TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የወ/ሮ ዳግማዊት ሽኝት⬆️

በቅርቡ የትራንስፓርት ሚንስትር በመሆን ለተሾሙት ወ/ሮ #ዳግማዊት_ሞገስ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ፣ የካቢኔ አባላትና የከንቲባ ፅ/ቤት ሰራተኞች በተገኙበት የሽኝት ስነ ስርዓት ተደርጎላቸዋል።

ምንጭ፦የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ዳግማዊት_ሞገስ 118 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለውን የጣርማ በር- መለያ-ሰፌድ ሜዳ-መለያ- ሞላሌ ወገሬ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ስራ ኘሮጀክት ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አብራሪዎች ሥልጠናን በተመለከተ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣውን ዘገባ «#ሐሰት» ሲል አስተባብሏል። የዩናይትድ ስቴትሱ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በድረ-ገጽ ዘገባው፦ «የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማክስ 8 ምስለ-በረራ (ሲሙሌተር) ነበረው፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ ግን ስልጠናውን አላገኘም» በሚል ርእስ ዘለግ ያለ ጽሑፉን አስነብቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ቅር መሰኘቱን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ዐሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎቹ ቦይንግ 737-8-ማክስን ማብረር ከመጀመራቸው በፊት፤ ቦይንግ-737 NG በሚባለው እና በቦይንግ-737 ማክስ መካከል ያለውን ልዩነት በቦይንግ ምክረ-ሐሳብ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትሱ የፌዴራል የበረራ አስተዳዳር (FAA) ልዩነታቸውን አስመልክቶ ባጸደቀው መሰረት ሥልጠና ማጠናቀቃቸውን ገልጧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፦ የቦይንግ-737-ማክስ ሙሉ ምስለ-በረራ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የMCAS ሥልት ችግርን ምስለ-በረራ ለማድረግ ተደርጎ የተቀናጀ አይደለም ብሏል። የMCAS ሥልት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአደገኛ መልኩ ወደላይ አስግገው መብረር ሲጀምሩ የአውሮፕላኖቹን አፍንጫ በራሱ ጊዜ ወደታች የሚጎትት ስልት ነው። በኢትዮጵያም ኢንዶኔዢያም የተከሰከሱት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የአደጋ መንስኤ አንዳንድ ግልጽ መመሳሰሎች እንደተገኘባቸው የኢትዮጵያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ #ዳግማዊት_ሞገስ በተለይ ለ«ጀርመን ራድዮ» ተናግረዋል። ደብረዘይት/ ቢሾፍቱ አጠገብ ወድቆ የተከሰከሰዉ አዉሮፕላን ሁለቱን ፓይለቶች ጨምሮ አሳፍሯቸዉ የነበሩ 157 ሰዎች በሙሉ አልቀዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia