TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ግብፅ #ሱማሊያ

በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ የተደረገላቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።

ሁለቱ ፕሬዜዳንቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግሥት " ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ " ብላ በስምምነቱ ላይ ተቃውሞ ያሰማቸው ግብፅ ነበረች።

ከዚህም ባለፈ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት በስምምነቱ ተቃውሞ ዙሪያ ቀደመው ስልክ ከደወሉላቸው መሪዎች አንደኛው ፕሬዜዳንት አልሲሲ እንደነበሩ አይዘነጋም።

ፕሬዜዳንት አልሲሲም ከቀናት በኃላ ፕሬዜዳንቱ ወደ ኤርትራ ባቀኑበት ወቅት ግብፅን እንዲጎበኙ ጥሪ አድርገውላቸው የነበረ ሲሆን በዚሁ ጥሪ መሰረት ለሁለት ቀን ጉብኝት ትላንት ምሽት ካይሮ ገብተዋል።

ግብፅ ፤ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 የባህር በር እንዲኖራት እድልን ይሰጣል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ከተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ወዲህ ኢትዮጵያን የሚወነጅሉ አስተያየቶችን ስትሰጥ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑን " ኢትዮጵያን በአካባቢው የአለመረጋጋት ምንጭ እየሆነች ነው " የሚል ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ተናግራለች።

ኢትዮጵያም ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ለተናገረችው ንግግር በአምባሳደር መለስ አለም በኩል ፤ " ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ በአንድ ቃል ለመግለፅ #ቧልት ነው፤ የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል። " በሚል የመልስ ምት ሰጥታታለች።

@tikvahethiopia