TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስሎቬኒያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ #ማብቃቱን አወጀች!

የስሎቬንያ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ማብቃቱን በይፋ አወጀ። ሀገሪቱ ወረርሽኙ (ኮቪድ-19) ማብቃቱን ያወጀች #የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ሀገር ሆናለች።

የሀገሪቱ መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ባለፉት 2 ሳምንታት ከ7 በታች አዲስ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ መመዝገቡን ተከትሎ ነው ተብሏል።

#NIPH የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መቀነስ አሳይቷል ፤ ባለፉት 14 ቀናት የተመዘገበው 35 ኬዝ ብቻ ነው ብሏል።

ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ወደ ስሎቪኒያ የሚገቡ ሰዎች ከዚህ በኃላ ኳራንታይ መግባት አይጠበቅባቸውም ተብሏል።

ከአውሮፓ አባል ሀገራት ውጭ የሚመጡና የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች የሚታይባቸው የውጭ ዜጎች ግን ለ14 ቀናት ኳራንታይ መግባት ይጠበቅባቸዋል።

የስሎቪኒያ መንግስት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ማብቃቱን ይፋ ቢያደርግም አሁንም በሽታው የመሰራጨት እድል ስላለው የመከላከል እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

እስሁን ድረስ በስሎቬኒያ 1,465 ሰዎች በቫይረሱ መያቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መኃል 103 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 270 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia