TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መከላከያ ሰራዊት🔝

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር #ከዛሬ ጀምሮ እንደሚሠማራም ተገልጧል፡፡

በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተ የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጎንደር ላይ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል #አለምነው_አየነ እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘላለም_ልጃለም ናቸው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር ከዛሬ የካቲት10/2011 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሠማራም በመግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

በፀጥታ ኃይሉ አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ የተከለከለከሉ ተግባራትም በመግለጫው ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከጎንደር-መተማ መስመር ከመንገድ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፤ በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ #ክልከላ ተደርጓል፡፡ በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሣሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ እንደማይችልም ታውቋል፡፡

ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል እርምጃ እንደሚወሰድበትና ‹‹ሰላም ለማስከበር›› በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፈቃድ ውጭ መሣሪያ ይዞ #እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ተላልፏል፡፡

በመግለጫው የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia