TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስቸኳይ መረጃ እና ትብብር‼️

(በአፋጣኝ ሼር እንዲያደርጉ እንማፀናለን)

ከቤኒሻንጉል ተፈናቅለው በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ለሚገኙ አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን እርዳታ ለማሰባሰብ በአዲስ አበባ እና አካባቢው ለሚኖሩ ወገኖቻችን ባቀረብነው የእርዳታ ጥሪ፤ በርካታ ወገኖቻችን መልዕክቱን ሼር በማድረግ ከፍተኛ ርብርብ በማድረጋችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ በሀገር ፍቅር የሚኖረውን የቁሳቁስ፣ አልባሳትና ምግቦች እርዳታ ከሰኞ ቀደም ባሉ ቦታዎች ግዚያዊ መረከቢያ #ጣቢያዎች እንዲኖሩ አብዛኛዎቻችሁ ጠይቃችኋል።

በዚህም መሰረት ከነገ ሐሙስ ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ፤ በሁሉም አቅጣጫ ግዚያዊ መረከቢያ ጣቢያዎች እና #ማስተባበሪያ ማዕከሎችን እናዘጋጃለን። ለዚህም የመረከቢያ ቦታ ችግራችንን ለመፍታት ይቻል ዘንድ ፍቃደኛ የሆናችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ
በየሰፈራችሁ ምቹ የሆነ መረከቢያ ቦታ በመፍቀድ እንድትተባበሩን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

* ቦታው ቢቻል ለምልክት ግልጽ የሆነ ቢሆንና ከዝናብና ፀሐይ ውጪ መሆን የሚችል ቢሆን ይመረጣል።

*ለትራንስፖርት አመቺ ቢሆን መልካም ነው።

*የንግድ ድርጅቶችና ተቋማትም መሆን ይችላሉ።

*የተሰበሰቡት ንብረቶች በሙሉ ወደ ዋናው መረከቢያ ጣቢያ (ሀገር ፍቅር ቴአትር) ተሰባስበው የሚገቡት ሰኞ እና ማክሰኞ በመሆኑ ቦታችሁን የምትፈቅዱልን በሙሉ እስከ ሰኞ ድረስ የእርዳታዎቹን ደህንነት ለመጠበቅ የማትቸገሩ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ትከቱልን ዘንድ እንለምናለን።

~በዚህ መሰረት ፍቃደኛ የሆናችሁ በሙሉ በቀጣዩ ስልክ ቁጥር ~ 0930 36 52 44
መሐመድ ካሳ እና ያሬድ ሹመቴ ብላችሁ ፈጣን ትብብራችሁን እንድትገልፁልን በማክበር እንጠይቃለን።

(በተደጋጋሚ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃለፊነታችንን እንወጣ ዘንድ እንለምናለን)

#ቅድሚያ_ለሰብዓዊነት!!

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia