TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል ፤ ለምን ?

ባለተጠበቀ ሁኔታ የዓለማችን ከፍተኛ የነዳጅ አምራች አገራት #የነዳጅ_ምርትን_ለመቀነስ ከተስማሙ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

በዚህም የብሬንት አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በ5 የአሜሪካ ዶላር ወይም በ7 በመቶ ጨማሪ አሳይቶ ከ85 ዶላር በላይ እየተሸጠ ይገኛል።

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው የመጣው ፦ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና ሌሎች በርካታ የባህረ ሰላጤው አገራት በቀን የአንድ ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ምርት ቅነሳ እናደርጋለን ካሉ በኋላ ነው።

የምርት ቅነሳውን ያደረጉት ኦፔክ+ የሚባሉት ነዳጅ አምራች አገራት ሲሆኑ ለዓለም ገበያ ከሚቀርበው የነዳጅ መጠን 40 በመቶውን ይሸፍናሉ።

ሳዑዲ አረቢያ የቀን ምርቷን በ500 ሺህ በርሜል የምትቀንስ ሲሆን ኢራቅ ደግሞ በ211 ሺህ በርሜል የዕለት ምርቷን ትቀንሳለች። የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች፣ ኩዌት፣ አልጄሪያ እና ኦማን ሌሎች የምርት ቅነሳ የሚያደርጉ አገራት ናቸው።

ነዳጅ አምራች አገራቱ የምርት ቅነሳ ማድረጋቸውን ካሳወቁ በኋላ የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ም/ቤት “ የገበያ መረጋጋት በሌለበት በዚህ ወቅት የምርት ቅነሳ ማድረጉ የሚመከር አይደለም - ይህን ግልጽ አድርገናል ” ሲል አሳውቋል።

የሳዑዲ የኢነርጂ ሚኒስቴር ፤ የነዳጅ ምርት ላይ ቅናሽ ማድረግ ያስፈለገው " የነዳጅ ገበያ መረጋጋት ለመፍጥር የተወሰደ የቅድመ ጥናቃቄ እርምጃ ነው " ብሏል።

ናታን ፓይፐር የተባሉ የዘርፉ ተንታኝ በበኩላቸው ነዳጅ አምራቾች ምርታቸውን የቀነሱት በዓለም ምጣኔ ሃብት መቀዛዝ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በበርሜል #ከ80_ዶላር_በታች_እንዳይወርድ በማሰብ ነው ብለዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia