TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara #Oromia

ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ "የታሰበው በጸጥታ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ከክልላችን ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሦ የማቋቋም ሥራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ "በጸጥታ ምክንያት ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ አብይ ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ መሪ ዕቅዱን ያወጣል" ሲሉ አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸው፣ "ሁለታችን ተቀናጅተን ለመስራት የሚቀጥለው ሰኞ ቀጠሮ ይዘናል። በዛ መሰረት ታይም ቴብሉን እናስቀምጣለን  መቼ ይመለሱ? መቼ ወደዛ እናጓጉዝ? የሚለው በቅዳችን ነው የሚመለሰው" ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነትም በሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ_ወረዳ ከአሥር በላይ ቀበሌዎች፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ታጣቂ ቡድኑ በንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹ፣ ይህ በእንዲህ እንያለ ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቧል።

አቶ ወንድወሰን ለዚሁ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን  መገድ ሁለታችንም አንሰራም" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሰሜን ሸዋ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር ወጣ ገባ የሚል ነው እናተም እደምታውቁት አማራ ክልልም የጸጥታ ችግር አለ። ይህን በዘላቂ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን ነው የምናስበው፣። ሆሮ ጉድሩ ያለውም ቢሆን አሸባሪው ሸኔ  ወጣ ገባ እያለ ችግር ሊፈጥር ይችላል " ብለው፣ በቅድሚያ የጸጥታውን ችግር የምረጋግጥ ሥር እንደሚከናወን አስረድተዋል።

አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " የጸጥታው ችግር በተረጋገጠባቸው አካባቢዎች የማስፈሩም መልሶ የማቋቋሙም ሥራ ይሰራል። የጸጥታ ችግር ያልተረጋገጠበት አካባቢዎች ደግሞ እያረጋገጥን ነው መልሰን የምናቋቁመው፣ ዛሬ መልሰን ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ በተሞላበት አኳኋን ነው የሚሰራው " ሲሉ ተናግረዋል።

የሁለቱም ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ኦሮሚያ ክልል ከመመለስ በፊት ይህን ሥራ ለማስኬድ የተዋቀረው አብይ ኮሚቴ መረጃዎችን ያጠራል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-27

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara #Oromia ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።…
#Amahra #Oromia

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ወደቄያቸው ለመመለስ ከሰሞኑን በክልሎቹ መካከል የተደረሰበትን የመግባባት ስምምነት በተመለከተ ለሁለቱም ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮዎች ተከታዮችን ጥያቄዎች አቅርቧል።

👉 ከሞት ሸሽተው ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመመልስ ፈቃደኛ ናቸው ? ይህንን ማወቅ ተችሏል ወይ ?

👉 በመንግሥት እና በታጣቂ ቡድኑ / መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት/ መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው ድርድር መቅደም አልነበረበትም ወይ ?


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ለእነዚህ ጥያቄዎች የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን አሰፋ ፤ ሥራው በሂድት የሚረጋገጥ እንደሆነ፣ ተፈናቃዮቹ ለመመለስ ፈቃደኛ እንደሚሆኑ፣ ድርድሩ የበላይ አካላትን እንደሚመለከት መልሰዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " ከቄያቸው፣ ከንብረቱ ተፈናቅሎ ያለ ሰው ዳግም ወደቄየው መመለስ ይፈልጋል የሚል እምነት አለኝ። ተቸግሮ እንጅ ፈልጎ የመፅዋች እጅ ለመጥበቅ የሚፈልግ ይኖራል ብለን አናስብም " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

#በተጨማሪ ፦ ለአማራ ክልል ኮሚኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንደሰን አሰፋ አሁንም ድረስ በንጹሐን ላይ ግድያ እየተፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች በሚገልፁበት ወቅት ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቦ ፤ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን መንገድ ሁለታችንም አንሰራም " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ መሆኑን ያስረዳል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው…
#Oromia

ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ በመንግሥትም ሆነ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን) በኩል ይፋዊ መግለጫ ሆነ ማብራሪያ ባይሰጥም በታንዛኒያ፣ ዳሬሰላም ውስጥ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር መጀመሩን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለፁት ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ነው።

የመንግሥት የተደራዳሪ ቡድን የሚመራው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ በነበሩት ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ሲሆን በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል ደግሞ በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ነው።

ጃል መሮ ከወለጋ ጫካ በኢጋድ፣ በአሜሪካ፣ በኖርዌይ መንግሥታት አስተባባሪነት ነው በአውሮፕላን ወደ #ኬንያ ከዛም ታንዛኒያ እንዲገቡ የተደረጉት።

ከጃል መሮ በተጨማሪ የደቡብ ኦሮሚያ አዛዡ ገመቹ ረጋሳ (ጃል ገመቹ አቦዬ) ከነበሩበት ቦረና አካባቢ በኬንያ አድርገው ወደ ዳሬሰላም እንዲገቡ መደረጉን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል።

ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እንዲሳካ ኢጋድ፣ አማሪካ፣ ኖርዌይ፣ ኬንያ ድጋፍ እና የማመቻቸት ስራን እየሰሩ ነው ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መሪዎች ከመንግሥት ጋር ፊት ለፊት መገናኘታቸው ለሰላም ድርድሩ ተስፋ እንደሰጠው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ያለ ውጤት ተበትኗል " የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን) ጋር በሁለት ዙር ሲካሄድ የነበረው ንግግር ያለ ውጤት መቋጨቱን አሳውቋል። (የመግለጫው ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል) @Tikvahethiopia
#OROMIA

" ' መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ ' የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት አልቻለም " - የኢፌዴሪ መንግሥት

የፌዴራል መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ ከሚጠራው እና በአሸባሪ ድርጅትነት ከፈረጀው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሲካሄድ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት መጠናቀቁን እና መበተኑን አሳውቋል።

ይህ ያሳወቀው ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው።

በመግለጫው ምን አለ ?

በታንዛንያ ዛንዚባር ከወራት በፊት ውይይት ተካሂዶ ሳይቋጭ መቅረቱ አስታውሷል።

በዚሁ ውይይት ወቅት ከ60 ዓመታት በፊት የኦሮሞም የሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ሁሉ ጥያቄዎች የነበሩና ተመልሰው ያደሩ ጥያቄዎችን አንሥቷል ብሏል።

ከለውጥ በኋላ በሥራ ላይ የዋሉ ጉዳዮችን ከማነብነብ ውጭ የሚቆጠርና የሚቋጠር አጀንዳ ማምጣት ስላልቻለ ተንጠልጥሎ እንዲቆይ መደረጉን አመልክቷል።

ባለፉት 2 ሳምንታት ደግሞ ሁለተኛ ዙር ውይይት ታንዛንያ ዳሬ ሰላም ላይ ሲካሄድ መቆየቱን ገልጿል።

በዚህኛው ዙርም ቡድኑ " መንግሥት አዝሎ መንግሥት ያድርገኝ " የሚል አጉራ ዘለልነት ያለፈ የድርደር ነጥብ ማምጣት አልቻለም ብሏል።

መንግሥት በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት መሞከሩን አመልክቷል።

ነገር ግን ሸኔ / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት OLF-OLA/ በሰላም ጊዜ እንዴት መኖር እንዳለበት ለማሰብ ቸግሮት ታይቷል፤ በዜጎች ደምና እንግልት መነገዱን መርጧል ሲል ገልጿል።

በመሆኑንም ውይይቱ በዛሬው ዕለት ያለ ውጤት ተበትኗል ሲል አሳውቋል።

መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሔ ያለው አቋም አሁንም እንደተጠበቀ እንደሆነ ገልጾ ሕግና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማስከበር ተልዕኮውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በድርድሩ ላይ ተካፋይ ከነበሩት መካከል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ) ምን አሉ ?

- ድርድሩ ካለስምምነት በመጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ማዘኑን ገልጸዋል።

- መንግሥት ጦርነት ቆሞ በዚህ ሳቢያ ሲደርስ የቆየው ጉዳትና ውድመት እንዲቆም ጽኑ ፍላጎት እንደነበረው ገልጸው በሌላኛው ወገን ግትር ፍላጎት ከስምምነት ሳይደረስ መቅረቱን አመልክተዋል።

- ሌላኛው ወገን / የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት OLF-OLA ተጨባጭ ሁኔታን መሠረት ያላደረገ ፍላጎቶችን በማቅረቡ እና አደናቃፊ አካሄድን በመከተሉ ምክንያት ንግግሩ ከስኬት ሳይደርስ ለመቋጨቱ ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል።

- የኢትዮጵያ መንግሥት የሠላም ስምምነቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እና ሕገ መንግሥትን ባከበረ ሁኔታ ከስምምነት እንዲደረስ ጽኑ ፍላጎትን ይዞ ከስምምነት ለመድረስ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ጥረት ማድረጉን ነገር ግን ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በድርድሩ ስምምነት ላይ እንዳይደረስ ያደረጉ ጉዳዮች የትኞቹ እንደሆኑ በዝርዝር ይፋ አላደረጉም።

በሌላ በኩል ፤ የድርድሩን ያለውጤት መጠናቀቅ በተመለከተ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLF-OLA) እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የታጣቂ ቡድኑ አመራሮች የሆኑት ጃል መሮ (ከወለጋ ጫካ) እና ጃል ገመቹ አቦዬ (ከቦረና አካባቢ) በኢጋድ፣ በአሜሪካ፣ በኖርዌይ መንግሥታት አስተባባሪነት በአውሮፕላን ወደ #ኬንያ ከዛም ታንዛኒያ፤ ዳሬ ሰላም እንዲገቡ ተደርገው ድርድሩ ላይ ሲካፈሉ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OROMIA #Peace

" . . . እርቁ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

አቶ ጃዋር መሀመድ የኢፌዴሪ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ያደረጉት የሁለተኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት ከተበተነ በኃላ ድርድሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ምን አሉ ?

- መንግስትንና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (WBO-OLA) ለማስታረቅ የተደረገው 2ኛው ዙር ሙከራ አለመሳካቱ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ሀዘን የፈጠረ ነው።

- በሕዝቡ በኩል ቢያንስ ሁለቱም ወገኖች በዚህ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ ተደርጎ ነበር። በተለይ የጦር አዛዦች ከጦር ሜዳ ለውይይት መምጣታቸው እርቀ ሰላሙን ያሳካል የሚል ተስፋ ፈጥሮ ነበር።

- ድርድሩ አለመሳካት እንደ ትልቅ ውድቀት ሲቀርብ እናያለን ነገር ግን ውይይቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ርቀት ተጉዟል። እርቅ ከማያስፈልግበት ወይም ከማይቻልበት ደረጃ ተነስተን የሁለቱም ወገን አመራሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው መወያየት ደረጃ ደርሰናል።

- ይህ እርቅ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም። ተስፋ ልንቆርጥም አንችልም። ሌላ መፍትሄ የለንምና። ስለዚህ የሰላም ድርድሩ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን።

🕊አቶ ጃዋር መሀመድ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ላይ ከተሳተፉት አካላት እና ከተለያዩ ምንጮች ተረዳሁት ያሉትንና ለቀጣይ ዙር የሰላም ድርድር ያግዛሉ ያሏቸውን ሃሳባችን በዝርዝር አቅርበዋል።

➜ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ሁለቱም ወገኖች በእውነት #እርቅ/#ሰላም ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ።

በዚህ የተነሳ ሁለቱም ወገኖች ልክ እንደ ህዝቡ ይህ ምዕራፍ በእርቅ ስምምነቱ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ (expectation) ይዘው ነበር የቀረቡት።

ሁሉም ተሳታፊዎች (WBO / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፣ መንግስት እና አሸማጋዮች) በሰላም፣ በእርቅ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ ይዘው ስለሄዱ ግባቸው ላይ ባለመድረሳቸው የመናደድ ስሜት ውስጥ ገብተዋል። በዚህ ምክንያት ለቀጣዩ የሰላም ውይይት በር ከመክፈታቸው በፊት ተለያይተዋል።

➜ ሁለቱም ወገኖች በቅን ልቦና ለመታረቅ ቢሄዱም፣ አንዱ ከአንዱ የሚፈልገውን (demands/concessions) ለመስጠት እና ለመቀበል ሙሉ በሙሉ የተዘጋጁ አይመስሉም።

በመጀመሪያው ዙር እርስ በርሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ተረድተው ተለያይተዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ አንዳቸው ለሌላው መስጠት የማይችሉትን ያወቁ ይመስለኛል።

አሁንም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኝነት ካላቸው፣ ቀጣዩ እርምጃ ሁለቱም ወገኖች ጥያቄዎቻቸውን ለማስተካከል (modifying demands) መዘጋጀት አለባቸው። ይህ ማለት እንዱ መቀበል የማይችላቸው ነገሮች ላይ በመግፋት መጋጨት መተው አለባቸው።

በሰላም ድርድር ውስጥ የሚፈልጉትን እና ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማግኘት አይቻልም። ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማጣትም አይቻልም። ሁለቱም ወገኖች ወደ መካከለኛው አቋም መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

➜ የሰላም ድርድሩ ዋነኛው #እንቅፋት እየሆነ ያለው ዋና ምክንያት አንዱ ከአንዱ የሚፈልገው ነገር ላይ ተራርቀው ነው ብዬ አላስብም። ትልቁ እንቅፋት #አለመተማመን ነው። በሁለቱ ወገኖች በታሪክ ካለው ግንኙነት እና ከአገራችን የፖለቲካ ባህል አንፃር አለመተማመናቸው ይጠበቃል። የውጪው አካል ያስፈለገበትም ምክንያት ይሄ ችግር ስለተረዳ ነው። እነዚህ አስታራቂዎች የእርቅ ስምምነት ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን የስምምነቱ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህንን አሻሚ የሆነ ችግር ለማሻሻል ይጠቅማል።

➜ ከውስጥ ከውጭ " እርቅ ሊመጣ ነው " ብለው እያዘኑ የነበሩት ወገኖች አሁን በመፍረሱ በደስታ እየፈነደቁ ነው። ሌላ ዙር ድርድር እንዳይደረግም እያሴሩ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) እና የመንግስት አመራሮች አሁንም ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል አቋም ካላቸው እነዚህ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ሁሉንም ክፍተቶች መዝጋት አለባቸው። በተጨማሪም የሚቀጥለውን ዙር እድሎች ከሚያጠብ ወይም ከሚያርቁ ድርጊቶች እና ቃላት መቆጠብ አለባቸው። ይህም የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የመስክ ውጊያን አለማባባስን ያካትታል።

➜ እኔ እስከተረዳሁት ድረስ ከ2ቱም ወገን ደጋፊዎች በኩል የነበረው የ " #ምታ - #ስበር - #አጥፋ " ዘመቻ ባለፉት አመታት በጣም መቀነሱን ነው። የእርቅ ሀሳብ መደገፍ እና ሰላም እንዲወርድ ያላቸው ምኞትም ከየትኛውም ጊዜ በላይ እያደገ መጥቷል።

➜ አሁንም የሁለተኛው ዙር ሙከራ ስላልተሳካ እርስ በርስ ጣት መቀሳሰር እና መደማማት ምንም ፋይዳ እንደሌለው መረዳት ያስፈልጋል። የሚጠቅመው የሚደግፉትን ወገኖች ወደ ድርድሩ እንዲመለሱ እና የሚጠበቅባቸውን እንዲሰጡ ማበረታታት እና ጫና ማድረግ ነው።

➜ በመጨረሻም ፤ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ይሄ የሰላም ድርድር የጦር ሜዳ ውጤቶች አይደለም።

ሁለት የሚዋጉ ወገኖች ለእርቅ ድርድር የሚቀመጡት በሁለት ሁኔታዎች ውስጥ ነው።

የመጀመሪያው ፦ በጦር ሜዳ ላይ አንደኛው የበለጠ የበላይነት አግኝቶ ወደ ድል ሲቃረብ እና ሌላኛው ወገን ሙሉ በሙሉ ከመሸነፉ በፊት ለመታረቅ ሲወስን ነው።

ሁለተኛው ፦ ከረዥም ጊዜ ጦርነት በኋላ ሁለቱም ወገኖች መሸናነፍ ካልቻሉ ነው። በWBO-OLA እና በመንግስት መካከል ያለው ጦርነት የመሸናነፍ ወይም የመድከም ደረጃ ላይ አልደረሰም። በአጭር ጊዜ ውስጥም እዚህ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም። ይህ ውይይት የመጣው በህዝብ እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ግፊት ነው።

በተለይም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን ያሳየው ትኩረት ያልተጠበቀ እና ትልቅ እድል ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት በፍጥነት እየተቀየረ ነው። ስለዚህ ፤ ጉዳያችን ትኩረት ባገኘበት በዚህ ወቅት በፍጥነትና በብልሃት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን እድል መጠቀም ካልቻልንና የሚባክን ከሆነ ለረጅም ጊዜ እንቆጫለን።

#JawarMohammed

Via https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

#TikvahEthiopiaAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
#Oromia

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትን በ20 በመቶ ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወንኩ ነው አለ።

ይህን ያለው የክልሉ የትምህርት ጥራት  ሽግግር የመጀመሪያው ጉባኤ በአዳማ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።

እንደ ቢሮው መረጃ ፦

- ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱት የክልሉ ተማሪዎች 1.8 በመቶ ብቻ ናቸው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡት።

- የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተኑት 518 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- የተመዘገበው የ12ኛ ክፍል ውጤት የትምህርት ጥራት ችግር እጅጉን አሳሳቢ መሆኑን ማሳያ ነው ብሏል። በዘንድሮው ፈተና ውጤቱን በ20 በመቶ ለማሻሻል እየተሰራ ነው ሲል አሳውቋል።

- የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 40 በመቶ ብቻ ወደ ዘጠነኛ ክፍል አልፈዋል።

- በክልሉ የ8ኛ ክፍል ካስፈተኑት 9 ሺህ 585 ትምህርት ቤቶች መካከል 971 የሚሆኑት አንድም ተማሪ አላሳለፉም።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመለየት ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።

በዚህ ጥናት መሰረት ፦

* 47 በመቶ የሚሆኑት መምህራን የተሰጣቸው የትምህርት ክፍለ ጊዜ በአግባቡ ያለመጠቀማቸው አንዱ ችግር መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።

* በትምህርት ዘርፉ የአመራር ሰጪነት ብቃት ማነስና የፖለቲካ አመራር አባላቱ ለዘርፉ ትኩረት ማጣት እንዲሁም የሱፐርቫይዘሮች ድጋፍና ክትትል ማነስ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው ሲል ገልጿል።

ክልሉ የትምህርት ጥራት ችግሮቹን ለመፍታት 15 ሺህ 520 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ከመገንባት ባለፈ ከ140 በላይ የሁለተኛ፣ ልዩና አዳሪ ትምህርት ቤቶች መገንባቱን ቢሮ አሳውቋል።

በተጨማሪ ብቁ መምህራን ለማፍራትና የመማር ማስተማር ስነ ዘዴን ለማሻሻል የሙያ ምዘና፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ የአይሲቲ ልማትና የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል ላይም እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

በዘንድሮው የ6ኛ፣ የ8ኛና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እየተሰራ ነው ብሏል።

🔵 በኦሮሚያ ክልል ከ11 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ አሉ።

#ENA

@tikvahethiopia
#Oromia

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ሰላማዊ ዜጎችን ያልለየ ግድያ በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ይፈጸማል ሲል ከሷል።

በመግለጫው ምን አለ ?

- በኦሮሚያ ተደጋጋሚ ግድያ እና የጅምላ እስሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሳያቋርጥ ይፈጸማል።

-  ህዳር 30 እና ታኅሣሥ 01 ቀን 2016 ዓ.ም. በአቡና ግንደበረት እርጃጆ፣ ጫፌ ኤረርና ፊኖ ቀበሌያት 8 ንጹሃን ዜጎች በጠራራ ጸሃይ ተገድለው ሁለት ሰዎች ቆስለዋል።

-  በቄሌም ወለጋ ዞን ጊዳሚ  ውስጥ ጸሎት ላይ እያሉ ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንዲወጡ ተደርገው የተገደሉ 9 አማኞች በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ነው።

- ከቀናት በፊት በአጋምሳ "ቆርቆቤ' በሚባል ቦታ ላይ መንግስት በስልጣን ላይ እያለ የፋኖ ታጣቂዎች ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል። የአገምሳ ወጣቶች እህል ለመሰብሰብ በሲኖትራክ መኪና ወደ ምእራብ ጎጃም ሲጓዙ በተፈፀመው ጥቃት ከ13 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

- በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ሲርካ ወረዳ በሚገኙ መንደሮች በዋጂ ራፋሳ፣ ቢዱ ባላ፣ ሄላ አመጃ፣ ሄላ ጠሬታ፣ ገለቤ አማጃ፣ ማካራራ፣ ሶጂዪ ሳዲ፣ ጋላቤ ሁሉል እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመክፈት ህፃናትን ጨምሮ ከ50 በላይ  ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- የመንግስት ወታደሮች ህዳር 15 በደምቢ ዶሎ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት የሰዎችን ህይወት ቀጥፈዋል።

- ህዳር 13 ቀን 2016 በቡኖ በደሌ ዞን ጨዋቃ ወረዳ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ተማሪዎችን ጨምሮ 52 ሰዎች ተገድለዋል።

ለኦነግ ፓርቲ መግለጫ የመንግስት ምላሽ ምንድነው ?

ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ፦

* መንግስት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚወሰድው እርምጃ አይኖርም።

* በንጹሃን ዜጎች ላይ ርምጃ የሚወስደው አሸባሪው የሸኔ ቡድን ነው። በቅርቡ ሽርካ ወረዳ በርካታ ንጹሐንን የቀጠፈውን አሰቃቂ ጥቃት የፈፀመው ይኸው ቡድን ነው። ከግድያ ባለፈ በአከባቢው የነዋሪዎችን ቤት አቃጥሏል።

* ንጹሃን ዜጎችን ከጥቃት ለመጠበቅና የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚረዳ ወታደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።

* እርምጃዎቹ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠሩ ብቻ ናቸው። ለአብነትም በቡኖ በደሌ ወረዳ ጨዋቃ ወረዳ የተወሰደው ሸማቂውን ቡድን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል። እርምጃው ታጣቂ ቡድኑ ለጥቃት ሲዘጋጅ የተወሰደ ነው።

* ለአሸባሪ ቡድን የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ወንጀል በመሆኑ ድጋፍ የሚሆኑት ሴሎቹ ላይ እርምጃ ይወሰዳል እንጂ ንጹሐንን መንግስት አይገድልም።

* በሺ የሚቆጠሩ ያሏቸው የታጣቂ ቡድኑ አባላት ለመንግስት እጅ ሰጥተው የታሃድሶ ስልጣና እየወሰዱ ነው።

" ለመሆኑ ሰዎች የሚገድሉት በመንግሥት የፀጥታ ኃይል ብቻ ነው ? " በሚል ለኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

አቶ ለሚ ፦

" ለሚፈፀሙ ለሁሉም ግድያዎች መንግስት ኃላፊነት መውሰድ የሚኖርበት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ብቸኛው ተቋም እሱ በመሆኑ ነው።

የታጠቀ ኃይል እኮ መንግስት አልሆነም፡፡ የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግስት ነው። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ባለቤት ዶቼቨለ ሬድዮ እንዲሁም መግለጫው ከኦነግ ማህበራዊ ትስድር ገፅ የተገኘ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#OROMIA

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።

ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።

ኢሰመኮ ፦

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)

ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ #በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦

* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።

* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።

* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Oromia

ዛሬ ሌሊት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ፤ ዱከም ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተጨማሪም 11 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

መረጃው የቢሾፍቱ ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016…
#Oromia

ኢሰመኮ ፦

- ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ #የድሮን_ጥቃት
° በየነ ጢቂ፣
° ጉደታ ፊጤ፣
° ሀብታሙ ንጋቱ፣
° ታዴ መንገሻ፣
° ዳመና ሊካሳ፣
° ዱጋሳ ዋኬኔ፣
° ሕፃን አብዲ ጥላሁን
° ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል።

በተጨማሪም፦
• ስንታየሁ ታከለ፣
• ሽቶ እምሩ፣
• ተሜ ኑጉሴ
• አለሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ #በድሮን_ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- ጥር 9/2016 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ለሌላ_ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ ይወጣል። ይህን ተከትሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በማግስቱ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር ” በማለት 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን #በጥይት_በመምታት ገድሏል። አቶ ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ አስክሬናቸው ወድቆ ተገኝቷል።

- ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ #የአማራ_ታጣቂ_ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ #በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል ፤ 
➡️ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትን አድርሰዋል
➡️ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎችን #አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶው “ ኦነግ ሸኔ ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 15 ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎች #ተገድለዋል
➡️ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን #አግተው_ወስደዋል
➡️ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል
➡️ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።

- መጋቢት 1/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል።

- መጋቢት 16/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ፣ ከባለቤቱ እና #ከ2_ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። 

- መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በዶዶላ ወረዳ በደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ” ) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ውስጥ “ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል።

ለምሳሌ ፦

👉 በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7/ 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል።

👉 መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል።

👉 ሚያዝያ 8/2016 ዓ/ም በደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል ፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል።

👉 በሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።

#Oromia #Ethiopia #EHRC

@tikvahethiopia