TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በጫማው ውስጥ 130 የክላሽንኮቭ #ጥይቶች ሊያሳልፍ የሞከረ ግለሰብ በመቱ ከተማ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረው የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ውስጥ ግለሰቡ ጥይቶቹን በጫማ ውስጥ አድርጎ ለማሳለፍ ሲሞክር ነው በሶር ፍተሻ ኬላ የተያዘው። የከተማው ፖሊስ የወንጀል ምርመራና ፍትህ ማሰጠት ስራ ሂደት መሪ ኮማንደር አበበ እንዳሉት ግለሰቡ የተያዘው በኮድ 3 - 00769 ጋም በሆነ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገው ፍተሻ መገኘቱንና ግለሰቡ በሕግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነም ገልጸዋል።

Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት 3 ነጥብ 4 በመቶ ደረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ያለው የኤች አይ ቪ የስርጭት መጠን 3 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፅ/ቤት ከአስሩም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ከተውጣጡ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ጋር የ2011 እቅድ አፈፃፀምን እየገመገመ ይገኛል።

በግምገማው ላይም በከተማዋ ያለው የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እና አሁን ላይም 3 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱ ተመልክቷል።

ለዚህም በከተማዋ ያሉ አጋላጭ ቦታዎች መስፋፋት እና የስነ ምግባር ክፍተት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

በአለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት የኤች አይ ቪ ስርጭት ከ1 በመቶ በላይ ከሆነ ያ ሀገር በበሽታው ወረርሽኝ ውስጥ ነው።

ይህም በከተማዋ ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት መጠን በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው የሚያመላክተው።

Via #AHADU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አስመራ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ልኡካቸው አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው በዛሬው እለት አስመራ የገቡት። በአስመራ ቆይታቸውም ከኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ትብብር ዙሪ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ወደ አስመራ አቅንተዋል።

Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅድመ ጥንቃቄ ይደረግ!

ከፊታችን ከአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍል ላይ የውሃ አገልግሎት እንደሚቋረጥ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ድጋፍ የሥራ ሂደት ተወካይ የሆኑት አቶ ንጉሡ ደሳለኝ ለአሐዱ እንደተናገሩት ከለገዳዲ የሚመጣው የውሃ መስመር ላይ ከፍተኛ ጥገና ማካሄድ በማስፈለጉ ሃያት፣ መገናኛ፣ ቦሌ፣ ካዛንቺስና ጉለሌ አካባቢ ውሃ እንደማይኖር ገልፀዋል፡፡ ከአርብ ምሽት ጀምሮ ጥገናው እንደሚካሄድ የገለፁት አቶ ንጉሡ እስከ ሰኞ እንደሚጠናቀቅና የህዝብ መገልገያ ተቋማት የሆኑት እንደ ጥቁር አንበሣ ሆስፒታልና የካቲት 12 የመሳሰሉ ውሃ እንዲያገኙ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ጥገናው እስከሚጠናቀቅም ህዝቡ በትዕግሥት እንዲጠብቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ከቀረጥ ነጻ እናደርጋለን" ዶ/ር አሚር አማን

የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በተመጣጠነ ዋጋ እንዲቀርብ እንዲሁም ተደራሽነቱ እንዲሰፋ ምርቶቹ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እንደማንኛውም መድኃኒት እና የህክምና አገልግሎት መስጫ መሣሪያ ተመርቶ እንዲሰራጭ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘም ተናግረዋል፡፡

"በግሌና እንደ ጤና ጥበቃ ሚንስትርነቴም፤ የንፅህና መጠበቂያ ማግኘት የእያንዳንዷ ሴት መብት መሆኑን አምናለሁ" ያሉት ዶ/ር አሚን፤ መንግሥት ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

Via #Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MoE

" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡

ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለ4 ወር የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማእከል ተብለው በተለዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የተዘጋጀ የአቅም ማሻሻያ ሪሜዲያል ትምህርት ማስተማሪያ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መላኩን ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል፡፡

Credit : #Ahadu

@tikvahethiopia
#Passport

የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ገልጿል።

ፖስፖርት ለማደስ 5 ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባው አሰራር መሰረት ግን ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።

#ICS #AHADU

@tikvahethiopia