TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአሜሪካ ወረራ ...

የቀድሞ የአሜሪካ መሪ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ እሁድ 20 ዓመት ደፈነ።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ 20 ዓመት ሞልቶታል።

የዛሬ 20 አመት ጦርነቱ ሲጀመር አስደንጋጭ እና አስፈሪ የቦምብ ጥቃት ዘመቻ ባግዳድን አቀጣጥሏት ነበር።

በዚህ ወረራ የአሜሪካ ጦር በስልጣን ላይ የነበረውን የሳዳም ሁሴን መንግስት አፍርሶ ሳዳምን ከስልጣን አውርዷል።

ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ እ.አ.አ ግንቦት 1 ቀን 2003 ዓ.ም ተልዕኳቸው መጠናቀቁን ቢያውጁም የሳዳም ባቲስት ፓርቲ አባላት እና ሌሎች አማፂያን ከአሜሪካ እና አጋር ኃይሎቿ ጋር ውጊያ በመቀጠላቸው ጦርነቱ ሊረዘም ችሏል።

ለወረራው ምክንያት የነበረው በኢራቅ አለ የተባለው " የጅምላ ጨራሽ ጦር መሳሪያ " ሲሆን ይህ ግን በኢራቅ አልተገኘም።

በአሜሪካ ወረራ እና እሱን ተከትሎ በቀጠለው ጦርነት የኢራቅ ነዋሪዎች ክፉኛ ዋጋ ከፍለዋል፤ በርከታ የአሜሪካ ወታድሮችም በጦርነቱ ህይወታቸው ጠፍቷል፣ አካላቸው ጎድሏል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂም ስታይንበርግን ጨምሮ በርካታ ተቺዎች አሜሪካ በኢራቅ ውስጥ ያደረገችውን ጣልቃ ገብነት / ወረራ " ጥበብ የጎደለው " ብለውታል።

ፕሬዝዳንት ኦባማ እ.አ.አ በ2011 የጦር ኃይላቸውን ከኢራቅ አስወጥተው የነበረ ቢሆንም ከሶስት አመት በኃላ ግን በኢራቅ ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ የተነሳውን አይኤስ ለመዋጋት በድጋሚ ገብተዋል።

ዛሬ የአሜሪካ ወታደሮች በኢራቅ የሚገኙ ሲሆን ግንኙነታቸው እ.አ.አ በ2003 እንደነበረው በጠላትነት ሳይሆን በቁልፍ አጋርነት መሆኑ ነው የሚነገረው።

በኢራቅ ጦርነት ምክንያት ህፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንን ጨምሬ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን ህይወት የጠፋ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ የአሜሪካ ወታደሮችም ተገድለዋል።

መረጃ ምንጭ ቪኦኤ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካ ወረራ ... የቀድሞ የአሜሪካ መሪ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ እሁድ 20 ዓመት ደፈነ። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ኢራቅን ለመውረር ትዕዛዝ ከሰጡ ዛሬ 20 ዓመት ሞልቶታል። የዛሬ 20 አመት ጦርነቱ ሲጀመር አስደንጋጭ እና አስፈሪ የቦምብ ጥቃት ዘመቻ ባግዳድን አቀጣጥሏት ነበር። በዚህ ወረራ የአሜሪካ ጦር በስልጣን ላይ የነበረውን የሳዳም ሁሴን መንግስት አፍርሶ ሳዳምን ከስልጣን…
#ኢራቅ

ዛሬ የቀድሞ #የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ቡሽ ኢራቅ ላይ ወረራ እንዲፈፀም ካዘዙ 20 ዓመት የሞላው ሲሆን በወቅቱ ለወራር ምክንያት የተባለው ኢራቅ ውስጥ አለ የተባለው የጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያ ነው።

ነገር ግን ይህ " አለ " የተባለው የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አልተገኘም።

እኤአ በ2003 ወረራው ከመፈፀሙ ከወራት በፊት በወቅቱ የኢራቅ ፕሬዜዳንት የነበሩት እና ከወራራው በኃላ #በስቅላት የተገደሉት ሳዳም ሁሴን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ (መስከረም 19/2002) ላይ እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር ፦

" ኢራቅ ከኒውክሌር፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል መሳሪያዎች ሁሉ የጸዳች መሆኗን ከዚህ በፊት አውጃለሁ።

#የአሜሪካ_አስተዳደር የመካከለኛው ምስራቅን ዘይት ለመቆጣጠር ኢራቅን ለማጥፋት ይፈልጋል ፤ ይህን ተከትሎ ፖለቲካውን እንዲሁም የመላው ዓለምን የዘይት / ነዳጅ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ይቆጣጠራል። "

@tikvahethiopia
" አደጋው አስደንጋጭ ድንገተኛ ክሰተትና መላው የተቋሙን ማህበረሰብ መሪር ሃዘን ላይ የጣለ ነው " - ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ

4 የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

ትላንት መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ/ም በደረሰ የመኪና አደጋ 4 የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ስለ አደጋው ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም አደጋው እጅግ በጣም አስደንጋጭ ድንገተኛ ክስተትና መላው የተቋሙን ማህበረሰብ መሪር ሃዘን ላይ የጣለ ነው ብሏል።

ተቋሙ በመኪና አደጋ ህይወታቸው እንዳለፈ ካሳወቃቸው ተማሪዎች ሶስቱ የሶስተኛ ዓመት ተማሪዎቹ አንዱ ደግሞ የአራተኛ አመት ተማሪ መሆኑን ገልጿል።

ስማቸውም ደሳለው ፈጠነ (ከተፈጥሮ ሃብት አያያዝ) ፣ በላይ አንዱዓለም (ከተፈጥሮ ሃብት አያያዝ) ፣ አቸነፍ አሰፋ (ከአግሮ ቢዝነስ) ፣ በላቸው አሳየ (ከአግሮ ቢዝነስ) መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " እናት እና ልጅን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል " በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት በጣለው ዝናብ እናት እና ልጆችን ጨምሮ አራት ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል። ትናንት ምሽት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከምሽቱ 12:05 ሰዓት በንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ማንጎ ሰፈር ወንዝ ዳርቻ ላይ በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ጎርፍ…
" የአራቱም ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል " - የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ " ማንጎ ሰፈር " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ #እናት እና #ልጅን ጨምሮ 4 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸዉን ተከትሎ የአስክሬን ፍለጋ ሲደረግ ውሏል።

በዚህም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የዋናተኛ ቡድን የአራቱንም ሰዎች አስከሬን ማግኘት እንደቻለ ኮሚሽኑ አሳውቋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሟቾቹን አስከሬን ለማግኘት በተደረገዉ ጥረት ለአካባቢዉ ማህበረሰብና ለጸጥታ ሀይሎች ምስጋናዉን አቅርቧል።

#ሰሞኑን_እየጣለ_ባለዉ_ዝናብ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም ህብረተሰቡ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

ምንጭ፦ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

@tikvahethiopia
" ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አልጠራሁም " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የጠራው ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ሊሰጥ በታሰበው የመውጫ ፈተና ዙሪያ ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስሙ የተሰራጨው መረጃ ህብረቱን የማይወክል መሆኑን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

በዚህ ዓመት እንዲሰጥ በተወሰነው የመውጫ ፈተና ላይ ተማሪዎች በሚያነሷቸው ስጋቶችና ቅሬታዎች ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች መደረጋቸውን ወደፊትም እንደሚደረጉ ህብረቱ ገልጿል።

በውይይቶቹ የተነሱ ሀሳቦች ገሚሶቹ ምላሽ ያገኙ ሲሆን በቀጣይ የሚስተካከሉ መረጃዎችን የሚያሳወቅ መሆኑንም ህብረቱ ጠቁሟል።

ፈተናው የተማሪዎችን ብቃት የሚመዝንና የትምህርት ጥራት ሊያስጠብቅ በሚችልበት ሁኔታ ላይ አሁንም በጋራ እየሠራ መሆኑን ህብረቱ አስታውሷል።

ተማሪዎች በፈተናው እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሀሳብ በግቢያቸው ለሚገኙ የተማሪዎች ህብረት እያቀረቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አማካይነት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመወያየት ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑንም ገልጿል።

በቅርቡ የተሰራጨው መረጃ ህብረቱን የማይወክልና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ህብረቱ፤ በህብረቱ የተጠራ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

ተመራቂ ተማሪዎች በተቋሞቻቸውና በተማሪዎች ህብረት አማካይነት የሚሰጡ የድጋፍ ትምህርቶችን በመከታተል ለመውጫ ፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ህብረቱ ጥሪ አድርጓል።

ሐሰተኛና የተዛባ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ህብረቱ አሳስቧል።

More : @tikvahuniversity
#Commercepal

ለነጋዴዎች በሙሉ፣ አዲሱና ዘመናዊውን የኮሜርስፓል የመገበያያ መድረክ በመጠቀም ማንኛውንም ምርት በቀላሉ ይሽጡ።

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡

1. የግብር ከፋይ ምዝገባ ቁጥር (TIN Number)
2. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ
3. ስልክ ቁጥር

በ 9491 የነፃ መስመር በመደወል ይመዝገቡ!

App Store:
https://apps.apple.com/us/app/commercepal/id1669974212

Play Store: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.commercepal

Visit our website: https://commercepal.com/browse
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ //t.iss.one/CommercePal_et
#HailemariamDessalegn

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ " የታንዛኒያ ፕሬዜዳንታዊ የምግብ እና ግብርና/እርሻ አቅርቦት ምክር ቤት " አባል ተደርገው መሾማቸውን ገለፁ።

አቶ ኃይለማርያም የምክር ቤቱ አባል ተደርገው የተሾሙት በታንዛኒያ ፕሬዜዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ነው።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የምክር ቤቱ አባል ተደርገው በፕሬዜዳንት ሳሚያ ሱሉሁ በመሾማቸው ክብር እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

ታንዛኒያ የግብርና ውጤቶቿን / ምርቷን ለገበያ ለማቅረብ እንዲሁም አነስተኛ እርሻን ለመለወጥ ያላት አቅም በጣም ትልቅ መሆኑን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ  አመልክተዋል።

#ምክርቤቱ : ከጥር 25 እስከ 27 ቀን 2023 በሴኔጋል ዳካር የአፍሪካ የምግብ ምርትን አስመልክቶ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ (የዳካር 2ኛው የምግብ ጉባዔ - አፍሪካን መመገብ ፣ የምግብ ሉዓላዊነት እና ፅናት) ላይ የተላለፈውን የውሳኔ ሃሳብ ማለትም  እያንዳንዱ ሀገር ግብርናን ለማስፋፋት እና የምግብ አቅርቦትን ለማሳደግ የስትራቴጂዎችን አፈፃፀም የሚመራ ም/ቤት ለማቋቋም በተወሰነ ውሳኔ መሰረት ነው ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ፕሬዜዳንቷ ምክር ቤቱን ያቋቋሙት።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በገዛ ፍቃዳቸው ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኃላ ከባለቤታቸው የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ ጋር በመሰረቱት " ኃለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን " እንዲሁም አፍሪካ ውስጥ በተለያዩ ተቋማት በመሪነት እየሰሩ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#አየር_ኃይል

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ አየር ኃይል በአውሮፕላን ቴክኒሻንነት ሙያ ፍላጎት ያላቸውን ወጣቶች ለማሰልጠን ዛሬ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

አየር ኃይል ፤ የአውሮፕላን ቴኪኒሻንነትን ሙያ መሰልጠን የሚፈልጉ ወጣቶች የወጡትን መስፈርቶች ሊያሟሉ እንደሚገባ አመልክቷል።

ከመስፈርቶቹ አንዱ የሆነው " የትምህርትና ሌሎች መመዘኛ " ሲሆን በዚህም በአየር ኃይል በአውሮፕላን ቴክኒሻንነት ለመሰልጠን ፦

- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑ በሂሳብ ፣ ፊዚክስ ፣ እንግሊዘኛ ትምህርቶች አማካኝ ውጤህ ከ50% እና ከዚያ በላይ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።

- በ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና አጠቃላይ ውጤት 300 እና ከዚያ በላይ ያላቸው መሆን አለባቸው።

- በ2014 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ደግሞ አጠቃላይ ውጤት 250 እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ አለባቸው።

አየር ኃይል የሚያመለክቱ ወጣቶች የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱበትን ኦርጂናል ሰርተፊኬት እንዲሁም የኮሌጅ / ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ ከሚማሩበት ተቋም የመጨረሻ አመት የውጤት ሪፖርት ማቅረብ አለባቸው ብሏል።

ከዚህ ባለፈ አየር ኃይል አካዳሚ የሚቀበላቸው በራሱ በአካዳሚው የሚሰጠውን #የመግቢያ_ፈተና ማለፍ የሚችሉትን እንደሆነ ገልጿል።

የምዝገባው ቦታዎች ከላይ ተያይዟል ።

የምዝገባው ቀን ከመጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ/ም እስከ መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እንደሆነ አየር ኃይል አሳውቋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia