TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጅግጅጋ

"ወንድማማችነትን በማጠናከር የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ለመሆን እንሰራለን" የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፌ_መሀመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ_ዩንቨርስቲ

‹‹2012 የሰላምን ምንነት የምናሳይበት እንዲሆን እየሰራን ነው›› - ዶክተር #አብዲ_አህመድ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት
.
.
የ2012 የትምህርት ዘመን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ብቻ ሳይሆን የሰላምን ምንነት ለማሳየት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። በትምህርት ዘመኑ 3ሺ612 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱም ተጠቁሟል። የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አብዲ አህመድ ሀሰን እንደተናገሩት፤ የ2011 የትምህርት ዘመን የጎላ ችግር አይታይበት እንጂ ለዩኒቨርሲቲው አመራር፣ መምህራንና አጠቃላይ ሰራተኛው ፈተና ሆኖ አልፏል። ከዚህ ሂደት በመማርም የ2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን፤ ተግባሩም ዩኒቨርሲቲው የሰላምን ምንነት የሚያሳይበት፤ ህብረተሰቡም ሰላምን የሚያስተምርበት እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ነው ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ
#ሀዋሳ
#ነቀምት
#አሰላ
#አዲስአበባ
#ሽሬ
#ደብረብርሃን
#ወላይታሶዶ
#አርባምንጭ
#ጅግጅጋ
#አዳማ
#ድሬዳዋ
#ባህርዳር
#መቐለ
#ሀረር
#ጎንደር

ከሌሎች በርካታ ከተሞች ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች የSAT ውጤት ያልጠበቁት እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አራተኛው አስቸኳይ ጉባዔ የቢሮ ኃላፊዎችን ሹመትና ረቂቅ ዓዋጅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የቀረቡለትን ኃላፊዎችን ሹመት ያፀደቀው አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች እንደገና ለማደራጀት ሥልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ ዓዋጅ ካፀደቀ በኋላ ነው።

ተሿሚዎቹ  ባላቸው የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና የፖለቲካ ብቃት መሠረት በማድረግ መመረጣቸው ተገልጿል። ምክር ቤቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ሁለት የምክር ቤቱ አባላትን #ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ወስኗል። እንዲሁም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ ዓዋጅ ለሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ አግኝተው የተሾሙት፦

•አቶ አብዲቃድር ሐሺ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሱቤር ሁሴን – የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ጠይብ አህመድኑር – የእንስሳት ልማት ቢሮ ኃላፊ
•አቶ አብዲሰላም ዩሱፍ – የኢንቨስትመንትና ዲያስፖራ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሩብሌ አዋሌ– የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፣

ባሉበት እንዲቀጥሉ የተደረጉት፦

•ዶክተር ዩሱፍ መሐመድ የጤና ቢሮ ኃላፊ
•ዶክተር አብዲቃድር ኢማን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ
•ወይዘሮ ዘይነብ ሐጂ አደን የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሙበሽር ዱበድ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ኤልያስ አቢብ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
•አቶ ሐሰን መሐመድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

10ኛው የፌደራል ና የክልሎች ማረሚያ ቤቶች የውይይት መድረክ በጂግጂጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ ውይይቱም ‘’ሃጋራዊ የማረሚያ ተቋማት ሪፎርም ለውጤታማ የማረም፣ ማነፅና ተሀድሶ ልማት’’ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሔደ ያለው፡፡በመድረኩ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙሰጠፌ መሀመድ ሁመርን ጨምሮ የክልሎችና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው በአግባቡ ሊተገበር ይገባል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ተናገሩ። ለአዲሱ ፍኖተ ካርታ ስኬታማነት የትምህርት ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የመሪነት ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ትናንት የተጀመረው 29ኛው አገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ በአዲሱ የትምህርትና የስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ #ጅግጅጋ ነገ ታላቅ የሰላም ፌስቲቫል እንደሚካሄድ ተገለጸ። ፌስቲቫሉ በሰላም ሚኒስቴርና በሱማሌ ክልል ሰላም፣ ፍትህና አስተዳዳር ቢሮ ትብብር ነው የተዘጋጀው።

ጅግጅጋ ሰላማዊ ከተማ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ፌስቲቫሉ ነገ በተለይ በከተማው ስታዲየም ነዋሪዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

በፌስቲቫሉ ሰላምን የሚሰብኩ መልዕክቶች የሚስጋቡባቸው ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችም ይቀርባሉ። በዛሬው እለትም በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ በማርሽ ባንድ የታጀበ የጎዳና ላይ ትርኢት ቀርቧል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህ ወር በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠሙ የእሳት አደጋዎች ፦

#ወልቂጤ_ከተማ (ጉራጌ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በኩር ክ/ከተማ አርሴማ መንደር

• የደረሰው ጉዳት - 14 ቤት ሙሉ በሙሉ 6 ቤት በከፊል ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው።

#ቤሮ_ወረዳ (ምዕራብ ኦሞ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ሾላ ቀበሌ

• የደረሰው ጉዳት - 1840 መኖሪያ ቤቶች፣ 547 የንግድ ቤቶች፣ 37 የወርቅ ማህበራት ፣ 109 የወርቅ ማሽን በአጠቃላይ 586 ሚሊዮን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እስካሁን አልታወቀም።

#ሆሳዕና_ከተማ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰው በአንድ የገበያ ማዕከል አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል። በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እና አልባሳት ንግድ ድርጅቶች ከነ ንብረታቸው ወድመዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ፖሊስ እያጣራው ነው።

#መካነሠላም_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• በመካነ ሠላም ከተማ በንግድ ቦታ ላይ ድንገት የተከሰተ አደጋ።

• የደረሰው ጉዳት - በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ በሴቶች የውበት ሳሎን፣ በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሳል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም።

#ወላይታ_ሶዶ_ከተማ (ወላይታ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - መርካቶ ገበያ

• የደረሰው ጉዳት - 1 ቢሊዮን 57 ሚሊዮን 670 ሺህ ብር ወድሟል። 42 ሺህ ገደማ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ለቀውስ ተጋልጠዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አንታወቀም፤ በፖሊስ እየተመረመረ ይገኛል።

#ማሻ_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - አዲሱ መናኸሪያ አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 2 ሼዶች በውስጣቸው ካለ ሙሉ ንብረት ጋር ወድመዋል። ሼዶቹ በውስጣቸው ሱቆች፣ ፖስታ ቤት፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ይገኙበታል። 1 ሚሊዮን 224 ሺህ 936 ብር የሚገመት ሃብት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም፤ እየተጣራ ነው።

#ዌራ_ወረዳ (ሀላባ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ

• የደረሰው ጉዳት - 11 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እህል የተከመረበት ቦታ ላይ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞባልይ ስልክ ፈንድቶ።

#ምሻ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ኤራ ጌሜዶ፣ ኩናፋ፣ ጉና ማጋቾ ቀበሌዎች

• የደረሰው ጉዳት - 128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያየ እህል፣ 18 የንብ ቀፎ ፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች በድምሩ 23 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - የተፈጥሮ እሳት

#ሶሮ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በጃቾ ከተማ

• የደረሰው ጉዳት - ከ250 ሺህ ብር በላይ ወድሟል።

• የአደጋው ምክንያት - የመብራት ኮንታክት

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

• የአደጋው የደረሰበት ቦታ - ዋናው ግቢ ህንፃ 3

• አደጋው የኤሌክትሪክ መቆጣጣሪያ ላይ የተነሳ ነው።

• የደረሰው ጉዳት - መጠኑ ያልተገለፀ ንብረት ጉዳት ደርሶበታል።

#ቡራዩ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ገብርኤል አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 16 ሱቆች ፣ 3 መኖሪያ ቤቶች፣ 3 ባርና ሬስቶራንቶች ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ ግምንቱ 10 ሚሊዮን ብር የሆነ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እየተጣራ ይገኛል።

#ባህር_ዳር_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 3 ጉዶባህር የሚባለው ሰፈር

• የደረሰው ጉዳት - 22 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በገንዘብ 300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - እንጀራ ከሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ ነው።

#ጅግጅጋ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 2 ልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ

• የደረሰው ጉዳት - 7 የምግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ንብረት አደጋ ደርሶበታል ይህም 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ከአንድ ቤት ውስጥ ነው የተነሳው ተብሏል።

#ደብረማርቆስ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ጉልት ገበያ አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - 48 የንግድ ሱቆች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ቅመማቅመም፣ አትክልት እና ፍረፍሬ ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የንብረት ግምት እየተጣራ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም በፖሊስ እየተጣራ ነው።

በዚህ ወር በደረሱት የእሳት አደጋዎች በርካቶች ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ፣ ቤታቸው ወድሞባቸው ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

በርካቶች ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

* የአብዛኛዎቹ የእሳት አደጋዎች ትክክለኛ መንስኤ በግልፅ አይታወቅም።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጅግጅጋ የሆነው ምንድነው ? ከሰሞኑን በጅግጅጋ ከተማ እጅግ አሰቃቂ የተባለ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፅሟል። የአስገድዶ መድፈር ወንጀሉ የተፈፀመባት የ9 ዓመት ህፃን ልጅ ስትሆን ይህ ድርጊት ከተፈፀመባት በኃላ የድርጊቱ ፈፃሚዎች የደፈሯትን ልጅ ገድለዋታል። ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት በኃላ ወንጀሉን የፈፀሙ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደቻሉ ተገልጿል። ነገር ግን ከዚህ የወንጀል ድርጊት…
#ጅግጅጋ

ከሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በተገኘው መረጃ በጅግጅጋ ከተማ የ9 ዓመቷን ልጅ #ደፍረው_ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 ተጠርጣሪዎች በአባቷ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ናቸው።

በልጅቷ አባት ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር ከተባሉት ከአራቱ ተጠርጣሪዎች አንዱ ላይ በዋናነት ምልክቶች እንደሚታዩ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል።

ከሚታዩት ምልክቶች አንዱ ፤ ልጅቷን ሲደፍሯት የጥፍሮቿ ምልክት እንዲሁም ደም ይታይበታል ተብሏል።

የወንጀሉ ድርጊት ምርመራ አሁንም እየተካሄደ ሲሆን ክልሉ ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጅግጅጋ ከሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በተገኘው መረጃ በጅግጅጋ ከተማ የ9 ዓመቷን ልጅ #ደፍረው_ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት 4 ተጠርጣሪዎች በአባቷ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ናቸው። በልጅቷ አባት ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር ከተባሉት ከአራቱ ተጠርጣሪዎች አንዱ ላይ በዋናነት ምልክቶች እንደሚታዩ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል። ከሚታዩት ምልክቶች አንዱ ፤ ልጅቷን ሲደፍሯት የጥፍሮቿ ምልክት እንዲሁም…
#ጅግጅጋ

" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ " - አባት

በጅግጅጋ ከተማ የተደፈረችው ልጅ አባት ምን አሉ ?

አባት ኡጋስ አረብ በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ልጃቸው በራሳቸው ሰራተኞች ከተደፈረች በኃላ መገደሏን ገልጸዋል።

ለቢቢሲ ሶማሊ ክፍል አባት ኡጋስ አረብ ፦

" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ። እለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፋ ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ።

በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከእኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም።

ልጄ ጋር ሄጄ ሳያት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ።

አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጬ ወደ ሐኪም ወሰድኳት።

ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰን ብንወስዳትም ሕይወቷ አልፏል።

በሞባይል ጥገና ሱቄ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ አራቱ ሠራተኞቼ በድርጊቱ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል። " ሲሉ ተናግረዋል።

Via BBC Somali

@tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱና ልኡካቸው ገራድ ዊልዋል ኤርፖርት ሲደርሱ የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሁለቱም በኩል ያሉ ባለስልጣናት የንግድ ትብብርን በተመለከተና በድንበር #የፀጥታ እና #ደህንነት ጉዳዮች (በሶማሌ ክልል እና በሶማሌላንድ) ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እውን ያደርጋል የተባለለንትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው አይዘነጋም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤስአርቲቪ ሶማሊኛ ክፍል ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የሶማሌና አጎራባች ክልሎች የሜትዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል አሳውቋል።

በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል #ጥንቃቄ እንዲደረግ ተብሏል።

የማዕከሉ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን ሀ/ማርያም ለሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ " በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የተሰራው ትንበያ እንደሚያሳየው በቀጣይ 10 ቀን ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር ይችላል የሚል ነው " ብለዋል።

" በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚጠበቁት በሰሜኑ ላይ #ከድሬዳዋ ጀምሮ #በጭናቅሰን እስከ #ጅግጅጋ ድረስ ነው " ብለዋል።

" በብዛት በኦሮሚያ ሃይላንድ በቀርሳ ፣ በቁልቢ ከፍታ ቦታዎች ላይ ከሚዘንበው ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይ #ድሬዳዋ ላይ ብዙ ዝናብ ከተማው ላይ ሳይዘንብ ጎርፍ የመምጣት እድል አለው። በተመሳሳይ #ጅግጅጋ ላይ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል " ሲሉ ገልጻዋል።

ዋቢ ሸበሌ፣ ከኢሚ፣ ጎዴ፣ ቀላፎ፣ ሙስታይል ወደታች ያለው አካባቢ ጎርፍ ሊመጣ የሚችልበት እድል ስላለ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia