TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በታጣቂዎቹ የተወሰዱት ሕፃናት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለንም " - አቶ ኡገቱ አዲንግ

#ከደቡብ_ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች 2 ሕፃናት #አፍነው መውሰዳቸውን የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት ቃል ፦

-  ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊትም በሕገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፣ ሕፃናትን አፍነው ወስደዋል፣ ከብቶችን ዘርፈዋል፤ አሁንም ቢሆን ድርጊቱ አልቆመም።

- በተለይ በአኮቦ፣ ዋንቲዋና መኮይ ወረዳዎች ሕፃናትን አፍኖ ለመውሰድ፣ ንብረት ለመዝረፍና በሰዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተስፋፍቷል ፤ ታጣቂዎቹ ባለፈው ሳምንት 3 ሕፃናትን አፍነው የወሰዱት በ3ቱ ወረዳዎች በነበራቸው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ነው።

- በታጣቂዎቹ የተወሰዱት ሕፃናት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለንም። የሰው ልጅ ካልሞተ ይገኛል ብሎ ማሰብ ቢቻልም፣ እስካሁን በተደረገው ሕፃናትን የማስመለስ ሙከራ አንፃር፣ አሁንም ቢሆን ሰሞኑን የተወሰዱት ሕፃናት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በሚደረግ ውይይት ይመለሳሉ የሚል ተስፋ የለም።

- እስካሁን ታፍነው የተወሰዱት ሕፃናትና የተዘረፉ ንብረቶች ለማስመለስ ከዚህ ቀደም የክልሉ መንግስት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ቢያደርግም፣ ውይይቱ ውጤታማ ባለመሆኑ በተጨባጭ የተመለሰ ሕፃንም ሆነ ንብረት የለም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-12-25-2

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia