TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዋጋ ንረት . . . #ኢትዮጵያ

" አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና #ጠንካራ ሆኖ ቀጥሏል " - አቶ አህመድ ሽዴ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ረቡዕ ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን እና ታጠሪ ተቋማትን የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ፥ በመጋቢት ወር አገራዊው አጠቃላይ የፍጆታ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት 33.7 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።

የምግብ ነክ ዋጋ ንረት 34.5 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ዋጋ ንረት 32.5 በመቶ ደርሷል ሲሉ አመልክተዋል።

አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና ጠንካራ ሆኖ መቀጠሉን ያሳያል ብለዋል።

" ይህም በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚያሳድር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ምን አደረጋችሁ ?

አቶ አህመድ ሽዴ ፦

- የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ዘንድሮ የብር 17 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል።

የማዳበሪያ ዋጋ በተለይ በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ያለው ዋጋ እድገትን ተከትሎ የማዳበሪያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ነው ያደገው።

ይህም አንደኛ የውጭ ምንዛሬ ጫና በከፍተኛ ደረጃ አስከትሏል በሀገር ደረጃ። ሁለተኛ ሙሉ በሙሉ በብር ተመንዝሮ ወደ ገበሬው ይተላለፍ ቢባል የገበሬውን የመግዛት አቅም ታሳቢ በማድረግ ጫናው ከፍተኛ መሆኑ በመንግስት ታምኖበት 17 ቢሊዮን ብር ከበጀት ፀድቆ ድጎማ አድርገናል።

- ለአፈር ማዳበሪያ መግዣ ለክልሎች ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር 56.7 ቢሊዮን ዋስትና ተሰጥቷል።

በየክልሉ ያሉ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲቀርብላቸው ለማድረግ በክልሎቹ በቀረበ ጥያቄ 56.7 ቢሊዮን ብር ዋስትና ተሰጥቷል።

- #ነዳጅ ላይ አሁንም መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየደጎመ ነው ያለው። ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ተደጉሟል ባለፉት ዓመታት ፤ ዘንድሮም ያለው ከፍተኛ ነው ፤ ደረጃ በደረጃ ከአጠቃላይ ድጎማ ወጥተን ወደ targeted subsidy የመግባት ስራው ከአንድ ዓመት በላይ እየተሰራ ነው። መሉ በሙሉ ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት እየተሰራ ያለው ስራ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ነው።

- መንግሥት በ97 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር 43 ሚሊዮን ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ለመግዛት ውል ገብቷል። ከዚህ ውስጥ በ33.8 ሚሊዮን ዶላር 15 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከውጭ ተገዝቶ ወደ ሀገር ገብቷል።

- የሡፍ የምግብ ዘይት አቅርቦትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው።

- ዘይት፣ ሩዝ፣ ስኳር፣ ከውጭ ሲገቡ ሆነ በሀገር ሲመረቱ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ታደርገዋል። የዋጋ ንረቱ ከዚህም ከፍ እንዳይል እያገዘ ነው።

- ለሀገር ውስጥ አምራቾች ከለላ ለመስጠት መኮሮኒ እና ፓስታ #ከተጨማሪ_እሴት_ታክስ ነፃ ታደርጓል። ይሄም የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ለማድረግ ታልሞ የተሰራበት ነው።

- መሰረታዊ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት መንግሥት ብር 11.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ሳይሰበስብ ቀርቷል። ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉት መግባታቸው የዋጋ ንረቱ ከዚህ በላይ እንዳይባባስ ጥሩ ሚና አለው።

... በማለት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ወስደናቸዋል ስላሏቸው እርምጃዎች አስረድተዋል።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia