TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ-የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ‼️

#የሲዳማ_ክልል_ጥያቄ የሕዝቤ ውሳኔ ቀን መዘግየት አስመልክቶ በቀን 14/6/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የሚካሄደው ሰልፍ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት #ማጠናቀቁን የሲዳማ ዞንና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች በጋራ በሰጡት መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የሰልፉ ዓላማ የሲዳማ ሕዝብ በክልልነት የመደራጀት መብት አስፈላጊውን ሕጋዊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ በቀን 12/3/2011 ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢቀርብም እስከ አሁን ድረስ ሕዝቤ ውሳኔ የሚካሄድበት ቀን ተወስኖ ምላሽ ባለመሰጠቱና በመዘግየቱ የሚካሄድ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅም ተችሏል።

"ሕገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር" በሚል መሪ ቃልና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ በዕለቱ ከጧቱ 1:00-6:00 ሰዓት ድረስ መነሻውን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገ በሲዳማ ዞን አስተዳደር- በአሮጌው መናኸሪያ -በተስፋዬ ግዛው ሕንጻ-በመሳይ ሆቴል አቋርጦ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ማሳረጊያ የሚደረግ ይሆናል።

በሰልፉ ላይ ከሲዳማ ዞን ሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ ሰልፈኞች የሚሳተፉ መሆኑን በመግለጽ ሰልፉም በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከተለያዩ ፀጥታ አካላትና ከሰልፉ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን በመግለጫው አክሏል።

ኀብረተሰቡም ይህን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ የራሱንና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ማንኛውንም ዓይነት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለፀጥታ አካላት ፈጥኖ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበርም ጥሪ ቀርቧል።

ከዚህም በተጨማሪ: በሰላማዊ ሰልፉ መነሻ-መድረሻ እንዲሆኑ በተፈቀዱ መንገዶች ላይ ማንኛውም ዓይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑንና የሰላማዊ ሰልፍ ትዕይንት እስኪጠናቀቅ ድረስ ለትራፍክ እንቅስቃሴ ዝግ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከዚህ ውጭ በቡድንም ሆነ በተናጠል የከተማውን ኀብረተሰብ ሰላማዊ እንቅስቃሴና የሰላማዊ ሰልፉ ሠላማዊ ህደቱን ማወክ የተለያዩ #የጦር_መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት፣በሰልፉ ወቅት በሕግ #የተከለከሉ ድርጊቶች መፈፀም በጥብቅ የተከለከሉ ሲሆን ተፈጽሞም ሲገኙ የፀጥታ አካሉ አስፈላጊውን ሕጋዊ #እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ኃላፊዎቹ በመግለጫቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

በማጠቃለያም ሕዝባዊ ትዕይንቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ኀብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰራ በድጋሚ ጥሪ በማቅረብ ኃላፊዎቹ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia