TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዱራሜ‼️

በደቡብ ክልል በዜጎች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ሞትና መፈናቃል ያሳቆጣቸው #የዱራሜ_ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ መዉጣታቸዉ ተነገረ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ዛሬ በከተማው ስታዲየም በመሰባሰብ መንግሥት የዜጎችን በህይወት የመኖር ህገ መንግሥታዊ መብት ሊያስከብር ይገባል ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ሠልፈኞቹ በቅርቡ ከከፋ ዞን ዴቻ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት የሞት አደጋ የደረሰባቸው ነዋሪዎችን ለማሰብ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዓት ያካሄዱ ሲሆን ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ቤተሰቦችም የገንዘብ ፤ የቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

የሰልፉ አስተባባሪ አቶ #ደሳለኝ_ዳለሎ በሰልፉ ላይ የከተማው ነዋሪዎች በዋናነት ሁለት መሠረታዊ መልዕክቶችን ያስተላለፉበት ነው ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

በደቡብ ክልል #ከፋ_ዞን ዴቻ ወረዳ ታጣቂዎች በሰፈራ መንደር በተሰባሰቡ የከምባታ ማህበረሰብ አባላት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ እንደሚገኙ የከንባታ ጠንባሮ ዞን መስተዳድር ማስታወቁ አይዘነጋም። እስከአሁን በጥቃቱ 32 ሰዎች ሲሞቱ ከ 35 ሺህ በላይ የሚሆኑት መፈናቀላቸው ይታወቃል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia