TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GondarUniversity

በቃጠሎው በሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም...

በጎንደር ዩንቨርሲቲ (ቴዎድሮስ ካምፓስ) የተማሪዎች የማደሪያ ህንጻ ላይ ዛሬ ምሳ ሰአት ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዩንቨርሲቲው አስታውቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን እንደተናገሩት የእሳት አደጋው የደረሰው የ1ኛ ተማሪዎች የሚገለገሉበት T-35 የተባለው የማደሪያ ህንጻ የመጨረሻ ፎቅ ላይ ነው፡፡ ቃጠሎውን ለመቆጣጠርም የከተማውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች ፈጥነው በመድረስ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውን ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የዩንቨርሰቲው ማህበረሰብ አባላትና ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሉና የከተማው አመራሮች እሳቱን ለመቆጣጠር ያደረገው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በቃጠሎው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የተናገሩት ፕሬዘዳንቱ በንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት ከማድረስ ውጪ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡ የቃጠሎው መንስኤ እስከ አሁን በውል እንዳልታወቀና የከተማው ፖሊስም በስፍራው ተገኝቶ የማጣራት ስራ መጀመሩንም ገልጸዋል፡፡

(ENA)

PHOTO: የቲክቫህ ጎንደር ቤተሰቦች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GondarUniversity

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአፄ ፋሲል እና አፄ ቴዎድሮስ ግቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ የማይማሩ ከሆነ ከነገ 12/03/2012 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ አገልግሎት እንደሚያቋርጥ፤ እንዲሁም በማይማሩ ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳታውቋል። ዩኒቨርሲቲው አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የመማር ማስተማር ስራውን በአግባቡ በማካሄድ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳለም ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GondarUniversity

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ታኅሳስ 14 ቀን 2013 ባደረገው ስብሰባ ለዶ/ር በላይ ተሰማን እና ዶ/ር ውዱ ተመስገንን የሙሉ ኘሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው ወስኗል።

ዩኒቨርሲቲው ኘሮፌሰር በላይ ተሰማ እና ኘሮፌሰር ውዱ ተመስገን ለዚህ ስኬት በመብቃታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#GondarUniversity

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ ኘሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ከ7000 በላይ ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ያስመርቃል።

በነገው ዕለት የሚመረቁት ወንድ 4804፣ ሴት 2489 አጠቃላይ 7293 ተማሪዎች ናቸው።

የዚህ ዓመት ተመራቂዎች በርካታ የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ችግሮችን እና ውጣ ውረዶችን አልፈው ለዚህ የበቁ በመሆናቸው ከሌሎች ጊዚያት ተመራቂዎች ልዩ እንደሚያደርጋቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ገልፀዋል።

የምረቃ መርሃ ግብሩ በዩኒቨርሲቲው ፌስቡክ ገጽ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን በአማራ ቴሌቪዥን ደግሞ ሙሉ ኘሮግራሙ ነገ ማታ ይተላለፋል ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#GondarUniversity

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ ኘሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ከ7000 በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

በ5 ኮሌጆች ስር በሚገኙ በ14 ፕሮግራሞች በመደበኛው መርሃ-ግብር ወንድ-629 ሴት- 503 በድምሩ 1,132 ትምህርታቸውን ከተከታሉት ውስጥ 1077 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

#JinkaUniversity

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመርቋል።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 854 ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

የዛሬዎቹ ተመራቂዎች 501 ወንድ እና 353 ሴት ናቸው።

#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለ12ኛ ዙር ዛሬ ጥር 15 እና ነገ ጥር 16/2013 ዓ/ም በቡሬ እና ዋናው ግቢዎች ያስመርቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት…
#GondarUniversity

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል #በራሳቸው_ገቢ እንዲተዳደሩ ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን አሥራት አፀደወይን (ዶ/ር) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

ለዚህም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደተግባር ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን በሂደት እየቀነሰ የሁለተኛ እና የሦሥተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የውጪ ሀገራት ተማሪዎችን ለመሳብ እየሰራ እንደሚገፅ የገለፁት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በአሁኑ ወቅት 50 ዓለም አቀፍ ተማሪዎች እንዳሉት ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦሥተኛ ዲግሪ እንዲሁም በስፔሻሊቲ እና በሰብ ስፔሻሊቲ መርሃ ግብሮች ከ48 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

Via @tikvahuniversity
#GondarUniversity

ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ #በተለያየ_ጊዜ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ #አንጋፋ የሚባሉ ምሁራን ፤ መምህራንን ፣ ሰራተኞችን ፣ ተመራቂ ተማሪ እና የዩኒቨርሲቲው ታላቅ #ባለውለታ የሆኑ አባትን በሞት ተነጥቋል።

አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እነማንን #በሞት ተነጠቀ ?

🕯አባሆይ አሰፋ ዘለቀ🕯

የመሬት ርስታቸውን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ካበረከቱት 59 አርሷደሮች መካከል አንዱ ነበሩ። በ1963 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ቁጥር መጨመር እና የሚሰጠውም የትምህርት ዓይነት እየሰፋ በመምጣቱ ግቢውን ወደ ማራኪ አካባቢ ማስፋፋት ሲፈልግ አባሆይ አሰፋ ዘለቀ ከሌሎች ልበቀናዎች ጋር በመሆን በማራኪ ከፍተኛ ቦታ አካባቢ የነበራቸውን የመሬት ይዞታ ለማስፋፊያ እንዲሆን በመፍቀድ ትውልድ እንዲቀረጽበት በማድረግ ዘመን ማይሸረው አበርክቶ አድርገዋል፡፡ በ94 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

🕯ፕሮፌሰር ሞገስ ጥሩነህ🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ መምህር ፣ ተመራማሪ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልጋይ ነበሩ።

🕯ዶ/ር ሰለሞን ይርዳው🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ ባልደረባ ነበሩ። ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ በህክምናው ሙያ በመተማ ሆስፒታል አገልግለዋል። ከ1992/93 ዓ.ም ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሙያቸው አገልግለዋል። በማስተማርም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በጤና እክል ህይወታቸው አልፏል።

🕯መምህር ደመቀ ደሱ 🕯

አንጋፋ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህር ነበሩ። በጡረታ እስከተገለሉበት ድረስ ለ40 ዓመታት ገደማ  በማስተማር ሙያ እንዲሁም በትምህርት ክፍል እና በዲን ኃላፊነት አገልግለዋል።

🕯አቶ ፍስሃ ሞሴ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም Nutrition & Dietetics Department ውስጥ የChief laboratory Technical Assistant ባለሙያ ነበሩ። ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄዱበት በደንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ተቀጥፏል።

🕯አቶ አታለል ምስጋናዉ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚዮሎጂ ት/ክፍል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ መምህርና በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ነበሩ። በ31 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

🕯ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ🕯

የኪነህንፃ / #Architecture / ተመራቂ ተማሪ ነበር። የትንሳዔ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር ባሄደበት ከፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል ነበር።

🕯አቶ ሙሉአለም ይትባረክ🕯

በህክምናና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተማሪዎች አገልግሎት ውስጥ የተማሪዎች ምኝታ ቤት አስተባባሪ ነበሩ። በህመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አጠቃላይ 8 አንጋፋ ምሁራን ፣ መምህራን ፣ ሰራተኞች ፣ ተማሪ እንዲሁም የተቋሙን ባለውለታ ታላቅ አባት በሞት ተነጥቋል።

የጤና እክል ፣ ድንገተኛ አደጋ ፣ የመኪና አደጋ የህልፈተ ህይወት መንስኤዎቹ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው ካገኘው መረጃ ተረድቷል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia