TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

" ፕሬዜዳንት በሆንን በአንድ ሳምንት ውስጥ ቲክቶክን እናግዳለን " ያለቱ የሪፐብሊካን እጩዎች !

የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በ2024 ይካሄዳል።

የሪፐብሊካን የፕሬዜዳንታዊ እጩዎች ቢሮ በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት " #ቲክቶክ " የተሰኘውን መተግበሪያ እንደሚያግዱ ገልጸዋል።

እጩዎቹ ሰሞኑን በነበረ ክርክር መድረክ ላይ ነው ይህን የገለፁት።

እጩዎች የቻይናን መረጃ መሰብሰብን ለመዋጋት አንዴ ፕሬዜዳንት ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ይግቡ እንጂ " ቲክቶክ" ን እስከወዲያኛው እንደሚያግዱት ገልጸዋል።

ክሪስ ክርስቲ የተባሉ የሪፐብሊካን እጩ ምን አሉ ?

እኚህ እጩ " ቲክቶክ " መረጃዎችን ከመሰብሰብ ባለፈ በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የወጣት አሜሪካውያንን አእምሮ እየበከለ ነው ብለዋል። " ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ ሆን ብለው ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ቲክቶክ " በአልጎሪዝሙ አሰቃቂ፣ ያልተገቡ፣ ከፋፋይ፣ አፍራሽ ፣ የወጣቶችን አእምሮ የሚበክሉ ጉዳዮችን ከፍተኛ ደረጃ ወደ ተጠቃሚው እንዲገፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ይህም ቻይና አሜሪካንን ለመከፋፈል ይበልጥ እየተጠቀመችበት ያለ ተግባር ነው ሲሉ ከሰዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው " ቲክቶክን ማገድ " በተመለከት ብዙ ሲናገሩ እንደነበር ነገር ግን መተግበሪያውን ማገድ ሲገባቸው ያን አለማድረጋቸው የሚያስወቅስ እንደሆነ ገልጸዋል።

እሳቸው ፕሬዜዳንት ሆነው በመጡ በመጀመሪያው ሳምንት ቲክቶክን እንደሚያግዱ አሳውቀዋል።

ሮን ዴሳንቲስ የተባሉ እጩ ደግሞ " የአሜሪካን ህዝብ ለመጠበቅ ስንል ቲክቶክን የማገድ እርምጃ እናሳያችኃለን " ብለዋል። ፕሬዜዳንት ሆነው ሲመጡም ይህንን እንደሚያደርጉትን ገልጸዋል።

ቲም ስኮት የተባሉት እጩ ፤ " እኛ ማድረግ ያለብን ቲክቶክን ማገድ ነው ፤ አለቀ !! " ብለዋል።

በቀድሞው ፕሬዝደንት ትራምፕ ቲክቶክን ለማገድ ሁለት ጊዜ ሲሞከር አይተናል ያለቱ ስኮት ፤ ነገርግን በፌደራል ፍርድ ቤቶቻችን እንዳይፈፀም ተደርጓል ሲል አስታውሰዋል።

ቲክቶክን ማገድ ካልተቻለ በመተግበሪያው ላይ ያለውን የቻይናን ተፅእኖ መኖር እንደወዲያኛው #ማስወገድ ነው ብለዋል።

ባይትዳንስ የተሰኘው ኩባንያ ንብረት የሆነው " ቲክቶክ " ከዚህ ቀደም በተለይም ግላዊ መረጃን በመበዝበዝ እና ከቻይና መንግሥት ጋር የተቆራኘ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ሲደርስበት ነበር ፤ ኩባንያው የቻይና መንግሥት መረጃውን እንደማያገኝበትና ቻይና ያለው ቲክቶክ ከሌላው ዓለም ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ደጋግሞ አሳውቋል።

@tikvahethiopia