TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የበርካታ ስደተኞች ደብዛቸው ጠፋ።

ከቀይ ባሕር ዳርቻ ስደተኞች የጫነች ጀልባ ሰጥማ አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሆኑ ስደተኞች ደብዛቸው መጥፋቱን የየመን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጀልባዋ 75 ስደተኞች እንደጫነች ትላንት እሁድ መስጠሟን የየመን የባሕር ድንበር ጠባቂ ኃይል አሳውቋል።

ከስደተኞቹ መካከል 26 ሲተርፉ የቀሩት 49 ሰዎች የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።

የጠፉትን ስደተኞች ለማግኘት ዛሬ ሰኞ ፍለጋ እየተካሔደ ነው ተብሏል።

የየመን መንግሥት የሚቆጣጠረው " ሳባ " የዜና ወኪል ጀልባዋ በኃይለኛ ንፋስ ሳቢያ ስትሰምጥ #ሴቶች እና #ሕጻትን ጨምሮ የጫነቻቸው ስደተኞች ወደ ባሕር መውደቃቸውን ስማቸው ያልተጠቀሰ የየመን ባሕር ድንበር ጠባቂ ኃይል ባለሥልጣን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የተሻለ ገቢ እና የሥራ ዕድል ፍለጋ ወደ ባሕረ ሰላጤው ሀገራት ለማምራት የሚሞክሩ የአፍሪካ ቀንድ ሰዎች የጫነ ጀልባ በቀይ ባሕር ዳርቻዎች የመስጠም አደጋ ሲገጥመው የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየዓመቱ ከኢትዮጵያ፣ ከጅቡቲ እና ከሶማሊያ በየመን በኩል አድርገው ሳዑዲ አረቢያን ወደመሳሰሉ ሀገራት ለመጓዝ ጥረት ያደርጋሉ።

መረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ / አሶሼትድ ፕሬስ / ሳባ ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia