TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #Attention🚨

የትራፊክ አደጋ የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል።

በዚህ ወር ብቻ ፦

- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ተጎድተዋል።

- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ ከኔጌሌ ወደ ዶዶላ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና 'አላንቱ' ላይ ከ " ሲኖትራክ " የጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። ሌሎችም ተጎድተዋል።

- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ፤ ከዋቻ ወደ ቦንጋ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሸከርካሪ እና ከሚዛን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ ተሸከርካሪ በጨና ወረዳ ቦባ በላ ቀበሌ ተጋጭተው 5 ሰዎች ሲሞቱ 13 ሰዎች ተጎድተዋል።

-  በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ወርት በተባለች ቀበሌ እንጨት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ #ሲኖ_ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ   የ6 ወጣቶች ህይወት ወዲያዉ ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል። አደጋዉን የከፋ ያደረገው ሲኖ ትራኩ  ወጣቶችን እንጨት ላይ አሳፍሮ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አደጋው በመድረሱ ነው።

ከላይ በተጠቀሰው እና በይፋ በታወቀው ብቻ 28 ዜጎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። በርካቶች የአካል ጉዳተኛ ሆነው።

እባካችሁ ጥንቃቄ አይለያችሁ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ አሽከርክሩ " - ፖሊስ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ የደረሱት የትራፊክ አደጋዎች የሰው ህይወት ቀጥፈዋል ፣ ከባድ እና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል፣ ንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአንድ ክ/ከተማ፣ በአንድ ቀን፣ በተለያየ ቦታና ሰዓት በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ አጠቃላይ የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ9 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋዎቹ የደረሱት ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ/ም ነው።

የጉዞ መስመሩን ከጎሮ ወደ ኮዬ ፈቼ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-69867 ኢት #ሲኖ_ትራክ ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቡስ ጋር ተጋጭቶ ትኬት ሊቆርጡ ወደ አውቶቡሱ ተጠግተው የነበሩ 3 ሴቶች እንዲሁም በአካባቢው ላይ ጧፍ ስትሸጥ በነበረች ሴት ላይ የሞት አደጋ ያስከተለ ሲሆን የከባድ መኪናው አሽከርካሪም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበታል፡፡

ከተከሰተው ሞት በተጨማሪ በ7 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

በዛው እለት ቡልቡላ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢም አካባቢ በደረሰው አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

የጉዞ አቅጣጫውን ከመድኃኒያለም ወደ ማርያም ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-8660 ኢት #ሲኖ_ትራክ ተሽከርካሪ ከማርያም ወደ ኮዬ ይሄድ ከነበረ ኮድ 3-46737 ኦሮ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭተው የደረሰ አደጋ ነው።

በአንድ ቀን በ7 ሰዎች ላይ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ መድረሱ በእጅጉ አስዛኝ  እንደሆነ የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ በአብዛኛው ለሚከሰቱት የትራፊክ አደጋዎች ዋነኛ ምክንያት ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ የሚደርሱ መሆናቸውን አስገንዝቧል።

አሽከርካሪዎች ከምንጊዜውም በላይ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የአካባቢውን߹ የመንገዱን እና የእግረኛውን የመንገድ አጠቃቀም ሁኔታ በተገቢው በማስተዋል ማሽከርከር እንደሚጠበቅባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር በኋላ ከሚመጣው መፀፀት እንደማያድን በመገንዘብ በጥንቃቄና  በእርጋታ ማሽከርከር እንደሚገባ ፖሊስ ገልጿል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia