TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል መቼ ይከበራል ?

የዘንድሮ ኢሬቻ መስከረም 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ/ም ይከበራል።

የአባገዳዎች ህብረት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም መግለጫ ፥ መስከረም 25 ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በማግስቱ መስከረም 26 ኢሬቻ ሆረ አርሰዴ እንደሚከበር ገልጿል።

#ኢሬቻ2017

@tikvahethiopia
#ኢሬቻ2017

የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' እና ' ሆራ አርሰዲ ' በዓልን ለሚያከብሩ ታዳሚዎች ትራንስፖርት መዘጋጀቱን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል።

በአዲስ አበባ በ5ቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶብሶች፣ 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶብሶች መዘጋጀታቸውን ተገልጿል።

ቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል 150 የሚሆኑ ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቢሶች ዝግጁ እንዲሆኑ መደረጉን ተመላክቷል።

በአጠቃላይ ታክሲዎችን ሳይጨምር 1 ሺህ 457 ተሸከርካሪዎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል።

#AddisAbaba #Bishoftu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ የ2017 ኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል ዋዜማ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ #ኢሬቻ2017 #Irreecha2017

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ለጋራ ደህንነት ፍተሻዎች ስለሚኖሩ ትብብር አድርጉ " - ፖሊስ

በአዲስ አበባ በተለይም የኢሬቻ ' ሆራ ፊንፊኔ ' በዓል በሚከበርበት አካባቢ እና መስመሮች ላይ ፍተሻ አለ።

በዓሉን ለመታደም ወደ ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

#ኢሬቻ2017 #Irreecha2017

@tikvahethiopia