TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከባድ ማሳሰቢያ‼️ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የምትማሩ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በፌስቡክ የሚፃፉትን መረጃዎች #እንደወረደ ከመቀበል #ተቆጠቡ። የዚህችን ሀገር #ሰላም መሆን የማይፈልጉ አካላት #በተመቻቸ ቦታ ሆነው ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እየተሯሯጡ እንዳለ በግልፅ ማየት ይቻላል። በፌስቡክ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ መንግስት ተገቢውን እና እጅግ በጣም ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ቻናላችን አጥብቆ ይጠይቃል።

🚫በፌስቡክ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ መልዕክቶችን አጥብቀን እንቃወማለን🚫
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታዳሚውን ያስለቀሰው የብሩክ የሺጥላ ንግግር...

"ከዛሬ ጀምሮ ይህቺ ምደገፍባት ነገር አታስፈልገኝም ለምን መሰላችሁ ሲደክመኝ ሚደግፈኝ #ኢትዮጵያዊ_ወንድም አለኝ፤ ሲርበኝ አይዞህ ብሎ የሚያበላኝ እህትና ወንድም አለኝ፤ እኔ ማውቃት ኢትዮጵያ ይህቺን ነው፤ እኔ #የኖርኩባት ኢትዮጵያ ይህቺ ነች፤ ልጄም ይህንን እውነት እንዲኖረው እፈልጋለሁ፤ #ልጆቻችንም ይሄንን እውነት የሆነ ኢትዮጵያ ኖረው እንዲያልፉ ሁሉንም ነገር #እናመቻችላቸው፤ ችግርን ከመፍጠር ይልቅ ብዙ ችግሮች አሉብን ስለ ችግሮቻችን ካወራን ችግሮቻችን አያልቁም። መሪዎቻችን ደግሞ ገና #በተመቻቸ ሁኔታ ላይ አይደሉም፤ እነሱ ላይ ብዙ ችግር አንፍጠርባቸው፤ እኛ የምንችለውን ችግር እንፍታ እነሱም ደግሞ መፍታት የሚችሉትን ያህል ችግር ይፍቱልን። የሚቀጥለው መሪ የተሻለ ወንበር እንዲያገኝ፤ የተመቻቸ ወንበር እንዲያገኝ፤ እኛንም ከዚህ በተሻለ በደንብ መምራት እንዲችል ሁሉን ነገር እኛ እናመቻችለት።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia