TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

#ቄሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ #ወጣቶች ተወካዪች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ወጣቶቹ ከም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰንደቅ አላማን ምክንያት በማድረግ የተፈጠረውን አላስፈላጊ ግጭት #አውግዘዋል

ነገ የሚደረገው አቀባበል በሰላማዊ እና በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን በትብብር ለመስራት #መስማማታቸውንም ገልፀዋል።

©አሀዱ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvaethiopia
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው‼️

#ሀላባ

#የፕሮቴስታንት እምነት ቤተክርስትያን ላይ በዛሬው ዕለት የተቃጣው ጥቃት ፍፁም የሀላባን ሕዝብና የየትኛውንም ኃይማኖቶችን #እንደማይወክል የሀላባ ዞን አስተዳዳሪ ገልፁ፡፡

ተግባሩ #የጥቂት ግለሰቦችን የግል ፍላጎት ከሟሟላት ጋር ተያይዞ የተፈፀመና ሁሉንም ኃይማኖቶች የማይወክል ሲሆን በድርጊቱ የተሳተፉና የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቀጣይ ጊዜያት ለሕግ የማቅረቡ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የተጠረጠሩ ግለሰቦችም ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የደረሰውን ማንኛውንም ጉዳት በዞኑ አስተዳደር እና ለዞኑ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ሕብረተሰብ ጭምር ከጎኑ በሚሆነው የሀላባ ሕብረተሰብ ድጋፍ እንደሚተካም አስተዳዳሪዋ ገልፀዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሀላባ ዞን ደኢህዴን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴንም ለኃይማኖት ተቋማት እና በሠላሟ ለምትታወቀው ሀላባ ሁሉም አካል ዘብ ሊቆም እንደሚገባ አሳስበው በዛሬው የፕሮቴስታንት እምነት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት በፅኑ #አውግዘዋል፡፡

ጥቃት የደረሰባቸውን የኃይማኖት ተቋማት የሀላባ ዞን አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን፣ የሀላባ ዞን ደኢህዴን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሂዲን ሁሴን፣ የሀላባ ዞን ደኢህዴን ቅ/ጽ/ቤት የከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አቶ አ/ባሲጥ አባኮ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ደኢህዴን ን/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀሩና አህመድ እና የሀላባ ዞን፣ የወረዳና የከተማ መካከለኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ጥቃቱ የደረሰባቸውን የኃይማኖት ተቋማት በቦታው ተገኝተው በመመልከት ደርጊቱንና የድርጊቱን ፈፃሚዎች በፅኑ አውግዘው የፕሮቴስታንት ኃይማኖት ተከታዮችን #አፅናንተዋል

ማንኛውም አካል በኃይማኖት ሽፋን ለሚያደርሰው ጥቃት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥና የየትኛውም ኃይማኖት ለዚህ ተግባር ሽፋን እንደማይሰጥ አውቆ ከዚህ እኩይ ተግባር እንዲቆጠብ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ደኢህዴን ን/ቅ/ጽ/ቤት አሳስቧል፡፡

Via HK sub Branch office
@tsegabwolde @tikvahethiopia