TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጉዞ ሉሲ~ለሰላምና ለፍቅር!

‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር መርሀ-ግብር›› ትላንት ምሽት በሚሊኒዬም ተጀምሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ካሰው ‹‹ዘረኝነት፣ መለያዬት፣ ማግለልና ንፉግነት የኛ የኢትዮጵያዊነት ባሕል አይደለም፡፡ ከዛሬ ጀምሮ የነበረንን መተዛዘን፣ #ፍቅርና #አንድነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ለውጥ የሚጀምረው ከራስ ነውና ለለውጥ እዘጋጃለሁ፤ ለለውጥ እንዘጋጅ›› በሚል #የአንድነት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በመርሀ-ግብሩ ከአፋር ክልል ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ሉሲ የአምስት ቀናት ቆይታ እያደረገች ሕዝቡ #በአንድነቱ ዙሪያ እንደሚወያይ የገለጹት ሚኒስትሯ ‹‹ሉሲንና ሌሎች አንድ የሚያደርጉን በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶችን በታላቅ ክብር ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ ፓርላማ አጓጉዘን ወደ አፋር በመሸኘት ይጀመራል›› ነው ያሉት፡፡

ሉሲ የእገሌ የሚባል ሃይማኖት፣ ብሔር፣ አስተሳሰብ ወይም ሌላ #ወካይ_ያልሆነች የሁሉም የሰው ዘር ግንድ መሆኗን የጠቀሱት ሚንስትሯ ‹‹ደግነትና አብሮነት ስላልተለየን በጎ ትሩፋት ሳይሠራ የሚውል #ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ የተራበ ሳያበላ፣ የተጠማ ሳያጠጣ፣ የወደቀ ሳያነሳ፣ የሞተ ሳይቀብር አይውልም፤ ኢትዮጵያዊነትም ይህ ነው›› ብለዋል፡፡ እንኳን እርስ በእርስ ከሌላውም ዓለም ጋርም ኢትዮጵያዊ በሉሲ የተዛመደ መሆኑንና #ዘረኝነት የኢትዮጵያዊነት ባሕል አለመሆኑን ነው ዶክተር ሂሩት ያስገነዘቡት፡፡

በመርሀ-ግብሩ መክፈቻ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ አንጋፋና ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia