TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና #ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል፡፡

በተለያዩ አውቶብሶች ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን፣ የፒያሳ አካባቢ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያን #ለመዝረፍ እንቅስቃሴ መደረጉንና ፖሊሶችም በጥይት መበተናቸውን፣ ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

የፒያሳ ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተረኛ መኰንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 700 የሚሆኑ ወጣቶች ጭነው የመጡት መኪኖች በአካባቢው ወጣቶችና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ሪፖርተርም ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ተገኝቶ፣ በአማርኛ መግባባት የማይችሉ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች የሕክምና ዕርዳታ ሲጠብቁ ለማስተዋል ችሏል፡፡

በዳግማዊ በአፄ ምንልክ አደባባይ ሐውልትና አካባቢም በመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የነበረ ሲሆን፣ የፌዴራል አድማ በታኝ ፖሊስም ወደ አመሻሹ አካባቢ #ዓርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ወደ ጎዳና የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶችን #ሲበትን ተስተውሏል፡፡

በፒያሳ የሚገኙ ባንኮችና የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ ከመዘጋታቸውም በተጨማሪ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትም በመቋረጡ ብዙዎች ሲቸገሩ ታይተዋል፡፡

©ሪፓርተር
@tikvahethiopia @tsegabwolde
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #ፒያሳ_አካባቢ_ለበርካታ ዓመታት ታጥሮ የቆየውን ቦታ የፓርኪንግ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#ሐምሌ_22

ኢትዮጵያ ቡና

ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ሰኞ በሙሉ ኢትዮጵያ ከተማዎች እንደሚተከል ይጠበቃል። ሁላችንም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማልያ በመልበስ ከጠዋቱ 1:00–1:30 በተመደበልን ቦታ በሰአቱ በመገኘት ቀጥታ የክለባችንን አሻራ ለሀገራችን እናሳርፍ።

የመሳፈርያ ቦታዎች፦

#ፒያሳ_መዘጋጃ
#ሜክሲኮ_ቡና_እና_ሻይ
#መስቀል_አደባባይ
#ጀሞ
#ሳሪስ_አደይ_አበባ
#ሰባተኛ_ቶታል

#ኢትዮጵያ_ቡና @BUNA_GEBEYA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፒያሳ

በአዲስ አበባ ፤ ፒያሳ አካባቢ በተለምዶ " ዶሮ ማነቂያ " ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከስፍራው እንዲነሱ ቀነ ገደብ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምትክ የመኖሪያ እና የንግድ ቦታ ሳያዘጋጅላቸው፤ ከስፍራው " በአጭር ጊዜ ውስጥ " ተነሱ ማለቱ በነዋሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል።

የፒያሳና 4 ኪሎ አካባቢ መልሶ የማልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ ትላንት በወረዳ ደረጃ የተደረጉ ውይይቶች " በአለመግባባት " እና " በረብሻ " መበተናቸውን ተከትሎ ዛሬ ከአዲስ አበባ አስተዳደር እና ከአራዳ ክ/ከተማ የስራ ኃላፊዎች ጋር ነዋሪዎች ውይይት አድርገው ነበር።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

° በፒያሳ አካባቢ በአክሲዮን የተደራጁ ነዋሪዎች ማህበርን በሰብሳቢነት የሚመሩ ግለሰብ ፦

" ቤት ለመቀባት እንኳ 3 ቀናት ይበቃል ወይ? ትላንት በነበሩ ውይይቶች ይህንን ውሳኔ የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ለሊቱን ሙሉ ሳይተኙ አድረዋል።አሁንም በስጋት ላይ ናቸው። "

° 5 አባላት ያሉት ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን የገለጹ እናት ፦

" አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ እኔ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ናቸው። በስፍራው የታቀደው የመልሶ ማልማት ነዋሪዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ እና ምትክ የመኖሪያ ስፍራ ያዘጋጀ ሊሆን ይገባዋል። "

° ሌላኛዋ የአካባቢው ነዋሪ ፦

" ለልማት ተነሺዎች የሚያዘጋጀው አማራጭ የስፍራውን ማህበራዊ ትስስር በማይበጥስ መልኩ ሊደርግ ይገባል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያለን የአካባቢው ነዋሪዎች እርስ በእርስ ተደጋግፈን የምንኖር በመሆናችን ምትክ የኮንዶሚኒየም ቤት የሚሰጠን ከሆነ በአንድ ቦታ ላይ የምንሰፍርበት ሁኔታ ይመቻች ። "

ከባለስልጣናት ምን ምላሽ ተሰጠ ?

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ፤ ነዋሪዎቹን ከቦታው ለማንሳት ያቀደው በዘጠና ቀናት ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

አስተዳደሩ ለነዋሪዎች  ምትክ የኮንዶሚኒየም፣ የቀበሌ እና የኪራይ ቤቶች እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብተዋል። 

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ተቀባ ፤ አስተዳደሩ " ቅደመ ሁኔታ ሳያሟላ አንድም ሰው አይነቃነቅም " ብለዋል።

የከተማው አስተዳደር " ቅደመ ሁኔታውን ካሟላ " ነዋሪዎች በ3 ቀን ቢነሱ ችግር እንደማይፈጥርም ጠቁመዋል።

" ይህ ፕሮጀክት እንዳያልቅ የሚያንጓትት ካለ ኃላፊነቱን ራሱ ነው የሚወስደው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በዛሬው ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በመልሶ ማልማቱ የልማት ተነሺዎቹን ሂደት የሚከታተል ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተከናውኗል።

በመልሶ ማልማት እቅዱ የተካተተውን የፒያሳ አካባቢን በ6 በመክፈል፤ ከእያንዳንዱ ስፍራ 6 ሰዎች በህዝብ ተመርጠዋል። 

(ከላይ በፒያሳ ስለሚካሄደው መልሶ ማልማት ስራ ማብራሪያ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#ዓድዋ #ፒያሳ

የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ እንደ ከዚህ ቀደሙ በ " ምኒሊክ አደባባይ " በዓሉን ማክበር የሚፈልግ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ ተሰብስቦ እንዲያከብር አልተደረገም የሚል ቅሬታ ያደረባቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

አንድ በጥዋት በዓሉን አከብራለሁ ብሎ ወደ ፒያሳ " ምኒሊክ አደባባይ " ያቀና የአዲስ አበባ ነዋሪ ፥ ምኒሊክ አደባባይ በከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች ጥበቃ ስር እንደነበር ፣ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ብቻ ማለፍ እንደሚቻል፣ ጥብቅ የሆነ ፍተሻም እንደነበር ገልጿል።

በዓሉን ለማክበር ወደ ዓድዋ መታሰቢያም ፍቃድ ከተሰጠው ውጭ መግባት እንደማይቻል በዚህም በዓሉም ለማክበር እንዳልቻለ ጠቁሟል።

ይህ የህዝብ በዓል በመሆኑ ህዝብ በመረጠው መንገድ ወይም ተካፋይ በሆነበት መንገድ ሊከበር ይገባ ነበር ሲል ያደረበትን ቅሬታ አጋርቷል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፤ " ዛሬ ከባለፈው ዓመት በበለጠ የዓድዋ በዓልን ለማክብር የመጣ ሰው ከቴዎድሮስ አደባባይ ጀምሮ መግባት ባለመቻሉ ሲመለስ ነበር። ፈረስ እና የተለያዩ የዓድዋ አልባሳትን የለበሱ ሰዎችም ሲመለሱ ነበር " ብሏል።

" በዓሉን ለማክበር ወደ ዓድዋ መታሰቢያ እየገቡ የነበሩትም በቀበሌ ይመስለኛል ባጅ የተሰጣቸው ብቻ ናቸው " ያለው ይኸው አስተያየት ሰጪ ፤ በዓሉ ሁሉም ለማክበር ባለመቻሉ እንዳደበዘዘው ጠቁሟል።

ይኸው አስተያየት ሰጪ ፤ " ካለፈው ሁለት ዓመት ጀምሮ ዓድዋን ከፒያሳ ምኒሊክ አደባባይ ለማላቀቅ ስራዎች የተሰሩ ይመስለኛል " ሲል ገልጾ " የኔ ጥያቄ የተገነባው ዓድዋ መታሰቢያ ከዚህ በኃላ ባለስልጣናት እና የሚፈልጉት ሰው ብቻ በብቸኝነት ለማክብረ ነው ? ወይስ በዓሉን ማክበር የሚፈልግ ህዝብ ተሰብስቦ እንዲከበርበት ነው ? " ብሏል።

መንግሥት የ128ኛው ዓድዋ ድል በዓል ከከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ ክብሩን በጠበቀ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን እየገለፀ ይገኛል።

@tikvahethiopia