TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update "የአንበሳ ስጋ ሰረቀ ተባልኩ"

ዶ/ር ሙሴ ክፍሎም⬇️

ባለፈው ቅዳሜ የአንበሳ ግቢ በመሄድ እንስሳዎቹ ያሉበትን አሳዛኝ ሁኔታ ከተመለከን በኀላ በቅርቡ ከስራቸው የተሰናበቱትን ዶ/ር #ሙሴ_ክፍሎምን ዛሬ ቢሮዋቸው ሄጄ አነጋግሬአቸው ነበር።

ይህንን ነገሩኝ፦

-በሁለት አመት ውስጥ 7 አንበሳ ሞተ የተባለው ፈፅሞ ስህተት ነው። ይኸው ዶክመንታቸውን ባሳይህ ባለፈው 5 አመት ውስጥ አምስት አምበሳ ነው የሞተው... አብዛኞቹ በእድሜ እና አንዱ በህመም።

-አንበሶቹ ከሱ ለተባለው፤ በፊት በሳምንት እስከ 300ኪግ ስጋ ይገባ ነበር። ብዙው ግን ተርፎ ይበላሻል ስለዚህ በእንስሳት አመጋገብ ባለሙያዎች አስጠንተን በቀን ለአንድ አምበሳ 7ኪግ እየሰጠን ነው። ምናልባት የባለሙያዎቹ ግምት ስህተት ከሆነ ብለን ጉዳዩን እያየነው ነበር።

-ፒኮክ የሚገኘውን እና 91 ሚልዮን ብር የጨረሰውን አዲስ የአንበሳ ግቢ ለማጠናቀቅ 3 እና 4 ወር ሲቀረን እኔን ካለ በቂ ማጣራት #ለማባረር መፈለጉ #አልገባኝም። ክሬዲቱን ለማን ለመስጠት ነው?

- ሚድያዎች ዘመቻ አርገውብኛል። እኔ ሸገርን (ወ/ሮ መአዛ ብሩን ጨምሮ) ኑ ዶክመንት ተመልከቱ ብላቸው ማንም አልሰማኝም። በሁዋላ ግን የአንበሳ ስጋ #ሰረቀ ተባልኩ።

© AP - Elias Meseret Taye
@tsegabwolde @tikvahethiopia
JiT👆

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የዓመቱ የማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥብት ቀን #ይራዘምልን በማለት ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። ተማሪዎቹ ፦ "ፊርማ አሰባስበን የፈተናው ቀን እንዲራዘም ብንጠይቅም ተቋሙ ጥያቄያችንን ወደኃላ በማለት በአቋሙ ፀንቷል፤ ብዙ portion ያልጨረስን በመሆኑ ተማሪውን ከግቢ #ለማባረር የተጠነሰሰ ሴራ ነው" ብለን እናምናለን ሲሉ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከJiT አመራሮች የሚሰጥ #ምላሽ ካለ ተከታትዬ የማቀርብላችሁ ይሆናል። #JiT
@tsegabwolde @tikvahethiopia