደሚባሉ ከተሞች እንኳን አልተጠጋም።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በሰሜን ህንድ እና በኔፓል ዋና ከተማ ካታህማዱ ሌሎችም ቦታዎች በእጅጉ ተሰምቷል።

ባለስልጣናት ዜጎቻቸው እንዲረጋጉ እና ቀጣይ ለሚመጣው ሾክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።

ስፍራው በተደጋጋሚ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስተናግድ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ቅፅበታዊ ፣ ለመገመት እና ለመተንበይ የሚያስቸግር የት ቦታ እንደሆነ እንጂ መቼ እንደሚፈጠር የማይታወቅ በመሆኑ ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ ንቁ ሆኖ መጠበቅ ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰባሰበ ሲሆን ቪድዮዎቹና ፎቶዎቹን ከቲቤት እና ኔፓል የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነው የወሰደው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብን ? የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ያንብቡ :
https://t.iss.one/tikvahethiopia/93267?single

@tikvahethiopia