TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መቐለ

ሕወሃትን ከኤርትራው ሕግዴፍ ጋር ለማስማማት ያለመ ምክክር መድረክ መቐለ ላይ ተጀምሯል፡፡ መድረኩን ያዘጋጀው ሰለብሪቲ ኤቨንትስ የተባለ የግል ተቋም ሲሆን ከሁለቱ ሀገራት ምሁራን፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የማቀራረቡ ጥረት ከሁለቱ ፓርቲዎች በጎ ምላሽ እንደተቸረውም DW የመድረኩን አዘጋጅ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በቀጣይነት የሁለቱን ድርጅቶች የቀድሞ ታጋዮች፣ የጦር ጉዳተኞች፣ የቀድሞ አመራሮች የሚሳተፉበት ውይይት በአዲስ አበባና አሥመራ ለማድረግ አቅዷል፡፡

Via #wazemaradio/#DW/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር #አበረ_አዳሙ ለክልሉ ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአማራ መገናኛ ብዙኻን ዛሬ ባስተላለፉት ማብራሪያ የሰኔ 15ቱ የባለ ሥልጣናት ግድያ ወንጀል ምርመራ እስካሁን ያልተጠናቀቀው ወንጀሉ ውስብስብና ምርመራው ዘርፈ ብዙ ስለሆነ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርብ ዝርዝር ሪፖርት እናቀርባለን ብለዋል፡፡ ሴራውን በማክሸፋችን ክልላችን ከመፍረስ አድነነዋል፤ ባንቆጣጠረው ኖሮ ግን የባሰ ትርመስ ይፈጠር ነበር ብለዋል፡፡ እስካሁን በተደረሰበት ድምዳሜ ከጀርባ ስላሉ አካላት ይህ ነው ተብሎ የሚቀርብ ድምዳሜ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ አማራን በጎጥ ለመከፋፈል #ፌስቡክ ላይ የሚሰሩ ሃይሎች ግን ከባድ ችግር ስለፈጠሩብን መንግሥት ያግዘን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዐቃቤ ሕግ በቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሃላፊ ደርበው ደመላሽና ሌሎች ተከሳሽ ሠራተኞች ላይ ምስክር ማሰማት መጀመሩን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ፖሊስ ምስክሮቹን በአድራሻቸው ማግኘት ስላልቻልኩ፣ በስልካቸው እንድጠራ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሏል፡፡ በአካል የቀረቡት ምስክሮች 5 ሲሆኑ፣ በደኅንነቱ ሃላፊ ደርበው ላይ የመጀመሪያው ምስክር ቃል ተሰምቷል፡፡

በደኅንነቶች ታፍኜ ስለ “ድምጻችን ይሰማ” በግድ በፌስቡክ እንድጻጻፍ ተደርጌያለሁ፣ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፤ ደርበው ትዕዛዝ ባይሰጡም በአካል በዝምታ ይከታተሉ ነበር በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ ደርበው የገራፊዎቹ አለቃ መሆናቸውን እንዴት እንዳወቀ ዳኛው ሲጠይቁትም ከሁኔታቸው ገምቼ ነው ብሏል፡፡ ተከሳሹ በበኩላቸው ምስክሩ ደመወዝ ተከፋይ የሆነ፣ የደኅንነት ተቋሙ ወኪላችን ነበር፤ ስለመታሰሩ የማውቀው ነገር የለም ሲሉ ተከላክለዋል፡፡

Via #reporter/#wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊ ቦምብ የሚል ቃል ተጠቅሞ ቀልድ በመቀለዱ የ4 ወራት እስራት ቅጣት ተጣለበት!

ባለፈው ሚያዚያ በኬንያ አየር መንገድ የተሳፈረ አንድ ኢትዮጵያዊ ቦምብ የሚል ቃል ተጠቅሞ ቀልድ በመቀለዱ የ4 ወራት እስራት ወይም የ100 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ቅጣት እንደተጣለበት ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ፍርድ ቤት ቅጣቱን የጣለበት፣ የበረራ አስተናጋጇ የዕቃ ማስቀመጫዎችን ስትፈትሽ፣ “ምነው ፈራሽ? ቦምብ መሰለሽ?” ብሎ በመቀለዱ ነው፡፡ በቀልዱ ሳቢያ ባለፈው ሚያዚያ ወደ ጁሃንስበርግ ሊደረግ የነበረ በረራ እንዲሰረዝ እና የናይሮቢው ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያም ለ3 ሰዓታት እንዲዘጋ ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በግዝፈቱ ከመርካቶ ቀጥሎ የሚታወቀው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ እሁድ ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል። መነሻው ቅመም ተራ እንደሆነ የተነገረው አደጋው በከፍተኛ ተዳርሶ በርካታ ቁጥር ያላቸው ልብስቤቶች እና ጫማ ቤቶችን አውድሟል።

እሳቱ ከምሽቱ 4 ሰአት በሁዋላ መነሳቱን በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች የተናገሩ ቢሆንም እስከ ሊሊቱ 9 ሰአት ድረስ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቢረባረቡም ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተስኗቸው ቆይቷል። በአደጋው አትክልት ተራ የሚባለውና እንደ ጌሾ እና በርበሬ እንዲሁም ሌሎች ቅመማ ቀመም የሚሸጥባቸው ቦታዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወድመዋል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች ዘግይተው ቢደርሱም ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።

Via #WazemaRadio

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይኖረናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቅምት2

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ለዕሁድ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ለአስተዳደሩ ስለ ሰልፉ ብናሳውቅም፣ እስካሁን ምላሽ አልተሰጠንም- ብሏል የባላደራው ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ፡፡ ሆኖም በሕጉ መሠረት፣ ዝምታው ዕውቅና እንደመስጠት ስለሚቆጠር ፖሊስ ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ሰልፉ ለሀገራዊ ዲሞክራሲ ነው፤ እናም ሕዝቡ ለሰልፉ ይውጣ ሲል ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰልፉ ከተደናቀፈ ባላደራው ወደሚቀጥለው የትግል ምዕራፍ ይሄዳል፡፡ መግለጫው በተሰጠበት ግቢ አቅራቢያ ወጣቶች ባላደራው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንነቱ ባልታወቀ ህመም ሰዎች እየሞቱ ነው...

በሱማሌ ክልል ሰዎች ምንነቱ ባልታወቀ ህመም እየሞቱ እንደሆነ ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡ ሟቾች እና ታማሚዎች በአፍ እና አፍንጫቸው ደም ይፈሳቸዋል፤ ከባድ ትኩሳትም ታይቶባቸዋል፡፡

የጤና ችግሩ የተከሰተው በቻይናው የካሉብ ጋዝ ፕሮጀክት አካባቢ ነው፡፡ ነዋሪዎች የሕመማችን ምክንያት የፕሮጀክቱ ኬሜካል የምንጠጣውን ውሃ ስለበከለብን ነው ብለዋል፡፡

https://www.theguardian.com/global-development/2020/feb/20/the-mystery-sickness-bringing-death-and-dismay-to-eastern-ethiopia

#WazemaRadio
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AccessNow

ባለፈው የፈረንጆች ዐመት ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሆኑ ብሉምበርግ Access Now የተሰኘውን ድርጅት ጠቅሶ ዘግቧል። ኢትዮጽያ 4 ጊዜ፣ አልጀሪያ 6 ጊዜ ዘግተዋል።

#wazemaradio
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ሀገር አቀፍ የፀሎት ቀን በኬንያ!

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መጭው ቅዳሜ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ የጸሎት ቀን ሆኖ እንዲውል ማወጃቸውን Daily Nation ዘግቧል፡፡ ጸሎቱ የታወጀው በሀገሪቱ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን እና ሌሎች በርካቶችም በማቆያ ክፍል መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

#DailyNation #WazemaRadio
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Mekelle

አሜሪካ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዜጎቿን ለማስወጣት ጥረት እያደረገች ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ባሰራጨው "የጥንቃቄ መልዕክት" መቐለ የሚገኙ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

በመቐለ የሚኖሩ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ለደኅንነታቸው ተጠልለው እንዲቆዩ መስሪያ ቤቱ መክሯል።

በክልሉ ያሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ወይም በመቐለ የሚኖር #አሜሪካዊ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ከመስሪያ ቤቱ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

#WazemaRadio #USEmbassyAA

@tikvahethiopia