#NBE
ብሔራዊ ባንክ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ላይ ወጥቷል ባለው አሳሳች ዘገባና አሉባልታ ምክንያት በዋጋ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ሰው ሠራሽ #ጭማሪ ተቀባይነት የለውም፤ ጥብቅ ክትትልም ይደረጋል ብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ምን አለ ?
- በጋዜጣዊ በህዳር 23/2016 እትም ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ የፕላን፤ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ከአንድ የፓርላማ አባል ቀረበ ከተባለ አስተያየት ላይ ተነሥቶ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ በቅርብ ጊዜና በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ለማድረግ ማቀዱን በማስመልከት የወጣው ዘገባ ፈጽሞ ሐሰተኛና አሳሳች፣ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ያፈነገጠ ድርጊት ነው ብሏል።
- " ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዮን በተመለከተ የቀረበ ዕቅድ የለም " ሲል ገልጿል።
- እስከ 4 ስዓት በፈጀው ውይይት ወቅት በብሔራዊ ባንክ የተነገረ ነገር እንደሌለ ህብራተሰቡ መረዳት አለበት ብሏል።
- በዚህ አሳሳች ዘገባና አሉባልታ ምክንያት በዋጋ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ሰው ሠራሽ ጭማሪ ተቀባይነት የለውም ጥብቅ ክትትልም ይደረጋል ብሏል።
በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ምን ይላል ?
- ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊውና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ሰፊ የውጭ ምንዛሪ ተመን ልዩነት #በ95_በመቶ ለማጥበብ ዕቅድ መያዙ መታወቁ ፤ ይህ ዕቅድ ግን መቼና እንዴት እንደሚፈጸም የታወቀ ነገር እንደሌለ ያስረዳል።
- ይህ ባንኩ ዕቅድ የተሰማውም ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ/ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የብሔራዊ ባንክን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመርያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ብሏል።
- ብሔራዊ ባንክ ይህንን ዕቅዱን በቋሚ ኮሚቴው የግምገማ መድረክ ላይ #በይፋ_ባያቀርብም፣ ለቋሚ ኮሚቴው የቀረበን #ሰነድ የተመለከቱ አንድ የም/ ቤት አባል፤ ዕቅዱን ከሪፖርቱ ላይ እንደተመለከቱ ጠቅሰው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የም/ቤቱ አባሉ ምን አሉ ?
" ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመንና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት በ95 በመቶ የማቀራረብ ዕቅድ ይዟል።
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊው የምንዛሪ ተመንና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት እጥፍ ነው።
ስለዚህ ልዩነቱን በ95% ለማጥበብ የተያዘው ዕቅድ በተጨባጭ የሚቻል ነው ወይ ? ወይስ ዲቫሉዌሽን ለማድረግ (የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም) አስባችኋል? " ሲሉ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
- የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ፤ "እንደየ ሁኔታው እየተመዘኑ የሚወሰዱ ዕርምጃዎች ይኖራሉ እንጂ በዚህ ወቅት ይህ ዕርምጃ ይወሰዳል ብሎ ብሔራዊ ባንክ ሊናገር አይችልም " የሚል ምላሽ መስጠታቸው በጋዜጣው ላይ ሰፍሯል።
- አቶ ማሞ " የውጭ ምንዛሪ ጉዳይን በተመለከተ ሁሉን ነገር እዚህ መናገር አልችልም። ብሔራዊ ባንክን በሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ የምናደርገው ውይይት ተገቢ ላልሆነ ስፔኩሌሽን (ግምት) የሚያጋልጥ መሆን የለበትም። ገና ጥናት ያልተደረገበት ጉዳይ ላይ ብንወያይም ትርጉም የለውም። ዋናው ቁልፍ ነገር ዓላማችን ላይ መወያየት ሊሆን ይገባል። የባንኩ ዋና ዓላማ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታና የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት እንዲኖር ማስቻል ነው " ማለታቸውንም ጋዜጣው አስፍሯል።
ብሔራዊ ባንክ ይህን ዘገባ ነው #አሳሳችና #አሉባልታ ነው ያለው።
$ በአሁኑ ወቅት የዶላር ሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመን 55.5 ብር የደረሰ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያው ግን አንድ ዶላር እስከ 110 ብር እየተመነዘረ ይገኛል።
@tikvahethiopia