TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ፀሀይ_ባንክ

ፀሀይ ባንክ ቅዳሜ ሀምሌ 16/2014 በይፋ ስራውን እንደሚጀምር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ባንኩ በ2.9 ቢሊዮን የተፈረመ ካፒታልና በ734 ሚሊዮን በስራ ላይ የዋለ ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን ዝቅተኛ የአክሲዮን ግዢውን ብር 100 ሺህ በማድረግ በ373 ባለአክሲዮኖች የባንክ ኢንዱስትሪውን ተቀላቅሏል፡፡

ምን ይዞ መጥቷል ?

👉 የባንኩ ዓላማ የባንክ ኢንዱስትሪውን
መቀላቀል ብቻ ሳይሆን ፤ በፋይናንስ ዘርፉ በቂ ትኩረት ያላገኙትን የጥቃቅንና አነስቸኛ ፤ ግብርናውን ዘርፍ ፤ የአምራች ኢንዱስትሪውን እንዲሁም አዋጪ ለሆኑ #የፈጠራ_ስራዎች እና #ስራ_ፈጣሪዎች ተደራሽ መሆንና ለሁሉም የሆነ ባንክ ሆኖ አዳዲስ ስልቶችን በመንደፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ቀልጣፋና ደንበኛ ተኮር የሆነ አገልግሎት ለመሥጠት መሆኑን አሳውቋል።

👉 የባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማዘን ዘመኑን የዋጀ መደበኛውን የባንክ አገልግሎት እና ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን በማቅረብ በኢንዱስትሪው ውስጥ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን፤ የተሻለ የባክ አገልግሎት ይዞ በመግባት ለሁሉ የሚያገለግል ባንክ እንደሚሆን ገልጿል።

👉 ስራ ሲጀምር ከሕብረተሰቡ የሚሰበሰበውን ከፍተኛ ሆነ ሃብት መልሶ የሕብረተሰቡን ህይወት ለሚያሻሻልና ልማቱን ሊያፋጥን ለሚችሉ ስራዎች እንዲውል ትኩረት ሰጥቶ እደሚሰራ ገልጿል።

👉 በባንኩ የምረቃ ዕለት በ30 ቅርንጫፎች በመጀመርና በቅርብ ቀን የቅርጫፎቹን ቁጥር ከ50 በላይ እንደሚያሳድግ የገለፀ ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ 100 ቅርንጫፎችን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ለክፈት የሚያስችለውን ስራ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia