TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ⬆️

አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን በፍቅር ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን የቅበላ ኮሚቴዉ አስታወቀ፡፡

ለአቀባበሉ የተዋቀረዉ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ አቀባበል ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል ብሏል፡፡

ታማኝ በየነ በኪነ ጥበቡ ዙሪያ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማነቃቃት፣ የመድረክ ፈርጥ ሆኖ ሌሎች ተከታዮቹን በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል፡፡

ለረጅም ዓመታት #አንድነትን#ፍቅርን#መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ ልጅ መሆኑን በተሰጠዉ መግለጫ ተገልጿል፡፡

ይህ ኢትዮጵያዊ #ጀግና ነሐሴ 26/2010 ዓ.ም በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና የሥራ ባልደረቦቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል ብለዋል። በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ ዕለት ተገኝተዉ በፍቅር እጃቸዉን ዘርግተዉ እንዲቀበሉት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደሴ ወደ ቀድሞ ሰላሟ ተመልሳለች!

#አብሮነትን እና #መቻቻልን ለመናድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ሕዝብና መንግስት በጋራ ሊከላከሉ እንደሚገባ የደሴ ከተማ የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ተናገሩ።

ካለፈው አርብ ዕለት ጀምራ ላለፉት ሁለት ቀናት አንፃራዊ የሰላም እጥረት አጋጥሟት የነበረችው ደሴ ወደ ቀድሞ #ሰላሟ ተመልሳለች፡፡

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች አብመድ ተዘዋውሮ ያነጋገርናቸው የደሴ ከተማ የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች አርብ እና ቅዳሜ የነበረው አለመረጋጋት ከዕሁድ ጀምሮ ወደ ቀደመ ሰላሙ ተመልሷል ብለዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ አቶ ከበደ ወልደ ሩፋኤል አብሮነትን እና መቻቻልን ለመናድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ሕዝብና መንግስት በጋራ ሊከላከሉ ይገባል ብለዋል፡፡

ሰላም #ከሁሉም በላይ ነው፤ ሰላም ከሌለ ሃገር፣ ቤትና ርስት ትርጉም የላቸውም፤ ስለዚህ ወጣቱ ለግጭት ምክንያት የሚሆኑ አሉባልታዎችን በማስተዋልና በማገናዘብ ሊመረምር ይገባል ነው ያሉት አቶ ከበደ፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪ ሼህ በሽር አሊ ‹‹ደሴ የሃይማኖት መከባበርንና መቻቻልን ለዘመናት ያፀናች ከተማ ናት›› የቆየውን እሴትና አብሮነት የሚሸረሽሩ ድርጊቶች አልፎ አልፎ የ ስለሚስተዋሉ ማረም ይገባል ብለዋል፡፡ ‹‹ተዛምደናል፣ ተጋብተናል፤ ተዋልደናል፤ እናም ሊለያይ የማይችለውን አንድነት መጠበቅ አለብን ነው ያሉት።

‹‹አንዱ በሌላው ላይ መነሳት የፈጣሪም ሆነ የደሴ ከተማ መለያ እና አስተምህሮ አይደለም›› ያሉት የመካነ ኢየሱስ ሰላም ማህበረ ምዕመናን መሪ እና የደሴ ከተማ የሃይማኖት ፎረም ፀኃፊ ቄስ መስፍን ጌታሁን ድብቅ ዓላማ በመያዝ የሚንቀሳቀሱ እና ለጥፋት ምክንያት የሚሆኑ አካላትን መንግስት እየለየ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ ሼህ ሰኢድ ዑመር ግዛቸው ደግሞ የከተማዋ የሃይማኖቶች ፎረም በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለይቶ ከመፍታት በዘለለ የቀደመውን አብሮነትና መቻቻል ለመመለስ እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡

"አልፎ አልፎ በከተማዋ የሚስተዋሉ ግጭቶች ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮች ናቸው ቢባሉም ሃይማኖታዊ ዝንባሌ ለማስያዝ የሚጥሩ አሉ" ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደሴ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ፀኃፊ እና የሃይማኖት ፎረም ሰብሳቢ መምህር ከተማው ኃይሌ ናቸው። ችግሩን ለይቶ አስተዳደራዊ እርምት በመውሰድ ለቀጣይ ስጋት እንዳይኖር ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት። "የሃይማኖት አባቶች ሽምግልና እና አስተምህሮ ይቀጥላል፤ የሃይማኖት ፎረሙም በቀጣይ እየተሰበሰበ ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ይሰራል" ብለዋል መምህር ከተማው፡፡

ግጭት በሚስተዋልባቸው ቦታዎች ላይም በግለሰብ እጅ ሊያዙ የማይገባቸው የጦር መሳሪያዎች ተስተውለዋል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ መንግስት የሕዝብን ደኅንነት ለመጠበቅ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሰራም አሳስበዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia