TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላብራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል በተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለፉት 24 ሰዓት በአጠቃላይ ሰላሳ አራት (34) ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ…
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ!
የአማራ ክልል 'የምዕራብ ጎንደር ዞን' ማህበራዊ ልማት መምሪያ በድንበር አካባቢ የሚደረገው የሠዎች ዝውውር #አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር የኮሮና ቫይረስ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከፍተኛ ህሙማን ሊመዘገብ እንደሚችል አስታውቋል።
የአማራ ክልል ባለስልጣናት እንዳሉት በአማካይ በቀን ከ100 እስከ 150 ሰዎች ድንበር #አቋርጠው ወደ ክልሉ ይገባሉ።
ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከሚደረጉት ከነዚሁ ሰዎች መካከል በምርመራ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም።
የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንደገለፁት ዞኑ ከጎረቤት ሱዳን 400 ኪሎ ሜትር ይዋሰናል።
በዚህም በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ድንበር እያቋረጠ ወደ ዞኑ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ችግሩ 'ከአቅም በላይ' እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ #ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ከሱዳንና ከጅቡቲ አካባቢዎች ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ሰዎች ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ከፌደራል መንግስት ጋር በጋራ የምንፈታው ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia