TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እገታ

ከሰሞኑን ጎንደር ላይ አንድ እስራኤላዊ ዜጋ ታግቷል ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግሥት ዜጋውን ለማስለቀቅ ፍለጋ ጀምሮ ነበር።

ነገር ግን ጎንደር ላይ ታግቷል ተብሎ የተነገረው ኤስራኤላዊ ጉዳይ ውሸት ሆኖ በመገኘቱ የእስራኤል ባለስልጣናት ፍለጋቸውን እንዳቋረጡ የእስራኤል ጋዜጦች ዘግበዋል።

ጋዜጦቹ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት ወደ ትውልድ ሀገራቸው ያመሩት የ79 ዓመቱ ፍራንሲስ አደባባዪ በውሸት " ታግቻለው " በማለት የማስለቀቂያውን ገንዘብ በመፈለግ ድርጊቱን እንደፈፀሙ #እንደሚያምን ፅፈዋል።

ባለፈው ሳምንት የፍረንሲስ አደባባዪ ዘመዶች እንዳስታወቁት ከሆነ ፍረንሲስ እጅ እና እግራቸውን ታስረው በታጠቀ ሰው ሲጠበቁ የሚያሳይ የተቀዳ መልእክት፣ ምስሎች እና አጭር ቪዲዮ ክሊፕ አጋቾቹ ልከውላቸዋል።

ታጋቾቹ ከእስር እንዲፈቱ 2.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወይም 45,000 ዶላር እየጠየቁ ነበር ተብሏል።

በተቀዳው መልዕክት ላይ ፍራንሲስ " እርዱኝ ወንድም እና እህቶቼ ፤ በጫካ ውስጥ ነኝ፤ ታግቻለሁ ፤ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ነው ... ይህንን ችግር በጠላቶቼም ላይ እንዲሆን አልመኝም " ሲሉ ተደምጠዋል።

የእስራኤል ባለስልጣናትም ከ #ኢንተርፖል ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ነበር።

ነገር ግን ፍራንሲስ አደባባዪ ከእስራኤል የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎችን እመለሱ መሆኑን ካወቁ በኋላ ባለስልጣናት ፍለጋውን ማቋረጣቸውን ጋዜጦቹ ዘግበዋል።

ዘመዶቻቸው ግን አሁንም ድረስ ፍራንሲስ አደባባዪ መታገታቸውን እና ለደህንነታቸው  አጥብቀው እንደሚሰጉ ተናግረዋል። ለእስራኤል መንግሥት አቤት እንደሚሉም አሳውቀዋል።

ፍራንሲስ የ79 አመት የእድሜ ባለፀጋና ባለትዳር እንዲሁም የ8 ልጆች አባት መሆናቸውን የገለፁት ቤተሰቦቻቸው እገታውን ያቀነባበረ አካል ስለመኖሩ ምልክት እንዳላገኙ  በእርግጠንኘት ደግሞ እገታውን እሳቸው (ፍራንሲስ) እንዳላቀነባበሩ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia