TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት #ሀዋሳ #ክልከላ

በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ ባለ ሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና የሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር #ተከለከለ

ሰሞኑን በሀዋሳ ከመዝናኛ መልስ እየደረሰ ያለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሲባል ከምሽቱ 3:00 በኃላ ባለሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪው ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦
°  ምክንያት ?
°  ክልከላው ለምን አስፈለገ ?
° በማህበረሰቡ የእለት ተእለት ህይወትስ ላይ የሚያሳድረዉ ጫና አይኖርም ? ወይ ስንል ኢንስፔክተሩን ጠይቋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፤ " ሁሉንም ያደረግነው ለማህበረሰቡ ደህንነት ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እየተስተዋለ ነው " ሲሉ ገልጸው ከአደጋዎቹ አብዛኛዉ በባለሦሰት እግር ባጃጅና በባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል የሚደርስ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በዚህ አመት ብቻ በምሽት በሞተር ሳይክል የደረሰዉ አደጋ የሚያስገርም ቁጥር ያለው ነው " ያሉት ኢስፓክተር ተስፋዬ በቁጥር ስንት ? የሚለውን ወደፊት ዳታውን አጠናቅረዉ ለማህበረሰቡ የማሳየት እቅድ እንዳለቸዉ ጠቁመዋል።

ከአደጋዎቹ ውስጥ በአብዛኛው የሚከሰቱት በምሽት መሆኑን ጠቅሰው ፤ " ጠጥቶ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር  ትልቁ ምክኒያት ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም በመንግስት ሞተር ሳይክሎች ሳይቀር ሶስትና ከዚያ በላይ ሆኖ መንቀሳቀስ አደጋ እየፈጠረ ነው ይህን ችግር ለመቀነስ ሲባል #ክልከላው ወጥቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፤ " የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የወንጀል መፈጸሚያ እየሆኑ ነው " ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ " ለአብነት ኮንትራት ተብለዉ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ እና የሌሎችም ወንጀሎች ምንጭ ሆነው ተገኝተዋል " ብለዋል።

" ጥንቃቄ ለራስ በመሆኑ ማህበረሰቡ ለራሱ ሲባል የወጣዉን ክልከላ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ " ሲሉ አሳስበዋል።

" እለት ተእለት የሚከሰተው ዘግናኝ የትራፊክ አደጋ እንዲቆም የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል " ብለዋል።

ክልከላው የሚያበቃበትን ጊዜን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia