TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜቴክ ይቅርታ መጠየቅና እርቅ ማውረድ እንደሚፈልግ አስታወቀ‼️
.
.
"ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ ይህንን ያደርጋል"

"መልዐክ ሆኖ ቢመጣ ሰው #ሰይጣን በሚል እንደሚያነበው አውቆ ስሙን ይቀይራል"
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታወቁ፡፡

ብርጋዴር ጀነራል አህመድ ሀምዛ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንገለጹት፤ ሜቴክ ከሥራ አጋሮቹ ጋር የነበረው ግንኙነት የተበላሸና በጸብ የተሞላ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ይቅርታ መጠየቅና እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ ይህንን ይፈጽማል፤ ተቋሙም የህዝብ እንደመሆኑ ከዚህ በኋላ ሚስጢር አይኖረውም፤ እቅዶች ድረ ገጾች ላይ ይቀመጣሉ፤ ለመገናኛ ብዙኃንም ክፍት ይሆናል ብለዋል።

ተቋሙ አብረውት ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹አገልግሎት ሰጪ እስከ ሆንን ድረስ ከአገልግሎት ፈላጊው ዝቅ ብሎ ነው መታየት ያለብን›› ብለዋል፡፡ ደንበኞች ለከፈሉት ገንዘብ እንኳን አገልግሎት ሲጠይቁ ይሰጣቸው የነበረውምላሽ በጣም አደገኛና በጸብ የተሞላ እንደነበር በማስታወስ ይህንን ሁኔታ ለመቀየርም እንደሚሰራ አብራርተዋል።

ስኳር ኮርፖሬሽንን ለአብነት በመጥቀስም ከኮርፓሬሽኑ ጋር የነበረው ግንኙነት ጥሩ እንዳልነበረ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ኮርፖሬሽኑ በጣም ከፍተኛ ገንዘብ ከፍሏል፤ ተቋሙ ግን ጨርሶ ያስረከበው አንድም ፕሮጀክት የለም፡፡ ፕሮጀክቶቹን ካለማጠናቀቅም በላይ አንዳንዶቹን ወገብ ወገባቸው ላይ እያደረሰ ነው በሀይል እንዲረከቡ ያደረገው›› ሲሉ ያብራራሉ።

በሌላ በኩል መልካም ስምን ከመገንባት አንጻር አደረጃጀቱን መቀየር ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዲዬር ጀነራል አህመድ ፣ ‹‹ሜቴክ ከአሁን በኋላ መልዐክ ሆኖ ቢመጣ እንኳ ሰው ሰይጣን ብሎ ስለሚያነበው ስሙን መቀየር አስፈልጓል››ብለዋል፡፡ ይህንን ለማከናወንም መረጃዎችን የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

መረጃ የማሰባሰብ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላም በጥቂት ጊዜ ውስጥ አደረጃጀቱንና ስሙን በመቀየር በአዲሱ ስሙም አዲስ ሆኖ እንደሚቀርብና እንደ ማንኛውም የልማት ድርጅት ህግን ተከትሎ መስራት እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በስድስት ወራት ውስጥ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ የሪፎርም እቅድ መዘጋጀቱን ገልጸው፣ ይህ እቅድ ሲዘጋጅ ይሳካሉ ተብለው ከተቀመጡ ግቦች መካከል ዋናው የተቋሙን የጠፋ ስም መመለስ፣ በህግና ስርዓት ብቻ ተከትሎ እንዲሰራ ማድረግ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በተለምዶ ሰይጣን ቤት ወይም ፒራሚድ አዲስ እና ባስ አዲስ ክለብ ታሸጉ ፤ 68 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስነዋሪ ድርጊት እና ትውልድን በሚጎዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ሲጠቀሙ የተገኙ 68 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተደረገ #ድንገተኛ_ፍተሻ በተለምዶ #ሰይጣን_ቤት ወይም #ፒራሚድ_አዲስ እና #ባስ_አዲስ_ክለብ በማህበረሰቡ ተቀባይነት የሌላቸው አፀያፊ ድርጊቶች ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲፈፅሙ በመገኘታቸው ቤቶቹ መታቸጋቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሠላምና ፀጥታ ቢሮ በጋራ በመሆን ትላንት ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው ህገወጥ ተግባራት ሲፈጸምባቸው የተገኙት የምሽት ቤቶች እንዲታሸጉ የተደረገው።

በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ፦

- ከ100 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ፣
- በርካታ መዋሰሎች፣
- ከ6 በላይ ሀሺሽ የያዙ እቃዎች እንዲሁም በወቅቱ በቦታው የነበሩ ከ68 በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን እና ወጣቱን በዚህ እኩይ ድርጊት ላይ እንዲሳተፍ ሲያደርጉ የቆዩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማው አስተዳደር ገልጿል።

ነዋሪዎች በየአከባቢያቸው አዋኪና ከማህበረሰቡ ወግና ባሕል ያፈነገጡ አስነዋሪ ድርጊቶች ላይ ወጣቱ እንዲሳተፍ የሚያደርጉ ምሽት ቤቶችንና ግለሰቦችን በማጋለጥ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

#MayorOfficeofAddisAbaba

@tikvahethiopia