TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace #GoE #OLA

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA መካከል ከዚህ ቀደም ታንዛኒያ ላይ ሁለት ጊዜ የሰላም ድርድር ተደርጎ ያለ ስምምነት / ወጤት መበተኑ ይታወሳል።

አሁንም ሌላ #ሶስተኛ_ዙር የሰላም ውይይት/ድርድር ሊኖር የሚችልበት ዕድል መኖሩን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

- የመጀመሪያው ንግግር በጣም ጥሩ ርቀት ሄዶ ነበር ፤ በዚህም ብዙ መካሰስ ቀርቶ ለሚቀጥለው ዙር ለመነጋገር እናመቻች በሚል ነው የተጠናቀቀው።

- ሁለተኛው የሰላም ድርድር መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገን አግባቢዎች ሄደው ከሳምንት በላይ ፈጅተዋል። አዝማሚያው ጥሩ ነበር።  መጨረሻ የማያግባቡ ነጥቦች መጡ። በዚህም ትንሽ የተሻለ ኃይል ያለው ሰው ይምጣ ተብሎ ከመንግሥትም ከነሱም ሄዷል። በዚህም ጊዜ ጥሩ ሂደት ነበር።

- በህገ-መንግስት ጥላ ስር "የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት መቀበል ላይ ፤ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት በምርጫ የመጣ Legitimacy ያለው መሆኑ ላይ መግባባት ተደርሶ ነበር። ወደ ዝርዝር ሲመጣ ግን እነዚህን መግባባቶች የሚሸረሽር ነገር ነው የመጣው።

- ስምምነቱ በመጨረሻ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ደረጃ / ወደ ሰነድ ደረጃ ሲደርስ ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ተነስትዋል።

ምንድናቸው ?

* አንደኛው --- ' #ስልጣን_አካፍሉኝ ' ነው እያንዳንዱን ጠብመንጃ የያዘ፣ ጫካ የገባ ሁሉ ስልጣን ለማግኘት ከሆነ የሚደራደረው ይሄ ለሀገር ሰላም አይሰጥም።

ጫካ እየገቡ ፣ ግጭት የፈጠሩ ፣ ህዝቡን እያበሳሰቡ ከዛ እንነጋገር እያሉ " እሺ " ሲባል ስልጣን አካፍሉኝ የሚባል ነገር ካለ መቼም ስርዓት አይመጣም። ሀገር ሰላም አይሆንም።

ምሳሌ ብንወድስ ፦ ከአማራ፣  ከቤንሻንጉል ጉምዝም ከሌላውም የታጣቁ ኃይሎች ስልጣን አካፍሉኝ ካሉ ስንት የታጠቀ ኃይል ስልጣን ሲካፈል ይኖራል ? ይሄ ኢትዮጵያን ይጎዳል።

እንዲህ አይነት ጥያቄ ነው ይዘው የቀረቡት (OLAን ማለታቸው ነው)።

መንግሥት ስልጣን ላካልፍ ቢልም ፍፁም አይችልም ፤ መብትም የለውም። #ማሳተፍ ግን ይችላል። ሸኔን ጭምር ማሳተፍ ይችላል።

ዋናው መሰረታዊ ልዩነት ይሄ ነው። ስልጣን አካፍሉኝ ስሉም እራሳቸው ፕሮፖዛል አስቀምጠው ፤ እዚህ ላይ ስልጣን ስጡኝ የሚል ነበር።

* ሁለተኛው --- ወደ ' DDR ' አልገባም ነው።

በሰላም ለመታገል ፣ ፓርቲ አቋቁሞ ለመታገል ፣ ወደ ህዝብ ምርጫ ለመቅረብ የገጠር ትጥቅ ትግል ትቶ በሰላም ወደ ህዝብ መመለስ ነው። ለዚህ ደግሞ ትጥቅ መፍታት አለባቸው።

DDR / Disarm, Demobilized , Reintegrate መሆን አለባቸው። ይሄ ዓለም የሚሰራበት ነው። ማንኛውም ግጭት የተፈታውም በዚህ ነው። ይሄን ለመቀበል የመቸገር ነገር ተከስቷል።

ትጥቅ ሳይፈታ ፦
° እንዴት እንደራደራለን?
° እንዴት Demobilize ይሆናሉ?
° እንዴት ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ?

መንግስት በግልፅ DDR ፕሮግራም ውስጥ መግባት አለብን ብሏል። በአንድ ሀገር በፍፁም ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም። ትጥቅ የመያዝ መብት ያለው መንግስት ብቻ ነው።

ይሄንን #መቀበል_ነበረባቸው። በዓለም ላይ ይሄን ሳይቀበሉ ስምምነት የለም። ድርድር ብሎ ነገር የለም።

ንግግሩ ጥሩ ሄዱ ከላይ ባሉት ሁለት ምክንያት ነው መጨረሻ ላይ የቆመው።

- ሶስተኛ ዕድል ይኖራል ? እኔ የሚኖር ይመስለኛል።

- ሁለቱን #ያልተስማማንባቸው_ነጥቦችን በተሳሳተ መንገድ እንዲወስዱ በማድረግ ሌሎች ኃይሎች እጅ አላቸው። OLA ላይ ታዝሎ የሚሄዱ ኃይሎች አሉ። ከሀገር ውስጥም ከሀገ ውጭም አሉ። ባዕዳንም ዜጎችም እነዚህ ኃይሎች OLA በሰከነ መንገድ አይቶ ስምምነቱን እንዳይቀበል አድርገውታል። OLA ሌላ መስማት አልነበረባቸውም፤ ችግር ውስጥ ያሉት እራሳቸው ስለሆኑ እራሳቸው መወሰን ነበረባቸው።

(ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እነዚ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተናገሩም)

- ሌላው ኃይል ጣልቃ ስለገባ በዓለም experience ታይቶ የማይታወቅ ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ መንግሥትን አስቸግረዋል (OLA ማለታቸው ነው)።

- ሶስተኛ ዕድል ሊኖር ይችላል። ሰከን ብለው አስበው አደራዳሪዎች ጭምር የሚያምኑበት የመጨረሻው ወረቀት / ዶክመንት / የቀበል ደረጃ ከደረሱ ሶስተኛ ውይይት ሊኖር ይችላል።

- ምናልባት ሶስተኛ ውይይት እንደሁለተኛው ውይይት ሰፊ ላይሆን ይችላል እስካሁን የተደከመበት ሰነድን መቀበል ላይ ከተደረሰ ሶስተኛው ውይይት ሊኖር ይችላል፤ ሶስተኛው ውይይት የመጨረሻም ይሆናልም ብዬ ገምታለሁ ወደሰላም ለመምጣት ወይም እስከመጨረሻው ሁለተኛ ላለመነጋገር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል።

🕊 የኢጋድ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሳምንታት በፊት ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድርን በተመለከተ ሰጥተው በነበረው መግለጫ ሌላ አዲስ ዙር ውይይት ይጀመራል ብለው #ተስፋ እንደሚያደርጉ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia