TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
(የካቲት 27/2011 ዓ.ም.)

#የሀዋሳ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ ሠራተኞች ሥራ የማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞች አድማ የመቱበት #ምክንያት በተደጋጋሚ ጊዜ አቅርበናል ያሉት #የደመወዝ ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ መሆኑን ተናግረዋል። ሠራተኞቹ #ደኅንነታቸው እንደማይጠበቅና ለፆታዊ ጥቃትና ለዝርፊያም እንደሚጋለጡ ገልፀዋል።

በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ #በላይ_ኃይለሚካኤል “ችግሩ የአንዳንድ ኩባንያዎችና የአስተዳደር በደል ነው” ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጤና ሙያተኞች #የደመወዝ እርከን ጭማሪ ተፈቀደ!!

ለጤና ሙያተኞች በተሰጣ ቸው ላይ ሁለት እርከን ተጨምሮላቸው የተፈጠረው ልዩነት እንዲስተካከል መደረጉንና በሐምሌ ወር ሁለት ዓመት ለሚሞላቸው የጤና ሙያተኞችም በዕድገት ስም ሦስት ዕርከን እንዲሰጣቸው ውሳኔ ማግኘቱን ሲቪስ ሰርቪስ ኮሚሽን ገለጸ።

የጤና ሙያተኞች ቀደም ሲል በተሰጣቸው አንድ እርከን ደመወዝ ጭማሪ ሁለት እርከን እንዲጨመርላቸውና ሌሎች ክልሎች እንዳደረጉት የተፈጠረው ልዩነት እንዲስተካከል፤ በሐምሌ ወር ሁለት ዓመት ለሚሞላቸው የጤና ሙያተኞችም ሌላ ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልግ በዕድገት ስም ሦስት ዕርከን እንዲሰጣቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ መጽደቁን የሲቪስ ሰርቪስ ኮሚሽን ለዝግጅት ክፍሉ በላከው መግለጫ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የሰው ሀብት አስተዳደር አማካሪ አቶ ይገዙ ጀማነህ፤ በ2009 ዓ.ም ጭማሪ ሲሰጥ እርከን ውስጥ የገቡ ባለሙያዎችና አጠቃላይ የመንግሥት ሠራተኞች በደንቡ መሠረት ከመነሻ በታች የሆኑትን ወደ መነሻው የማምጣት፤ መነሻውን ለደረሱበት ደግሞ አንድ ተጨማሪ እርከን እንዲያገኙ ተደርጎ እንደነበረ በማስታወስ፤ ለጤና ሙያተኞች አንድ እርከን ተሰጥቷቸው የነበረው ተቀይሮ ሁለት እርከን ተጨምሮላቸው የተፈጠረው ልዩነት እንዲስተካከል መደረጉን ጠቁመዋል።

በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ሁለት ዓመት ለሚሞላቸው የጤና ሙያተኞችም ደግሞ ሌላ ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልግ በግንቦት 8 ቀን 2011 ዓ.ም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወስኖ ባሳወቀው በዕድገት ስም መሠረት ሦስት ዕርከን ጭማሪ እንዲሰጣቸው መባሉንም ነው የገለጹት፤ “ጄኢጂ” ከተተገበረ ግን አሁን የወረደው መመሪያ ሊቀር እንደሚችልም ጠቁመዋል።

 “ኬሪየር ስትራክቸሩ” ይቀጥላል ያሉት አማካሪው፤ ባለሙያዎቹ ሦስት ሦስት እርከኖች እያገኙ “ጄኢጂ”ው ከገንዘብ ጋር ተሳስሮ ተግባራዊ እስከሚሆን ይቀጥላሉ ብለዋል። የሚተገበረውም በዚህ ዓመት ይሁን በቀጣይ ጊዜውን በውል እንደማያውቁትም ተናግረዋል። የውጤት ምዘና ተግባራዊ እንደሚደረግ በመጠቆምም፤ ትግበራው የሚያስገኘው ውጤት ሊኖርም ላይኖርም ይችላል፤ እንደ ባለሙያው አፈጻጸም ይወሰናል ነው ያሉት፤
የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶክተር አየለ ተሾመ፤ የጤና ሙያተኞች አንዱ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን በማንሳት፤ “ሙያው ቴክኒካል ነው፤ ሲከፈል የሚጨመር ሳይከፈል ደግሞ የሚቀነስ አይደለም። የሰሞኑ ሥራ ማቆምም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያደረሰው ተጽእኖ የለም” ብለዋል። ጥያቄው የቆየ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። ጥያቄው መመለሱ አግባብነት እንዳለውም ተናግረዋል።

ትናንትናም የተወሰኑ ተመራቂ ተማሪዎች ሥራ እናቆማለን ብለው የቀሩ እንዳሉ የጠቀሱት ዶክተር አየለ፤ ቀድመው በደብዳቤ አሳውቀው ስለነበረ ያለውን የሰው ኃይል በመጠቀም ሥራው መሸፈኑን ተናግረዋል። በአገልግሎቱ ላይ የተፈጠረ ችግር ባይኖርም ባለሙያዎች ላይ ጫና ማሳደሩን ግን ጠቁመዋል።

አሁን የሚነሱ ጥያቄዎች አብዛኛዎቹ እርሳቸው ተማሪ በነበሩበት ጊዜም ይነሱ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ ከደመወዝ ማስተካከያ፣ የጤና ትምህርት አሰጣጥ ሥርዓትና ምቾት፣ ጥቅማ ጥቅምና የጤና ደህንነት ችግሮች የዘርፉ ማነቆዎች እንደሆኑና ሊቀየሩ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። “በጥያቄዎቹ ልዩነት የለንም፤ ልዩነታችን የጤና ባለሙያዎች በጥያቄው አቀራረብ ላይ ነው። ባለሙያዎች ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ አገልግሎት ፈላጊዎችን እያገለገሉ ሊሆን ይገባል” ብለዋል።

በእኛ ዕድሜ ጥያቄ ስናቀርብ ተሰሚነት አልነበረንም ያሉት ዶክተር አየለ፤ አሁን ጥያቄው ምላሽ ማስገኘት መጀመሩን በበጎነት አንስተዋል። አብዛኛው ሐኪም ገቢው ዝቅተኛ ነው፣ የደህንነት ስጋቶችም አሉበት፤ መስተካከል ይገባዋል ብለዋል። የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን በመጠቆምም፤ በአገር አቀፍ ደረጃ በውጤት ላይ የተመሰረተ የአከፋፈል ሥርዓት መተግበር አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶክተር ይርጉ ገብረ ሕይወት በበኩላቸው፤ በሆስፒታሉ ዋናውን አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ሥራ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። እስከ ትናንት በነበረው ሂደት ግን ተለማማጅ ዶክተሮች ተግባር ላይ እንዳልተገኙ ጠቅሰዋል። “ተማሪ ሐኪሞች ናቸው፤ አስተዋጽኦ አላቸው፤ ያም ሆኖ ግን ሥራው ቀጥሏል” ብለዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተፈጠረ ምንም ተጽዕኖ አለመኖሩን ገልጸዋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ የጤና ባለሙያ እንዳሉትም፤ ለሠራተኞች የጤና ደህንነት ክፍያ እንዲኖር፤ የሥራ ላይ ዋስትና ሊገባላቸው፤ የመኖሪያ ቤትና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ሊሰጧቸው እንደሚገባ አመልክተዋል። እንደርሳቸው አባባል፤ የሥራ ሰዓት በሕጉ መሠረት እንዲከበርላቸው፤ በእ ረፍት እንዲጣጣላቸው ወይም በክፍያ እንዲካካስላቸው ነው የሚፈልጉት፤ መድኃኒቶች እንዲሟሉ፤ የሕክምና መሣ ሪያዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እና አስፈላጊ የሕክምና መሣሪያዎች እንዲሟሉ የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚገባም አመልክተዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ መምህራን ጥያቄ ምን ተባለ ?

የዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ " በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ " መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች መግለጻቸውን የማኅበሩ አመራሮች ተናገሩ፡፡

አመራሮቹ ይህን ያሳወቁት ትላንትና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመምህራን እና በሀገር ጉዳይ ከተወያዩ በኃላ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።

የማህበሩ ፕሬዜዳንት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፤ እንደተለመደው አሠራር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን በሚሠሩበት አካባቢ የመኖሪያ ቦታ የማግኘት አሠራሩ የሚቀጥል ሆኖ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን መኖሪያ ቤት በሚመለከት ግን ውይይት እየተደረገበትና ጥሩ ምላሽ ሊገኝ እንደሚችል እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡

" የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት ጥያቄን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን ዕልባት እንዲያገኝ እየተሠራበት እንደሆነ ነው የተገለጸልን " ሲሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላገኙት ምላሽ አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከዚህ በፊት ሲያነሱት ስለነበረው #የደመወዝ ጥያቄን በሚመለከት ማኅበሩ አንደኛው ይዞት የሄደው ጉዳይና የተወያየበት ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ ለደመወዝና መሰል ጥያቄዎች በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንዳደረጉባቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል፡፡

የደመወዝ ጭማሪውን በሚመለከት፣ የኑሮ ውድነትን በአጠቃላይ የማቅለል ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹላቸው፣ ይህንንም ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ በውይይታቸው ላይ እንደተነሳ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

የማኅበሩ አመራሮችም ስለ ደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለማግኘት ጠብቀው እንዳልሄዱም ተናግረዋል፡፡

" ማናችንም ደመወዝን በሚመለከት ‹ከዛሬ ጀምሮ ይህን ያህል ጨምረናል› የሚል መልስ አንጠብቅም፡፡ ችግሩ እንዳለና ትኩረት ተሰጥቶ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲፈጽም ነው ያነሳነው " ሲሉ የማህበሩ ፕሬዜዳንት ገልጸዋል።

የማኅበሩ አመራሮች ከመምህራን ጥያቄዎች በተጨማሪ ፦
- የሙያ ጥያቄና የመምህርነት ሙያ ምንነትን በሚመለከት፣
- የት/ቤቶች አቅምና ግብዓት ፣
- ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠርን በሚመለከት
- ማህበሩ ለመገንባት ስላቀደው ህንፃና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion ➡️ " ... በረሀብ ከምንሞት መብታችን እየጠየቅን አደባባይ ላይ መሞት መርጠን ነው ወደ ርእሰ መስተዳድሩ ቢሮ የሄድነው " - የሶዶ ዙሪያ የመንግስት ሰራተኞች ➡️" ማንም መብቱን በነጻነት የመጠየቅ መብት አለው " - የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃፊዉ አቶ ወገኔ ብዙነህ የ2 ወራት ደሞዛችን ይከፈለን ያሉ የወላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች አደባባይ መውጣታቸዉን…
#ደመወዝ #ደቡብኢትዮጵያ

° " ...ድርጊቱ የደመወዝ ቅሸባ ነው ሊባል የሚችለው ፤ እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል ሰምተንም አናውቅ " - ሰራተኞች

° " ከእኛ #የሚወርደው የበጀት ሀብት እኮ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው " - የክልል ፋይናንስ ቢሮ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች " የደመወዝ ይከፈለን " ጥያቄ በብርቱ ከተነሳባቸው አካባቢዎች አንዱና ዋነኛው የ #ወላይታ_ዞን እንደሆነ ይታወቃል።

ሰራተኞቹ ችግር ሲብስባቸው እና ታግሰው ሲመራቸው ሰልፍ  ጭምር በመውጣት ጥያቄ አቅርበዋል።

ለ3 ወራት ያለ ደመወዝ የቆዩት የመንግስት ሰራተኞች አሁን ላይ #የ40_በመቶ እና #የ50_በመቶ ክፍያ ብቻ እየተፈጸመላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል #የፋይናንስ_ቢሮ ፤ " ደመወዝ ባለመክፈል የመንግሥት ሰራተኛውን እያስራቡ ይገኛሉ " ባላቸው የዞንና የወረዳ የስራ ሃላፊዎች ላይ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ #እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል።

ቢሮው ለወረዳዎቹ በቂ በጀት ማስተላለፉን ገልጿል።

" ለሰራተኛው #ግማሽ_ደመወዝ በመክፍል ቀሪውን ለሌላ የወጭ ርዕስ ይጠቀሙበታል " ሲል ወቅሷል።

አሁን በተለያዩ ወረዳዎች እየተከፈለ ይገኛል የተባለው ደመወዝ በዞኑ መንግሥት ሰራተኞች ዘንድ አጥጋቢ ምላሽ ተደርጎ አልተወሰደም።

ሰራተኞቹ ለ ' ዶቼ ቨለ ሬድዮ ' በሰጡት ቃል ፤ " ምላሹ አጥጋቢ ያልሆነ ፣ የሰራተኛውን ስነ ልቦናም የጎዳ ነው " ብለውታል።

የመንግስት ሰራተኞቹ ፥ ደመወዛቸው ባልተለመደ ሁኔታ ተቆራርጦ እየተከፈላቸው እንደሚገኝ ተናግረው ፤ " የሰራተኞች ጥያቄው ተመልሷል ለማለት እንቸገራለን " ብለዋል።

በአብዛኞቹ ወረዳዎች ላይ አሁን እየተከፈለ የሚገኘው የደመወዛቸውን ከ40 እስከ 50 ፐርሰት ያህል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሰራተኞቹ ፦

ደሞዛችን እንደተፈለገ ተቆረጦ እየቀረ ነው፤

አከፋፈሉ የፋይናንስንም ሆኖ የመንግሥት ሰራተኛ አስተዳደር መመሪያን የሚጻረር ነው፤

ድርጊቱ #የደመወዝ_ቅሸባ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም ምክንያቱም እንዲህ አይነት የደመወዝ አከፋፈል በትኛውም ዓለም ሰምተን አናውቅም ብለዋል።

ሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ዎላይታ ሶዶ ላይ የፋይናንስ ባለሙያዎች ሥልጠናዊ ውይይት አካሄዶ ነበር።

በመድረኩ የደሞዝ ጉዳይ በሰራተኞች ተነስቷል፡፡

የቢሮው ሃላፊ የሆኑት አቶ ተፈሪ አባተ ፥ ፋይናንስ ቢሮ ለወረዳዎች በቂ የበጀት ሀብት እያስተላለፈ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።

ወላይታን ጨምሮ በክልሉ አንዳንድ ወረዳዎች ውቅጥ የፋይናንስ ቁጥጥር / ኦዲት / መደረጉን ጠቅሰዋል።

" ወደ ወረዳዎች ሚወርደው የበጀት ሀብት የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ ለመክፈል የሚያስችል ነው፡፡ ይሁን አንጂ አንዳንድ ወረዳዎች ከአሰራር ውጭ ደመወዝ #በፐርሰንት_እየከፈሉ ሰራተኛው እንዲራብ ፣ በክልሉ ላይም እንዲያማርር እያደረጉ ይገኛሉ " ብለዋል።

ክልሉ በቀጣይ በእነኝህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ " #ለሽብረቃ የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመገደብ የሚያስችል የወጭ ቅነሳ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል " ሲሉ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።

Credit - #ዶቼቨለሬድዮ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል። ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው። ተጨማሪ በጀቱ ፦ ➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣ ➡️ ለነዳጅ…
#የደመወዝ_ጭማሪ

" ታች ላለው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ስለ መንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ ምን ተባለ ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በዚህ ማብራሪያቸው በሪፎርሙ በዋጋ ንረት ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ / ሪፎርሙ በትሩን ሊያሳርፍባቸው ይችላል ተብሎ ከተለዩት የመንግሥት ሠራተኞች ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።

በመሆኑም ዝቅተኛ  የሆነ ወርሃዊ ደመወዝ ለሚበሉት ሠራተኞች ከፍተኛ የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦

" መንግሥት በወር 1,500 ብር የሚበላ ሠራተኛ አለው።

የአሁኑ ደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት ጠይቆናል።

ለዚህ ምን አይነት መንገድ ተከተልን ታች ያለው 1,500 ብር የሚበላው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም።

ላይ ያለው ከ25 ሺህ በላይ ያለውን ለጊዜው ታገሰን አልነው።

ደመወዝ የጨመርነው ታች ለሚጎዱት ይሄ ሪፎርም ለሚጎዳቸው ሰዎች በርከት ያለ ሃብት ጨምረን ትንሽ ሻል ሻል ያለና ለተወሰነ ጊዜ ጫናውን ለሚቋቋሙት አቆየን  ይበቃቸዋል ማለት አይደለም እነሱም ቢሆኑ ፤ በንጽጽር ግን በጣም እያለቀሰ የሚያድረውን ሠራተኛ ማገዝ አለብን ነው።

ተሿሚዎች ብዙ ላያገኙ ይችላሉ። ታች ግን አድርገናል። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት 971.2 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ከጸደቀው ገንዘብ ውስጥ ፦ ➡️ 451,307,221,052 ለመደበኛ ወጪዎች ➡️ 283,199,335,412 ለካፒታል ወጪዎች ➡️ 222,694,109,445 ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ➡️ 14,000,000,000 ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የተመደበ ነው፡፡ @tikvahethiopia
#Ethiopia

ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል።

የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል።

ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡

ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

ከነዚህም ውስጥ #ድጎማ እና #የደመወዝ_ጭማሪ የሚጠቀሱ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ወጪዎች በአመቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

IMF ሰንድ ትንበያ ምን ያሳያል ?

- የመንግስት ወጪ ቀደም ሲል ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።

- ይህንን ወጪ ለመሸፈን ከአገር ውስጥ ገቢ 1.3 ትሪሊየን ብር (1.15 ትሪሊየን ብር ከታክስ) 214 ቢሊየን ብር ከውጭ የበጀት ድጋፍ በጥቅሉ 1.52 ትሪሊየን ብር የሚገኝ ይሆናል።

- ከውጭ ከሚገኘው 214 ቢሊየን ብር ብድር እና እርዳታ አምና (2016) ከተገኘው 43 ቢሊየን ብር አንፃር በአምስት እጥፍ (500 በመቶ) ጭማሪ ይኖረዋል።

- ከውጭ ከሚገኘው የበጀት ድጋፍ በተጨማሪም ደግሞ በእርዳታ ተቋማት አማካኝነት የሚፈሰው ሃብት ሲካተትበት በጠቅላላ ወደ 304 ቢሊየን ብር ይደርሳል።

- ወጪ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው 1.8 ትሪሊየን ብር ሲሆን የበጀት ጉድለቱ 270 ቢሊየን ብር ይሆናል።

- ከጠቅላላው የመንግስት ወጪ 1.24 ትሪሊየን ብር የመደበኛ ወጪ ይሆናል። ቀሪው 557 ቢሊየን ብር የካፒታል ወጪ ይሆናል፡፡

ሰኔ መጨረሻ ለ2017 በጀት አመት ፀድቆ ከነበረው 971 ቢሊየን ብር በጀት ውስጥ 358.5 ቢሊየን ብር ወይም ከጠቅላላው በጀት 37 በመቶ የሚሆነው የበጀት ጉድለት ነበር፡፡

ሆኖም በIMF ትንበያ ወጪ ይደረጋል ከተባለው 1.8 ትሪሊየን ብር ውስጥ የበጀት ጉድለቱ ከወር በፊት ተቀምጦ ከነበረው መጠን የሚያንስ ነው፡፡

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

#Capitalnewspaper #Ethiopia #IMF

@tikvahethiopia