TIKVAH-ETHIOPIA
" ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው " ከሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ያሳለፈው አዲስ አደረጃጀት በጉጂ ዞን በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እንደገጠመው የቲክቫህ አባላት ከየአካባቢው አሳውቀዋል። ትላንት ከዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በቦሬ ማቲ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ተሰምቷል። አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ…
" ሠልፉ ያልተፈቀደ ነበር " - የቦሬ ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት
ትላንት በኦሮሚያ ክልል፣ ጉጂ ዞን ቦሬ ከተማ ከተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ 3 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው መግለፁ ይታወሳል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቦሬ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ትላንት በከተማው ስለደረሰው ጉዳት ማረጋገጫ ሰጥቷል።
የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቡሌ ትናንት በከተማው በተካሄደው ሠልፍ ጉዳት መድረሱን አረጋግጠው " ሠልፉ ያልተፈቀደ " እንደነበር ገልጸዋል።
ኃላፊው ፤ " አንዳንድ የሠልፉ ተሰታፊዎች በተቋማት ላይ #ድንጋይ በመወርወር እና ገበያ በመበተን ሁከት ለመፍጠር ሞክረዋል " ብለዋል።
" የፀጥታ አባላት የጉዳቱ መጠን ሳይሰፋ ለመቆጣጠር ችለዋል " ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
Credit : #ዶቼቨለ_ሬድዮ
Photo : Social Media
@tikvahethiopia

#Mekelle ተጨማሪ ፎቶዎች ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት #በብፁዕ_አቡነ_ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ትግራይ ፣ መቐለ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል። Photo : Tigrai Television @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ ዛሬ በመቐለ ከተማ የብፁዕ አቡነ ዮሓንስ የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት ማድረጋቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት አሳውቋል።
Photo Credit ፦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት / ድምፂ ወያነ
@tikvahethiopia
Photo Credit ፦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት / ድምፂ ወያነ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ ዛሬ በመቐለ ከተማ የብፁዕ አቡነ ዮሓንስ የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት ማድረጋቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት አሳውቋል። Photo Credit ፦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት / ድምፂ ወያነ @tikvahethiopia
" በሰላም ወደ መንበረ ፓትርያርክ ተመልሰዋል " - የቤተክርስቲያና ሕዝብ ግንኙነት
ቅዱስነታቸው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት መርሐ ግብር ላይ በመገኘት አሸኛኘት ካደረጉ በኋላ በሰላም ወደ መንበረ ፓትርያርክ መመለሳቸውን የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት አሳውቋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የብፁዕ አቡነ ዮሐንስን እረፍት ተከትሎ ዛሬ ጠዋት #መቐለ የገቡ ሲሆን በብፁዕነታቸው የሽኝት መርሐ ግብር ላይ የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ከሰጡ በኋላ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ በሰላም መግባታቸውን የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

#አዲስ_አበባ #የሚዘጉ_መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በዕለቱ በ #ምኒሊክ_አደባባይ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የአከባበር…
#ማስታወሻ
ነገ የካቲት 23/2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
👉 በምኒሊክ አደባባይ በሚከናወነን የአከባበር ስነ ስርዓት ምክንያት ፦
• ከሰሜን ሆቴል ትራፊክ መብራት ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከዮሀንስ መብራት ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከጊዮርጊስ ቴሌ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከሀገር ፍቅር መታጠፊያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከብሪቲሽ ካውንስል ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከሲኒማ አምፒር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከእሪ በከንቱ ( እሪ በስራ) ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአራዳ ህንፃ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከሰባራ ባቡር ቶታል ወደ ጊዮርጊስ ቴሌ መስቀለኛ
• ከዳትሰን ሰፈር መገንጠያ ወደ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡
👉 ከምኒሊክ አደባባይ ወደ አደዋ ድልድይ የእግር ጉዞ በማድረግ በአድዋ ድልድይ የሚከናወነውን ስነ ስርኣት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦
• ከእንግሊዝ ኤምባሲ ትራፊክ መብራት ወደ አድዋ ድልድይ
• ከፈረስ ቤት ኮንደሚኒየም መታጠፊያ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከምስራቅ መገንጠያ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከሴፍቲ መብራት ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከ22 አደባባይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከቺቺኒያ ወደ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከካዛንቺስ ቶታል ወደ አቧሬ
• ከድሮው ሰንደይ ማርኬት ወደ ሴቶች አደባባይ
• ከሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከአቧሬ ጀርመን አደባባይ ወደ ሴቶች አደባባይ ያሉት መንገዶችን ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ #ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
👉 በመስቀል አደባባይ የሚከናወነው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፦
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከፒኮክ ትራፊክ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ባምቢስ
• ከጥላሁን አደባባይ( መሿለኪያ) ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር
• አልሳምጨለለቅ ህንፃ ወደ ለገሀር
• ከገነት መብራት ወደ ለገሀር
• ከጠማማ ፎቅ (ገነት ሆቴል) ወደ ሜክሲኮ
• ከሱዳን ኤምባሲ (ጠማማ ፎቅ) ወደ ሜክሲኮ
• ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ወደ ሜክሲኮ
• ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ
• ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም ወደ ለገሐር
• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቲያትር
• ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት መብራት
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን መብራት
• ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኢምግሬሽን መብራት(ፖስታ ቤት)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ
• ከሚያዚያ 27 አደባባይ (4 ኪሎ) ወደ ፓርላማ መብራት
• ከጥይት ቤት ወደ ግቢ ገብርኤል
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ፖሊስ ገልጿል።
ፖሊስ አሽከርካሪዎች #ሌሎች_አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።
ከዛሬ ረቡዕ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሸከርካሪን #አቁሞ_መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

#ዓድዋ
እንኳን ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ቀን በሰላም፣ በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ !!
" ዓድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች " - ጂጂ
መልካም የድል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ !!
@tikvahethiopia
እንኳን ለ127ኛው የዓድዋ ድል በዓል ቀን በሰላም፣ በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ !!
" ዓድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእነርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች " - ጂጂ
መልካም የድል በዓል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ !!
@tikvahethiopia
የዓድዋ በዓል በአዲስ አበባ ?
ዛሬ የዓድዋ ድል በዓል በመላው ሀገሪቱ እየተከበረ ነው።
በመዲናዋ በሚገኘው የአፄ ሚኒሊክ ሀውልት ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ እንዳልነበር ወደ ስፍራው የሄዱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቤተሰባችን አባል እንዲህ ሲል ዛሬ ጥዋት የተመለከተው አስረድቷል፦
" በመጀመሪያ ከጥቁር አንበሳ ጀምሮ ቀይ ለባሾች፣ አድማ በታኞች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከታች ወደ ላይ እየተመላለሱ ህዝቡን ሲቃኙ ነበር።
ህዝቡ በብዛት ወደ ምኒሊክ ሃውልት እንደወትሮ እየሄደ ነበር፤ እኔም እንደ ድሮው መስሎኝ እስከ ሃውልቱ ድረስ ሄጃለሁ።
እዛ ስንደርስ ግን ድሮ ሚደረጉ የነበሩ ፕሮግራሞች ምንም አልነበሩም። ፌዴራሎች ሀውልቱን ከበው መንገዱን ዘግተው ነበር።
ህዝቡ መበሳጨት ጀምሮ 'ይሄ ነው ንጉሱ' እያለ መጨፈር ጀመረ አልፎ አልፎም ' ሿ ሿ እያለ ድምፁን ያሰማል። ጥቂት ቆይቶ ቀይ ለባሾች እና ፌደራሎች አዲስ ከሚሰራው ዓድዋ ህንፃ እና ማዘጋጃ መሃል ይመጡ የነበሩ ሰዎችን አስቆሙ።
እኔ ቀድሜ ደርሼ ስለነበር ወደ ምኒልክ አደባባይ ተጠግቶ የተቆረጠው ህዝብ ውስጥ ነበርኩኝ፤ የአድማ በተና መኪና ሲጠጋ ሳይ ጥግ ይዤ ወደ ሀውልቱ እንዳይደርስ የተቆረጠው ህዝብ ጋር ተቀላቀልኩ፤ ወዲያድ መተኮስ ተጀመረ ህዝቡም መሮጥ ጀመረ።
ከላይ የላኩት ቪድዮ እና ፎቶ ቸርቸል ከወርድኩ በኃላ የቀረፅኩት ነው። "
በሌላ በኩል፤ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በዓሉ በምኒልክ አደባባይ መከበሩንና ባለስልጣናት የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን ዘግበዋል።
ከዚህ ባለፈው በዓሉ በዓድዋ ድልድይ ስለመከበሩ አመልክተወዋል።