ጎንደር🔝
በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው #የሰላም_መድረክ የአማራ ክልል ሰላም ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ጄነራል #አሳምነው_ጽጌ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ጄኔራሉ ‹‹ከየትኛውም ወገን ያሉ አጥፊዎች #ዘርን_ሳያማክል በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡›› ቅማንት እና አማራን ሽፋን አድርጎ ግጭትን ሲያነሳሳ የነበረ ማንኛውም አካልም ስርዓት እንዲይዝ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠው ህዝብ፤ አጥፊዎችን በመለየትና በማጋለጥ አንድነቱን ማጠናከር እንጂ መፍትሄውን ከሌላ አካል መሻት የለበትም ነው ያሉት፡፡
የአካባቢውን ሰላም የሚጠብቀው ህብረተሰቡ መሆኑን በመገንዝብ ይህን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ወጣቶች እና አርሶ አደሮችም ሰላምና አካባቢውን ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም እንዲያገኙ የክልሉ ሰላም ደህንነት ቢሮ ይሰራል፡፡
የተከሰቱ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈታሉ፡፡ ነገር ግን በየጊዜው ለሚፈጠሩ የብጥብጥ አጀንዳዎች መጠቀሚያ ላለመሆን ነቅቶ እና እየተናበቡ መንቀሳቀስ ይገባል ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፡፡
ውይይቱም በዕለቱ ምክክር ላይ የተነሱ ሀሳቦችን የሚያጠናክሩ ባለሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ተጠናቋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia