TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ትንሳኤ ጥቅል እስከ 50% በሚደርስ ቅናሽ ከ1ጊ.ባ ዳታ ስጦታ ጋር !

እንደ ወግ ልማዳችን እንኳን አደረሰን የምንባባልበትን ልዩ የትንሳኤ የሞባይል ጥቅል እስከ 50% በሚደርስ ቅናሽ ከ1ጊ.ባ ዳታ ስጦታ ጋር ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን!

ልዩ የትንሳኤ ጥቅሎቹን በቴሌብር ሱፐርአፕ ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል እና *999# ለራስዎ በመግዛት እና ለወዳጅ ዘመድ በስጦታ በማበርከት በዓሉን በደስታ ያሳልፉ!

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#ETHIOPIA

ዛሬ የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የጣልያንን ጠ/ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ለሁለት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጽያ የመጡ ሲሆን የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገሮቻችንን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አጋዥ ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የጎረቤት ሀገር ፕሬዜዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ኢትዮጵያ የመጡት በተመሳሳይ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በተለያዩ ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

" ከኃላፊነት ለቀዋል "

የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከብሔራዊ ቡድኑ #በጋራ_ስምምነት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ በብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ቆይታቸው ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ እና የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማብቃት ችለዋል።

More : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

Via @tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በዓለ ስቅለት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን በተለያዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ተከብሯል።

በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ስቅለት  በስግደትና በጸሎት ሥነ ሥርዓት ነው የተከበረው።

ይህ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅን ለማዳን ሲል የተቀበላቸውን መከራዎች ለማስታወስ የሚከበር ነው።

Photo Credit ፦ ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ስቅለት " በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው። ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን…
ፎቶ፦ በዓለ ስቅለት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን በጾም ፣ በጸሎት እና ስግደት ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።

ሐዋርያዊት ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ፤ ጌታዋ እስከመስቀል ሞት ድረስ የከፈለላትን መከራና ዋጋ በማሰብ ነው የዛሬውን ቀን (ስቅለት) በመላው ዓለም በሚገኙት አብያተ ክርስቲያኗ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በጾም በጸሎትና በስግደት የምታከብረው።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የጸሎትና የስግደት ሥነ ሥርዓቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መሪነት ነበር የተከናወነው።

Photo Credit : EOTC TV ፣ Demtsi Woyane (Mekelle) ፣ ተጨማሪ ከማህበራዊ ሚዲያዎች

@tikvahethiopia
ጠቅላይ ኢተማዦር ሹሙ ምንድነው ያሉት ?

የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ኢተማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፥ " ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም " ብለዋል።

ይህንን ያሉት የክልል ልዩ ሃይሎችን በፌዴራልና የክልል የጸጥታ ተቋማት መልሶ የማደራጀት ስራ የመከላከያ ጀነራሎች፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልል የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ሲገመገም ነው።

ፊልድ ማርሻሉ ምንድነው የተናገሩት ?

" የክልል ልዩ ሃይሎች እንደገና በመደራጀታቸው ህብረ ብሄራዊ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም ይገነባል።

የክልል ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት ህጋዊ አለመሆን፣ በክልሎች መካከል እንደ ስጋት መተያየት እንዲሁም ችግሮችን በሃይል ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ አደረጃጀቱን ለመቀየር አስገድዷል።

በአሁኑ ወቅት በሁሉም ክልሎች መልሶ የማደራጀት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀትና መዋቅር የለም።

በመሆኑም የጸጥታ መዋቅሩ መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ሲሆን በክልል ልዩ ኃይሎች ስም ተልዕኮም ሆነ ግዳጅ የሚቀበል ኃይል አይኖርም።

ከዚህ በኋላ በመረጡት አደረጃጀት መሰረት ሁሉንም ወደ ተመደቡበት የማጓጓዝና ወደ ስልጠና የማስገባት ስራ ይከናወናል። "

#ENA

@tikvahethiopia