አሳዛኝ ዜና‼️
በመተማ ዮሐንስ ትላንት ረፋዱ ላይ ቤት ውስጥ #ተደብቀው ተኩስ በከፈቱ አካላት በ23 ሰዎች ላይ #የሞትና የአካል #መቁሰል አደጋ መድረሱን የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ሃላፊ ኮማንደር #ጌትነት_አልታሰብ ማምሻውን ለኢዜአ እንደገለፁት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በቤት ውስጥ መሽገው በተከቀመጡ ግለሰቦች በተከፈተ ተኩስ የ3 ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ በ20 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደሷል።
የቅማንት ማህበረሰብ ተቆርቋሪ ነኝ በሚሉ አካላት በከተማው ባለ የመኖሪያ ቤት ውስጥ በመመሸግ በመንገድ ይጓዙ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ጉዳቱ ሊደርስ መቻሉን ገልፀዋል።
ጉዳቱ ከደረሰባቸው መካከልም አንድ የፀጥታ አካልን ጨምሮ ሴቶችና ወጣቶች ይገኙበታል ብለዋል።
ጉዳቱን ካደረሱት አካላት መካከልም አራቱ እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ለፀጥታ ሃይሉ እጃቸውን እንዲሰጡ እየተጠየቁ ነው ብለዋል።
ጉዳት ካደረሱት ግለሰቦችም 9 የክላሽንኮቭ፣ አንድ ኤፍ ኤን መሳሪያ፣አንድ ሽጉጥ፣ አንድ ቦንብና በርካታ ጥይት ተይዟል ሲሉም ኮማንደር ጌትነት አስታውቀዋል።
በደረሰው ጉዳት ህይወታቸው ያለፈ ግለሰቦች አስከሬን ወደ ቤተሰቦቻቸው የተላከ ሲሆን የቆሰሉት ሰዎች ደግሞ በመተማ ዮሐንስ ጤና ጣቢያ፣ በገንዳ ውሃ ሆስፒታልና በጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረጋላቸ ነው ብለዋል።
ለዘመናት ተሳስሮ በኖረው የአማራና የቅማንት ማህበረሰብ መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ከማንደሩ፤ ችግሩ አስኪበርድ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ህብረተሰቡን በማስተማር የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመሰለፍ ጥፋተኞችን የመለየትና በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማደረግ ማገዝ እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።
በመተማ ዩሐንስ ከተማ ረፋዱ አካባቢ በተፈጠረው ግጭትም የፌደራል መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ልዩ ሃይል፣ የፖሊስ አባላትና የአካባቢ ሚሊሻዎች በጋራ በመሆን ወደ አካባቢው እንዲረጋጋ ጥረት አድርገዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግብፅ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጋሪብ አብደል ሃፌዝ ፥ በሱዳን ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል። ቃል አቀባዩ ሱዳን ውስጥ ልምምድ የሚያደርጉ የግብፅ ሃይሎች ስለመኖራቸው ተናግረው ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ይህ የቃል አቀባዩ ማብራሪያ የተሰጠው ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሚመሩት RSF (ፈጥኖ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሱዳን ነገር ከቁጥጥር እየወጣ ይሆን ?
የአል-ሱዳኒ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ያሲር አብዱላህ ሀገሪቱ ወደ ከፋ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራች እንደሆነ አስጠንቅቋል።
በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ብሏል።
እስር በርስ የሚደረገውን ግጭት ለማስቆም በሰራዊት አመራሮች በኩል ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ከሌለ ሁኔታው እጅግ ወደ ከፋ ሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት እያመራ ነው ሲል ገልጿል።
ይህ ሁኔታ በአጠቃላይ ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን የገለፀው ያሲር አብዱላህ በዚህ ውስጥ ማንም አሸናፊ የለም ብሏል።
ዛሬ ካርቱም ውስጥ በሱዳን ጦር እና RSF (ፈጥኖ ደራሽ) መካከል የከፋ የከተማ ውስጥ ውጊያ ጭምር ሲካሄድ ነበር።
ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው ድል እየተቀዳጁ መሆኑንና አንዱ የአንዱን መሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተፈላለጉ መሆኑን በሚያወጧቸው መግለጫዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።
በጄነራል አል - ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር በሄሜቲ የሚመራውን RSF " አማፂ " ቡድን ብሎ በይፋ ጠርቶታል። ዳጋሎም (ሄሜቲ) ተሸሽገው የሚገኙ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ ናቸው በማለትም ማንኛውም ዜጋ ከእሳቸው ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው አሳስቧል።
ጦሩ RSF እስካልፈረሰ ድረስ በምንም ለድርድርም ይሁን ለንግግር እንደማይቀመጥ አስገንዝቧል።
በጄነራል ሄሜቲ የሚመራው RSF በበኩሉ ድል እየተቀዳጀ መሆኑንና " ወንጀለኛ ናቸው " ያላቸውን አል ቡርሃንን #ለማሰር እያሳደዳቸው መሆኑን ገልጿል ያሉበትንም ደርሼበታለሁ ብሏል፤ ቡርሃን ግራውንድ ስር #ተደብቀው የህዝብ ልጆችን እንዲዋጉ እየገፋፉ ነው ብሏል።
@tikvahethiopia