TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 20,770
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 2,016
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 0
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 59
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አዲስ ያገገሙ - 3
• አጠቃላይ ያገገሙ - 69
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 133

#DrLiaTadesse #MoHEthiopia #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#correction

በዛሬው መግለጫ ላይ ጠቅላላ የተደረገ ላቦራቶሪ ምርመራ ቁጥር 19,857 ሳይሆን 20,770 መሆኑን ከይቅርታ ጋር ለማሳወቅ እንወዳለን - #EPHI

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል!

በዛሬው መግለጫ ላይ የተጠቀሱት የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመተንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ በምርመራ ውጤቱ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

#MoH #EPHI #DrLiaTadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EPHI

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አሐዛዊ መረጃ!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በላብራቶሪ ምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር እድሜ ፦

• ከ5 ዓመት በታች - 1

• ከ5-14 ዓመት - 7

• ከ15-24 ዓመት - 91

• ከ25-34 ዓመት - 75

• ከ35-44 ዓመት - 43

• ከ45-59 ዓመት - 26

• ከ60 ዓመት በላይ - 18

በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው 261 ሰዎች ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፍተኛ ጥንቄቄ ይደረግ!

- በአዲስ አበባ ያለው ሁኔታ ለይቶለት ታውቋል ፤ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነውና ከመደናገጥ #መጠንቀቅ ያዋጣል።

- በክልል ከተሞች ስርጭቱ አነስተኛ ነው በሚል መዘናጋት ተፈጥሮ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳይከተን ሊሰራ ይገባል። ከአዲስ አበባ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ አለመቋረጡን ልብ እንበል!

- ኮቪድ-19 በክልል ከተሞች ሳይታወቅ ውስጥ ውስጡን በከፍተኛ ሁኔታ ከተሰራጨ በኃላ ለመቆጣጠር ፍፁም ከባድ ይሆናልና ሁሉም አካል ከወዲሁ ኃላፊነቱን ይወጣ።

በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች (መታጠብ፣ መሸፈን፣ መራራቅ፣ መቆየት) ተግባራዊ እናድርግ!

VIDEO : #EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ 100 ቀናቶች!

#EPHI እና #MoHEthiopia ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ላለፉት 100 ቀናት (ከመጋቢት 4-ሰኔ 14) መጠነ ሰፊ የሆኑና በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።

የተሰሩ ስራዎችን እንደሚከተለው ዘርዝረዋል ፦

- 216,328 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል (እስከ ትላንት ሰኔ 14)

- 4,532 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል (እስከ ትላንት ሰኔ 14)

- ንክኪ ያላቸው 31,573 ሰዎች ተለይተው 708 ሰዎች የኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል

- ለ764,948 ተጓዦች ልየታ እና ክትትል ተደርጓል (ከጥር 15 ጀምሮ)

- 32 ሚሊዮን ሰዎች በቤት ለቤት ዳሰሳ ታይተዋል

- 13,859 የማከምያ አልጋዎች ተዘጋጅተዋል

- ከ4,500 በላይ ተጨማሪ የጤና ባለሞያዎች ተቀጥረዋል፤ 12,000 በጎ-ፍቃደኞች ተሰማርተዋል

- 513 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የግል መከላከያ ቁሳቁሶች (PPE) በሃገሪቱ ተሰራጭተዋል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SHARE #ሼር

በተሻሻለው መመሪያ መሰረት በቤት ውስጥ ሆነን የኮሮና ቫይረስ ሕክምና የምንከታተል ሰዎች በሽታው ወደ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እንዳይሰራጭ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ አለብን - #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EPHI

አንዳንድ የግል ጤና ተቋማት የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች እንደደረሰው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በሃገራችን ምርመራዉን ማድረግ የሚቻለው በrRT-PCR Machine ብቻና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፍቃድ ሲያገኙ ሲሆን ከዚህ ውጭ ሲሰራ የተገኘ የግል ጤና ተቋም አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ለግል ጤና ተቋማት በላክው ደብዳቤ አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈም የሚመለከተው አካል እና ማህበረሰቡ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ምክንያትአልሆንም የኮሮና ስርጭትን እገታለሁ!

ኤ.ቲ.ኤም (ATM) ከመጠቀሜ በፊት እና በኃላ እጄን በውሃ እና በሳሙና ወይም በሳኒታይዘር አፀዳለሁ #EPHI #MoH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ስለኮቪድ-19 ኢትዮጵያ መተግበሪያ፦

የኮቪድ ኢትዮጵያ መተግበሪያ በውስጡ ስለኮቪድ ቁጥጥር ፣ ህክምና እና መከላከል ማወቅ ያለብንን በ7 ኮርሶች የያዘ ሲሆን ስልጠናው ፦

- የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶቦት በቤት ውስጥ እራሳችንን ለይተን ለራሳችን ማድርግ ስለሚገባን እንክብካቤ እና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ማድረግ ስለሚገባን ጥንቃቄ ያሳውቃል።

- ስለኮቪድ-19 ክትባት ለማወቅ እና ስልጠና ለመውሰድ ይጠቅማል።

- ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሰራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ለማውቅ ይረዳል።

- ሰልጣኞች ስልጠና እንዳጠናቀቁ በሚመዘገቡበት የስልክ ቁጥር ባላቸው የቴሌግራም አድራሻ ስልጠናውን በአግባቡ ላጠናቀቁ እና የስልጠና መመዝኛውን ከ80 በመቶ በላይ ላስመዘግቡ በጤና ሚኒስቴር የተረጋገጠ የተከታታይ ሙያ ማጎልብቻ ነጥብ ያለው ሰርተፍኬት የሚላክላቸው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በየ3 አመት ለሚደረገው የሙያ ፍቃድ እድሳት ነጥብ ለመጠቀም ያስችላል።

- መተግበሪያውን በተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከጫኑና ስልጠናዎች ካወረዱ በኋላ ኢንተርኔት የማይፍልግ ሲሆን ስልጠናውን የሚስብ እና ለመረዳት ቀላል ለማድረግ ቪድዮዎች ተካተውብታል።

- ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የኮቪድ ስርጭት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም የተሻለ እንክብካቤ ለመስጠት ይረዳል።

መተግበሪያውን ከየት ላግኘው ?

መተግበሪያውን በስልክዎ ለመጫንና ስልጠናውን ለመከታተል ይህን ሊንክ ይጫኑ - https://bit.ly/3apv5J2

#MoH #EPHI

@tikvagethiopia @tikvagethiopiaBOT
#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia