TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትኩረት

በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተ የዝናብ እጥረት የተነሳ ድርቅ በሰው እና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ስር በምትገኘው ሐመር ወረዳ እንደ ሶማሌ እና እንደ ቦረና ሁሉ ለወረዳው ለአርብቶ አደሮች ጊዜው ከፍቷል ተብሏል።

በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት የሆኑት የቀንድ ከብቶቹ በየጫካና ጥሻዎቹ ውስጥ በተኙበት እየሞቱ ይገኛሉ።

አሁን ላይ በሐመር ድርቁ ዕለት በዕለት የአርብቶ አደሩ መተዳደሪያ የሆኑ የቁም እንስሳትን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨረሰ ነው።

ውኃ የለም፤ ሣር የለም። አርብቶ አደሩ የእንስሳት ተዋጽዖ በመመገብ ነው የሚኖረው። ዝናብ የለም በዚህ ምክንያት ብዙ ከብቶች እየሞቱ ነው።

ሰውም በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በረሐብ እየተሰቃየ መሆኑን ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በወረዳው ለተከታታይ አራት ዓመት እና በላይ በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ነው ድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ የተፈጠረው ተብሏል።

የእንስሳት መኖ አለመኖሩ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረ ሲሆን በየትኛውም አማራጭ ውኃ ማግኘት ወደማይቻልበት ሁኔታ ተደርሷል።

ለ4 አመታትና በላይ በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ እንስሳቱ የሚግጡት ሳር ጠፍቷል።

ወንዞች በመድረቃቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው የቀንድ ከብቶች ለሰው ልጅ የመጠጥ ውሃ የተቆፈሩ የጉድጓድ ውሃዎችን ፖምፕ እየተደረጉ ለማጠጣት ቢሞከርም ከአቅም በላይ ሆኗል።

የከርሰምድር ውሃ እየሸሸ መሄዱና የፓምፖች ብልሽት እየተከሰተ በመሆኑ በሰው ላይ ከዚህ የከፋ ችግር ከመከሰቱ በፊት መንግስትና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ሐመር_ወረዳ

@tikvahethiopia