TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች
~ ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት

አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን፤ ስልክ 0979099909/ 0911039377

በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
#ኬንያ

በጎረቤት ኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ አንድ ሰው ተገደለ።

የኬንያ ተቃዋሚው ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ የኑሮ መወደድን እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገው ደጋፊዎቻቸው ዛሬ ሰኞ መጋቢት 11/2015 ዓ.ም. ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጡ ጠርተው ነበር።

የኬንያ መንግሥት የተቃውሞ ሰልፉ ሕገወጥ እና ያልተፈቀደ ነው ቢልም፣ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ውስጥ በአንስተኛ ደረጃ ወደ ጎዳና የወጡ ተቃዋሚዎች ታይተዋል።

ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን ከፍተኛ ኃይል ያለው ውሃ እና አስለቃሽ ጋዝ የተጠቀመ ሲሆን፣ እስካሁን አንድ ሰው ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መሞቱ ተዘግቧል።

የተቃዋሚ ፓርቲው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት ክሳቸውን ውድቅ ቢያደርገውም ባለፈው ዓመት ነሐሴ የተካሄደው ምርጫ ተሰርቋል የሚለውን ክሳቸውን አሁንም እያቀረቡ ነው።

በተጨማሪም ሥልጣን ከያዘ ስድስት ወራትን ያስቆጠረው የዊሊያም ሩቶ መንግሥት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ያለውን የኑሮ ውድነት መፍትሄ ሊያበጅለት አልቻለም በማለት ደጋፊዎቻቸውን ለአደባባይ ተቃውሞ ጠርተዋል።

በተለይ ኦዲንጋ ከፍተኛ ደጋፊ ባላቸው የናይሮቢ የድሆች መኖሪያ በሆነው ኪቤራ አካባቢ ፖሊሶች ከተቃዋሚዎች ጋር ተጋጭተዋል።

በማዕከላዊ ናይሮቢ የሚገኙ የንግድ ተቋማትም የፀጥታ ችግሩን በመፍራት ዝግ ሆነው አስከ እኩለ ቀን ድረስ የቆዩ ሲሆን፣ ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጋዝ በትነዋል።

በማዕከላዊ የከተማዋ ክፍል ውስጥ በሚገኘው የኬንያታ ጎዳና ላይም አንዳንድ ተቃዋሚዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ መታየታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" የተዘረፍነው ካሜራን ጨምሮ ሙሉ ንብረቶቻችንን ነው " - ጋዜጠኛ ሙልጌታ አንበርብር

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ በኦንላይ ሚዲያ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው " ኢትዮ 251 " ሚዲያ ካሜራን ጨምሮ ሙሉ ንብረቶቹን እንደተዘረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ሚዲያው ዘረፋው የተፈጸመው ትናንት ዕሁድ መጋቢት 10/2015 ዓ/ም መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮ 251 ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር ለቲክቫህ በላከው መልዕክት " ዘረፋው ጠንካራ ጥበቃ ባለውና መሐል አራት ኪሎ ድንቅ ሥራ ኮምፕሌክስ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ ስቱዲዮ ነው የተፈፀመው። " ብሏል።

በዘረፋው የድርጅቱ መገልገያ የነበሩ ፦
- አራት ዘመናዊ ካሜራዎች፣
- ኔክማይክ፣
- ዙመር እና ሌሎችም መገልገያ ቁሳቁሶች ተዘርፈው ተወስደዋል ሲል አመልክቷል።

ቁሳቁሶቹ ከ "ኢትዮ 251" በተጨማሪ፤ " አራት ኪሎ ሚዲያ " እና "ነገረ ወልቃይት "ን የመሳሰሉ ሚዲያዎች የሚገለገሉባቸው እንደነበረም ገልጿል።

" የፕሮዳክሽን እቃዎቹን ትናንት እሁድ ዕኩለ ቀን ድረስ ስንሰራባቸው ነበር " ያለው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ " የተዘረፉት ንብረቶች አጠቃላይ ዋጋ ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን (1,700,000) ብር በላይ የሚገመት ነው " ሲል አስረድቷል።

" የተከራየንበት ህንፃ ድንቅ ሥራ ኮምፕሌክስ ላይ ሁለት ባንኮችን ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ድርጅቶች ለዓመታት እየሠሩ ያለ ቢሆንም አንዳቸውም ሊዘረፋ ቀርቶ ሙከራ እንኳ ተደርጎባቸው እንደማያውቅ ባደረግነው ማጣራት አረጋግጠናል " ያለው ጋዜጠኛው " ስምንተኛ ፎቅ ድረስ በመውጣት የሚዲያ ተቋምን መዝረፍ የሕዝብ ድምፅ በሆኑ በሚዲያ ላይ የተቃጣ ጥቃት በመሆኑ፣ እንደ ቀላል የሚታይ ጉዳይ አይደለም " ብሏል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከባድ ያለ ዝናብ የጣለ ነው።

ዛሬም በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ጥሏል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆናችሁ አሽከርካሪዎች በዚህ ወቅት ስታሽከረክሩ የአየር ሁኔታውን ታሳቢ አድርጋችሁ እንዲሆን አደራ እንላለን።

ወላጆችም ልጆቻችሁን ጠብቁ። በተለይም ደግሞ ወቅቱ የትምህርት ሰዓት እንደመሆኑ ከቤት ወደ ከትምህርት ቤት ሲሄዱና ሲወጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ልጆቻችሁን አሳስቡ። የአየር ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ የሚደረብ ልብስም እንዲይዙ አድርጉ።

የትምህርት ተቋማት በዚህ በዝናብ ወቅት ለልጆች ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉላቸው።

በአጠቃላይ ውድ የአ/አበባ ቤተሰቦቻችን በተለይ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ያላችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንላለን።

በአዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተዘረፍነው ካሜራን ጨምሮ ሙሉ ንብረቶቻችንን ነው " - ጋዜጠኛ ሙልጌታ አንበርብር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ በኦንላይ ሚዲያ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው " ኢትዮ 251 " ሚዲያ ካሜራን ጨምሮ ሙሉ ንብረቶቹን እንደተዘረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። ሚዲያው ዘረፋው የተፈጸመው ትናንት ዕሁድ መጋቢት 10/2015 ዓ/ም መሆኑን ገልጿል። የኢትዮ 251 ሚዲያ ባለቤትና…
ሌላ ዝርፊያ ...

" ከድርጅታችን 250 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ተዘርፏል " - ጋዜጠኛ ሚኪያስ ጌታቸው

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ በኦንላይን የሚንቀሳቀሰው " ዩሪካ ቲቪና ሬድዮ " ከቢሮው 250 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት እንደተዘረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ድርጅቱ ዝርፊያው የተፈፀመበት አራት ኪሎ ከሚገኘው " ተስኒም ህንፃ " 5ኛ ፎቅ መሆኑን አመልክቷል።

ዩሪካ ቲቪና ሬድዮ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሚኪያስ ጌታቸው  " ሁለት Canon Camera Body ፣  ሶስት Canon Camera Lens እና አንድ laptop አሁን ባለው የገበያ ዋጋ አጠቃላይ ግምታቸው 250ሺህ ብር የሚደርስ ንብረት አራት ኪሎ ከሚገኘው ተስኒም ህንፃ 5ኛ ስቱዲዮችን ተዘረፏል " ብሏል።

ዘረፋው እንደ ተፈጸመው የታወቀው ትናንት ዕሁድ መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ከቀኑ 7:20 ሰዓት ላይ እንደነበር ገልጾልናል።

" አርብ መጋቢት 8 የዕለቱን ስራችን አጠናቀን ከቢሮ ወጣን። በንጋታው ቅዳሜ ስለሆነ ስራም ስላልነበረን ቢሮ አልገባንም። ከአርብ 11:00 ጀምሮ እስከ እሁድ 7:00 ድረስ እኔም ሆንኩ ባልደረቦቼ ቢሮ አልገባንም። እሁድ ዕለት ግን ለሰኞ ማስረከብ ያለበትን ስራ ለማጠናቀቅ አንደኛው የኤዲቲንግ ባለሙያ ቢሮ በገባበት ወቅት ነው ዝርፊያ መፈፀሙን ያወቅነው " ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

ጋዜጠኛ ሚኪያስ ጌታቸው በነገው ዕለት በራሱ " ዩሪካ ቲቪና ሬድዮ " የዩትዩብ ገፅ ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጿል።

በዛው 4 ኪሎ አካባቢ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ በኦንላይ ሚዲያ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው " ኢትዮ 251 " ሚዲያ ካሜራን ጨምሮ ሙሉ ንብረቶቹን (ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት) እንደተዘረፈ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በካሽ ጎ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት ሲልኩ ምንም ሳይሸራረፍ እንደ አደራ እቃ በአስተማማኝነት እና በፍጥነት ይደርሳል።

ቪዛ ወይም ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው በካሽጎ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

ነፃ፣ ምቹ እና ቀላል፡፡ የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች 👇
https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306
#CashGo #visa #mastercard #የሁሉም_ምርጫ
#ዶክተር_ተወልደብርሃን_ገብረእግዚአብሔር

የአካባቢ ጉዳይ ተመራማሪ ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር  ማን ነበሩ ?

- ከአባታቸው ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ መዓዛ ወልደመድህን በትግራይ ክልል፣ ዓድዋ  ርባገረድ መንደር በ1932 ዓ/ም ነው የተወለዱት።

- የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በንግስተ ሳባ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዊንጌት ተምረዋል፤ 1959 ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ወደ ቀዳማይ ኃላይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ  / በኃላ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

- በአካባቢ ጉዳይ ላይ ለዓለም የሚጠቅም ተጠቃሽ ሥራዎችን ሰርተዋል።

- በብዝሐ ሕይወት ፣ በማሕበረሰብ (የአርሶ አደሮችን መብት) ማስከበር እና በዘረመል ምሕንድስና በሚመረት እህል ላይ ያደረጓቸው ምርምሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናና ሽልማት አስገኝቶላቸዋል።

- ካገኟቸው ከዓለም አቀፍ ሽልማታቸው መካከል " የአማራጭ የኖቤል ሽልማት " እና " የምድራችን ጀግና " በሚል ሲንጋፖር ላይ በፈረንጆቹ 2006 ላይ የተሸለሙት ይጠቀሳሉ።

- ሕይወታቸው እስከአለፈበት ድረስም አዲስ አበባ ይኖሩ እንደነበር።

- ዶ/ር ተወልደብርሃን በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

- ዶክተር ተወልደ ብርሃን የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ፡፡ እንዲሁም ከ60 በላይ ሌሎች ልጆችን አሳድገዋል፡፡

Credit : #ኤፍቢሲ #ኤኤምሲ

@tikvahethiopia
" ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የጦር ወንጀሎችን ፈፅመዋል " - አንቶኒ ብሊንከን

አሜሪካ በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተዛመተው ጦርነት ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የጦር ወንጀሎች ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሷን አሳውቃለች።

ይህንን ያሳወቀችው ትላንት በውጭ ጉዳይ ቢሮዳ በኩል የአገራትን የሰብዓዊ መብቶች ይዞታን በተመለከተ የሚያደርገው ግምገማ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ ስታደርግ ነው።

ሪፖርቱን ይፋ ያደረጉት በቅርቡ አዲስ አበባ መጥተው ከፌዴራል እና ከህወሓት አመራሮች ጋር መክረው የተመለሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ናቸው።

ብሊንከን ምድነው ያሉት ?

- የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ ጦር፣ የህወሓት ኃይሎች እና የአማራ ኃይሎች የጦር ወንጀሎች ፈጽመዋል።

- ከጦር ወንጀሎች በተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ ጦር እና የአማራ ኃይሎች ግድያዎችን፣ መድፈር እና አስገዳጅ ስደትን ጨምሮ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ፈጽመዋል።

- የአማራ ኃይሎች አባላት በምዕራብ ትግራይ አስገዳጅ ማፈናቀል እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈፅመዋል። 

- እነዚህ ወንጀሎች ብዙዎቹ በዘፈቀደ ወይም በጦርነት ውስጥ የተከሰቱ ሳይሆን ሆን ተብለው ታስበው የተፈጸሙ ናቸው።

- ይህን ድምዳሜ ያስተለለፍነው መረጃዎችን መርምረን ነው፤ ይህ ድምዳሜ በአሜሪካ ፖሊሲ ላይ ወዲያውኑ የሚያስከትለው ለውጥ አይኖርም። ወንጀሎቹን የፈጸሙ አካላት ግን ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።

- ሁሉም ወገኖች ለፈጸሙት ግፍ እውቅና መስጠት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ወሳኝ እርምጃ ነው። በኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡትን ጨምሮ ጥሰቶቹን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።

ብሊንከን ከሰሞኑን በነበራቸው የኢትዮጵያ ቆይታ ወቅት ከፌዴራል እና ከህወሓት ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ገልጸዋል።

ይህንን በተመለከተ እንዲህ ብለዋል ፦

" ሁለቱም ወገኖች ግጭትን በዘላቂነት ለመፍታት በደረሱት ስምምነት ላይ እና በአተገባበሩ ላይ ስለደረሱበት ጉልህ መሻሻል አመስግነናቸዋል።

ስምምነቱን ተከትሎ ጦርነቱ ቆሟል፤ ሰብዓዊ እርዳታን እየገባ ነው ፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችም እየተመለሱ ነው፤ የኤርትራ ኃይሎች እየወጡ ናቸው።

ሆኖም ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ሁሉም ወገኖች ለፈጸሟቸው ግፎች እውቅና መስጠት አለባቸው ከዕርቅ ጋር ተጠያቂነት ሊመጣ ይገባል፤ ይህን ከባለስልጣኖች ጋር ተነጋግሬያለሁ።

ተፋላሚ ወገኖች ለተፈጸሙ ጥሰቶች ተጠያቂነት ለማስፈን የገቡትን ቁርጠኝነትም በበጎ የምንመለከተው ነው።

ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ መንግሥት መጠነ ሰፊ ጥሰት ከተፈጸመባቸው አገራት ተሞክሮን በማጎልበት የሸግግር ፍትህ አማራጭን በማምጣት የመጀመሪያ እርምጃ ወስዷል።

የሽግግር ፍትህ ሁሉን አካታች፣ ተዓማኒ እና በተለይም የተጎጂዎች ደምጽ የሚሰማበት መሆን ያስፈልጋል።

ተጠያቂነት፣ እርቅ እና መግባባት ማምጣት በኢትዮጵያ ለዓመታት የቆየውን የጥቃት አዙሪት ለመስበር ቁልፍ ነው፤ አሜሪካ በዚህ ሂደት አጋር ትሆናለች። "

በሌላ በኩል ፦ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በጦርነቱ የተፈጸሙ ጥሰቶችን በሚያጣራው የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያ ቡድን ዛሬ መጋቢት 12/ 2015 ዓ.ም ገለጻ ይቀርብለታል ተብሏል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia