TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮማንድ_ፖስት

በደቡብ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ። ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ በዛሬው እለት ዝርዝር ተግባራትን እና የአፈጻጸም ሁኔታዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም በክልሉ በተለይም በሲዳማ ዞን እና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር በተያያዘ በደረሰው ጉዳት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ላይ የመለየትና የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ያለው ኮማንድ ፖስቱ፥ ህብረተሰቡም ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠትና ንብረቶችን የማስመለስ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ከህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘም ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ጠቅሶ፥ የፍተሻ ኬላዎችን አልፈው በግለሰቦች እጅ የሚገኙ መሳሪያዎች ተይዘዋልም ነው ያለው።

ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ከ12 ቀናት በፊት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር መከሰቱን ተከትሎ መቋቋሙ የተገለጸ ሲሆን፥ ክልሉ ወደ ቀደመ ሰላሙ እስከሚመለስ ድረስ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CMP-07-31
#ኮማንድ_ፖስት

ሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓም #በሲዳማ_ዞን እና #በሀዋሳ ከተማ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መደበኛውን የህግ ማስከበር ስርዓት ተከትሎ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን አስመልክቶ ዛሬ በሀዋሳ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CM-07-31
#ኮማንድ_ፖስት

√መደበኛ ህጎችን መጣስ
√ያልተፈቀዱ ሰልፎችን ማድረግ፣
√በዜጎች ላይ ሰብዓዊ ጥቃት መፈጸም፣
√የተለየ እና የሰላም ማደፍረስ እንቅስቃሴ ማሳየትና ማድረግ በኮማንድ ፖስቱ ተከልክለዋል።

ከዚህ ባለፈም...

በሃዋሳ ከተማ ክልከላው እስከሚነሳ ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሞተር ብስክሌታቸው የተያዘባቸው ግለሰቦች ባለቤትነታቸውን አሳውቀው መውሰድ ይችላሉ ነው ብሏል ኮማንድ ፖስቱ።

በቀጣይም ከሃዋሳ ውጭ ባሉ ሌሎች ከተሞች ከሞተር ብስክሌት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለፀጥታ ችግር ሊሆኑ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ከተስተዋሉ ክልከላ ይደረጋል።

ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ በኮማንድ ፖስቱ የሰዓት እላፊም ሆነ የተለየ ክልከላ አልተደረገም፤ ኮማንድ ፖስቱ፥ ወደፊት ከዚህ ጋር ተያይዞ የተለዩ አካባቢዎች ካሉ ይፋ ይደረጋል።

🏷አሁን ላይ በክልሉ ሁሉም መንገዶች ክፍት መሆናቸውን ተጠቅሷል፥ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ላሳየው ትብብር ምስጋና ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮማንድ_ፖስት

በቡኢ የኮማንድ ፖስት ግብረኃይል መቋቋሙ ተሰማ።

የቡኢ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያይዞ መንግስት ካስቀመጠው አቅጣጫ ውጭ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ተግባራትን መፈጸም ወይም ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም " ሲል አሣውቋል።

በከተማ አስተዳደሩም የኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት መቋቋሙን ገልጿል።

" አብዛኛው ማህበረሰብ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል " ያለው የቡኢ ከተማ " " ነገር ግን አንዳንድ ሠርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ የእነዚህ አፍራሽ አካላት ሴራ ሰለባ እንዳይሆን እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል " ብሏል።

ከዛሬ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮም በከተማው ውስጥ " ጉራጌ ክልል ወይም ክላስተር አንቀበልም " የሚሉ ተሸርቶችን ፣ኮፊያዎችን እና ባነሮችን ይዞ ወይም ለብሶ መውጣት እንደማይቻል አሳስቧል።

ከሰሞኑን የደቡብ ክልል ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው ክልል ለመመስረት በምክር ቤቶቻቸው ውሳኔ አሳልፈው ትላንት ለፌዴሬሽን ም/ቤት አቅርበዋል በዝርዝሩ ውስጥ የጉራጌ ዞን የለበትም።

በሁለት ተከፍሎ ከአጎራባች ዞኖች ጋር አንድ ክልል ይመሰርታል ከተባሉት ውስጥ አንዱ የጉራጌ ዞን ሲሆን ዞኑ በአዲሱ ክልል አደረጃጀት ዙሪያ እስካሁን በምክር ቤት ተሰብስቦ አልወሰነም / አላፀደቀም።

የዞኑ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ከቀናት በፊት ፤ " የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው " ሲሉ ገልፀው ፤ የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት ዙሪያ እንዳልተወያየትና በቀጣይ በጉዳዩ መቼ ውይይት እንደሚደግ እንደማይታወቅ ገልፀው ነበር።

@tikvahethiopia
#ኮማንድ_ፖስት

በጉራጌ ዞን በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ተከለከለ።

በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል።

ውሳኔው የተላለፈው በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ ስብሰባውን ካካሄደ በኃላ መሆኑን ከወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያወጣው መረጃ ያሳያል።

በዚህም ኮማንድ ፖስቱ ፦

- ከዛሬ ነሀሴ 12 ጀምጎ በዞኑ በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ከልክሏል።

- በመንግሥት የስራ ሰአት የቢሮ ሀላፊም ይሁን ባለሙያ በቢሮ አለመገኘት እንደማይችል አሳስቧል።

- የንግድ ሱቆችና ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋትም ከልክሏል።

- ማንኛውም ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከልክሏል።

- የሞተር ሳይክል እንቅክቃሴ እስከ ምሽት 1 ሰአት ብቻ እንዲሁም የባጃጅ እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 2 ሰአት ድረስ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አዟል።

ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉትን ትእዛዛት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ገፅ ላይ የሰፈረው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia